የቁስቋም ማርያም በዓልና የገዳመ ሲታውያን ፪ኛ ደረጃ ካቶሊክ ት/ቤት መሠረት ድንጋይ ሥርዓት በደብረ ብርሃን

Category: ዜናዎች Written by Super User Hits: 9907

DebreBrhanእሑድ ኅዳር 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ብፁእ አባታችን ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው የደብረ ማርያም ቁስቋም ዓመታዊ በዓል ላይ በመገኘት ከአካባቢው፣ ከአዲስ አበባ ከመጡ ምእመንና ከብዙ ካህናት ጋር በጋራ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርጉ።

ይህ ደብር የሚተዳደረው ከቦታው 27 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በሚገኘው በደብረ መድኃኔዓለም የሲታውያን ገዳም መነኮሳት ሲሆን፤ በዚሁ ገዳም በደብረ ብርሃን ከተማ ሊከፈት ለታቀደው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም ብፁእ አባታችን ካርዲናል የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል።