ሢመተ ክህነት በማኅበረ ሲታውያን

ሢመተ ክህነት በማኅበረ ሲታውያን

Abba Tadeosጥር ፯ ቀን ፪፻፱ ዓ.ም. ብፁእ አባታችን ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ለዲያቆን ወመነኮስ ታዴዎስ ተስፋዬ ሢመተ ክህነትን አከናውነዋል።

አባ ታዴዎስ በአ.አ. የካፑቺን ፍልስፍናና ነገረ መለኮታዊ ተቋም ለሰባት ዓመታት ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን በተጨማሪም እንደ ሲታዊ መነኮስ ሁለት የሰአሊነት አንድ የተመክሮ እንዲሁም አንድ የቅድመ ክህነት ዓመታትን ካሳለፉ በኋላ ፲፱ ቀዳስያን ካህናት፤ ወላጅ፤ ቤተሰቦቻቸውና ሌሎች ምእመናን በተገኙበት በቅ. ዮሴፍ ዘሲታውያን ቁምስና ቤ/ያን ክህነትን ተቀብለዋል። 

በእለቱ የገዳመ ሲታውያን ዘቅዱስ ዮሴፍ ማርያም ጽዮን ት/ቤት ለሁለተኛ ደረጃ ማስፋፊያ ያሠራውን አዲስ ሕንጻ በብፁእ አባታችን ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስና በኢትዮጵያ የሲታውያን ማኅበር ኃላፊ አባ ባዘዘው ግዛው የተመረቀ ሲሆን ማኅበሩ በሰፊው ደግሞ ካቶሊካዊት ቤ/ያን በኢትዮጵያ ትውልድን በትምህርት በመቅረጽ ዙሪያ ያላትን ሰፊና አኩሪ ነባር ታሪክ በብቃት የሚያስቀጥል መሆኑም በእለቱ ለተገኙት የት/ቤቱ መምህራን፤ የተማሪዎች ወላጆችና ተጋባዥ እንግዶች ተግልጿል።

School Inauguration