ምስጢረ ክህነትና ሢመተ ዲቁና በገዳመ ሲታውያን

ጥር 8 ቀን 2003 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሚገኘው በቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ሁለት የሲታውያን መነኮሳን፤ ማለትም ዲያቆን ሰሎሞን (ተሻለ) ንማኒ ምስጢረ ክህነትን እንዲሁም ወንድም ኃይለገብርኤል (ዓለማየሁ) ነጋሽ ሢመተ ዲቁናን በብፁዕ አባታችን አቡነ ልሳነ-ክርስቶስ ማቴዎስ እጅ ተቀበሉ፡፡

Priestly and Diaconate ordination- Cistercians Ethiopiaበዕለቱ ከጠዋቱ 1፡30 ላይ ብፁዕ አባታችንና ከሃያ አምስት የሚበልጡ ካህናት በታላቅ ሥነ ሥረዓት በመዘምራን ታጅበው ለሢመት በተዘጋጁት መነኮሳን ቤተሰቦችና በብዙ ምእመናን ወደሞላው ቤተክርስቲያን ከገቡ በኋላ መስዋዕተ ቅዳሴው ተጀመረ፡፡ ቅዳሴው በድምቀት እስከ ወንጌል ቀጥሎ ብፁዕ አባታችን ምስጢረ ክህነትንና ሢመተ ዲቁናን ከሰጡ በኋላ ባሰሙት ስብከተ ወንጌል እነዚህ የቤተ-ክርስቲያን ማዕረጋት ለምእመናን ያላቸውን የአገልግሎት ሚና በሰፊው በማስረዳት ለዚህ አገልግሎት የተመረጡ ሰዎች  የእረኝነት ተልእኮአቸውን ከመስዋዕትነቱ ጭምር በጥልቀት ተረድተው ወደ ኋላ ሳይሉ የክርስቶስ ምስክሮች መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ቀጥሎም ወጣቶች ለጥሪያቸው ተገቢ መልስ መስጠት እንዲችሉ የምእመናን ጸሎትና የወላጆች ክርስቲያናዊ ኩትኮታ ወሳኝ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።