ለር.ሊ.ጳ. ምርጫ ዝግጅት የመጀመሪያው የካርዲናሎች ጉባኤ ተካሄደ

conclaveከቤኔዲክቶስ 16ኛው የአገልግሎት ማቋረጥ በኋላ የመጀመርያው የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ሰኞ ጥዋት በካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ መሪነት በቫቲካን ከተማ በጳውሎስ 6ኛው አደራሽ ተካሄደ፡፡ ከሰዓት በኋላም በአስራ አንድ ሰዓት ሁለተኛው ጉባኤ እንደሚካሄድ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክቷል፡፡ ክቡር አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅድስት መንበር የዜናና የሕትመት ክፍል ኃላፊና የቫቲካን ሬዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ከአንደኛው ጉባኤ በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
እንደ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ መግለጫ ይህ ጉባኤ ር.ሊ.ጳ. ለመምረጥ ለሚካሄደው የዝግ ጉባኤ (ኮንክሌቭ) ማዘጋጃ ነው፣ በዚሁ ጉባኤ 142 ካርዲናሎች ተሳትፈዋል ከእነዚህም ውስጥ 103 ሊመርጡና ሊመረጡ የሚችሉ መሆናቸውንም አመልክተው ሌሎች 12 ሊመርጡና ሊመረጡ የሚችሉ ካርዲናሎች ማምሻውን እንደሚደርሱ አስገንዝበዋል፡፡
ዛሬ ጠዋት የተካሄደው ጉባኤ  መንፈስ ቅዱስ ሆይ ና በሚለው ጸሎት እንደተጀመረና ጉባኤውን የካርዲናሎች አፈ ጉባኤ እንደከፈቱት ሁሉም ካርዲናሎች በኅብረትና በተናጠል ቃላ መሃላ መፈጸማቸውን አመልክተዋል፣ በጉባኤው የተገኙ መንበረ ጴጥሮስ ክፍት ሆኖ በሚቀርበት ጊዜ ር.ሊ.ጳ እስከሚመረጡ ድረስ የመንበረ ሐዋርያው ቤት ተጠሪ ማለትም ካመርለንጎ ብፁዕ አቡነ ታርቺዝዮ በርቶነ የቤተ ጳጳሱ ሱባኤ ሰባኪ የነበሩ ጥቀ ክቡር አባ ራኒየሮ ካንታላሜሳ በማታው ክፍለጊዜ ጉባኤ የመጀመርያውን አስተንትኖ እንዲመሩ ባቀረቡት ኃሳብ ሁላቸው አባቶች ተስማመተዋል፣ ከዚህ በመቀጠል የካርዲናሎቹ ጉባኤ ለልሂቀ ር.ሊ.ጳ ቅዱስነታቸው የምስጋና መልእክት እንደሚጽፉላቸውም ተስማምተዋል፣
በዛሬው ጉባኤ ከተደረጉ ዋና ዋና መሰረታዊ ሃሳቦች አንዱ ለመንበረ ሐዋርያ ተጠሪ የሚረዱ ሶስት ካርዲናሎችን መርጠዋል፣ ለአቡናት ሥርዓት ብፁዕ ካርዲናል ሬ ለካህናት ሥር ዓት ብፁዕ ካርዲናል ሰፔ ለዲያቆና ሥርዓት ብፁዕ ካርዲናል ሮዴ ተመርጠዋል፣ እነኚሁ ሶስት ካርዲናሎች ከአሁን በኋላ በሚካሄዱት ልዩ ጉባኤዎች የመንበረ ሐዋርያ ተጠሪውን ይረዳሉ፡፡

ምንጭ፡- ቫቲካን ራድዮ

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።