"አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አግኝተናል!"

"አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አግኝተናል!"

balco extraዛሬ መጋቢት ፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. አመሻሹ ላይ በቫቲካን ከሚገኘው ሲስቲና ቤተ ጸሎት ጭስ ማውጫ ነጭ ጭስ መውጣቱ ለዓለም የአዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን መመረጥ ያወጀ ሲሆን ከዚያም ከአንድ ሰዓት በኋላ አካባቢ በተለመደው ሥርዓት በደብረ ቅዱስ ጴጥሮስ ሕንጻ መስኮት እጩ ከነበሩት 115 ካርዲናሎች ውስጥ 2/3ኛውን ደምጽ ማለትም ከ77 የምርጫ ድምጽ በላይ በማግኘት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ 265ኛው የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ በመሆን በዚህ መንበር ላይ ሆነው እንዲያገለግሉ የተመረጡት ማን እንደሆኑ ተገለጠ።

አዲስ የተመረጡት ር.ሊ.ጳጳሳት አርጀንቲናዊው የቦነስ አይረሱ ጳጳስ ካርዲናል ጆርጅ ማሪዮ ቤርጎሊዮ ሲሆኑ የ77 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ናቸው። በአዲሱ ጴጥሮሳዊ አገልግሎታቸውም ፍራንቼስኮ /ፍራንሲስ/ የሚል ሥያሜን የወሰዱ ሲሆን ከ1300 ዓመታት ወዲህም ከአውሮጳ ውጪ የሆነ ር.ሊ.ጳ. ሲመረጥ እርሳቸው የመጀመሪያው ናቸው። እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከኢየሱሳውያን ማኅበር ለዚህ ኀላፊነት የተመረጡ የመጀመሪያ ር.ሊ.ጳ. ናቸው። ተጨማሪ የሕይወት ታሪካቸውን ይዘን በሌላ ዘገባ እንመለሳለን። እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያኑን አሁንም በመልካም እረኝነቱ ይጎብኝልን ስለ ሰጠንም እረኛ ይመስገን!

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።