ረዳኢተ ክርስትያን

Category: ዜናዎች Written by Super User Hits: 3103

የምሥራቅ አቢያተ ክርስትያናት ጥበቃ ቅዱስ ማኅበር ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ለዮናርዶ ሳንድሪ እዚህ በቫቲካን ባለፈው ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. የሳሌዚያን (ዶን ቦስኮ) ማኅበር ባከበረው ዓመታዊ የማርያም ረዳኢተ ክርስትያን በዓል ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ በመምራት ባሰሙት ስብከት፣ “ቅድስት ድንግል ማርያም ስለኛ በጌታ ፊት የምትማጠን የሁላችን ረዳት እናት ነች። የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ በሙላት የፈጸመው ልጅዋ ቅርብ በመሆን፣ የእርሱ ሙሉ ኃይል ወሮታ ሆኖልናል፣ ማርያም ስለኛ ኃጢአት ምሕረትን የምትማጠን የሐጥአን ጠበቃ ነች” ብለዋል።

“ሕይወታችን አለ መፍነስ ቅዱስ መሠረታዊ ትርጉሙን በማጣት በተስፋ መቁረጥ ሲሰቃይ ቅድስት ድንግል ማርያም ቅርብ በመሆን ትደግፈናለች፣ በሞት ላይ ድል የነሣው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን እንዳናይ የሚጋርደን ስለ ክርስቶስና ስለ እምነታችን በልባችን መጠራጠርና መደናገር እንዲኖር የሚያደርገው ውስጣዊውና ውጫዊው የጨለማው መንፈስ ሲከበንም ለኛ ቅርብ በመሆን እርሱ የሚላችሁ አድርጉ በማለት መግነዱን ትመራናለች” ብለዋል።

ስለ ሃይማኖት ስለ ቅዱስ መጽሐፍ ስለ ቤተ ክርስትያን ያለንን ያለ ማወቅ የክርስቶስ ቃልና በዚህች ምድር የርሱ ኅየንተ የሆኑት ር.ሊ.ጳ. ቃል ምንኛ አስፈላጊና አንገብጋቢ መሆኑ ያመለክተናል” ብለዋል። ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ አክለውም፣ “ይህ ቃል ለሁሉም እንዲዳረስ የእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን የመገናኛ ብዙኀንና ማተሚያ ቤቶች በዚህ በአሁኑ ወቅት እውነትን ለራስ ጥቅም በሚበጅ መንገድ እያማቱ ለሚያደርጉት የመቆጣጠር ሂደት ተገቢ ምላሽ የሚሰጡና የእንተ ላእለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን መሪ ትምህርትና ሥልጣናዊ ትምህርት በማስረዳት ጠበቃም በመሆኑ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው” እንዳሉም ሎሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰኘው የቅድስት መንበረ ዕለታዊ ጋዜጣ በትላንትናው ኅትመቱ አመልክቷል። በመጨረሻም “ብፁዕነታቸው በቅርቡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በቅድስት መሬት ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተትረፈረፈ ጸጋ ያስገኝ ዘንድ በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ጸሎታችንን እናቅርብ” እንዳሉም ለማወቅ ተችለዋል።