ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትሪያሪክ ዘኢትዮጵያ ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጋር ሊገናኙ ነው

Patriarch Mathias of Ethiopia Romeየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ያኑ ብ.ወ.አ. ማቲያስ ፓትሪያርክ ዘኢትዮጵያ ሰኞ የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጋር ለመገናኘት ወደ ሮም እንደሚያቀኑ ተገለጸ። ፓትሪያርክ ማቲያስ በዚሁ ጉዟቸው ወቅት በካቶሊካዊት ቤ/ያን የክርስቲያኖች ኅብረት እንቅስቃሴን ከሚያጠናክረው ምክር ቤት ጋር ስብሰባ እንደሚያደርጉና በቫቲካን የሚገኘውን የሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ መቃብር እንደሚጎበኙም ታውቋል።
በሮም በሚገኘው የኡርባኒያኑም ኮሌጅ ቤተ ጸሎት ፓትሪያርኩና በሮም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጋራ ሥርዓተ አምልኮ እንደሚያካሂዱ መርኃ ግብር ወጥቷል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በካቶሊክ ቤ/ያን መካከል ያለው ግንኙነት በጥሩ መልኩ የተጠናከረው በቀድሞው ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ ጊዜ ሲሆን እርሳቸው እ.ኤ.አ. በ1993 ዓ.ም. ከር.ሊ.ጳጳሳት ቅ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊና እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. ደግሞ ከር.ሊ.ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው ጋር መገናኘታቸው ይታውሳል።
ምንጭ፡- http://en.radiovaticana.va/news/2016/02/25/ethiopias_orthodox_patriarch_to_meet_with_pope_francis/1211046

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።