ር.ሊ.ጳ. ቤኔዴክቶስ 16ኛው ለጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ህልፈት የኀዘን መግለጫ ላኩ።

pmMelespmMelesበዛሬው እለት ር.ሊ.ጳ. ቤኔዴክቶስ 16ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ብራሰልስ በሚገኝ ሆስፒታል ሲታከሙ ቆይተው ባለፈው ሰኞ ምሽት መሞትን በተመለከተ ለአገሪቱ ርእሰ ብሔር ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የኀዘን መግለጫ ላኩ። በቴሌግራም የተላከው መልእክትም የሚከተለው ነው።

ለየኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሳዊ ሪፐብሊክ ርእሰ ብሔር ክቡር ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፡-

የጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊን ያልተጠበቀ ሞት በመስማታቸው ቅዱስነታቸው ር.ሊ.ጳ. ቤኔዴክቶስ 16ኛው ለአቶ መለስ ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ልባዊ የኀዘን መግለጫቸውን ያስተላልፋሉ። የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ብዙ ዓመት መሪነታቸውን በማስታወስ ቅዱስ አባታችን ዘላለማዊ እረፍትን ያገኙ ዘንድ ይጸልዩላቸዋል። ለቤተሰቦቻቸውና እርሳቸውን በማጣታቸው ላዘኑት ሁሉ የሁሉን ቻይ አምላክ ቡራኬ መጽናናትንና ተስፋን ይሰጣቸው ዘንድ ጸልየዋል።

ብጹእ ካርዲናል ታርቺዚዮ ቤርቶኔ የአገረ ቫቲካን ጸሐፊ።

ምንጭ፡ http://www.news.va

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።