በሰባት ዓመቱ ሕፃን ጆሴፍ ራዚንገር /የአሁኑ ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው/ ለሕፃኑ ኢየሱስ የተጻፈ የገና ደብዳቤ

Category: ዜናዎች Written by Super User Hits: 1821

Popeበቅርቡ የተገኘው የሰባት ዓመቱ ሕፃን ጆሴፍ ራዚንገር  /የአሁኑ ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው/ ለሕፃኑ ኢየሱስ የተጻፈ የገና ደብዳቤ ለቅዱስ ልበ ኢየሱስ ያላቸውን መንፈሳዊነትና ካህን የመሆን ምኞታቸውን ያሳያል፤ እንዲህ ይነበባል፡-

“ውድ ሕፃኑ ኢየሱስ፣ ለሕፃናት ደስታን ታመጣለህና ፈጥነህ ወደ ምድር ና! ለእኔም ደስታን አምጣልኝ። የጸሎት መጽሐፍ፣ አረንጓዴ የቅዳሴ አልባስና የኢየሱስ ቅዱስ ልብን ስዕል ብታመጣልኝ ደስ ይለኛል፤ ጥሩ ልጅም እሆናለሁ።

ሰላም ሁን! ጆሴፍ ራዚንገር


ሕፃኑ ጆዜፍ አረንጓዴ የቅዳሴ አልባስ የጠየቁበትን ምክንያት ካህኑ ታላቅ ወንድማቸው ሞንሲኞር ጆርጅ ራዚንገር ሲያስረዱ ጆሴፍና ወንድሞቻቸው እንደ ካህን በመሆን “እቃቃ” ይጫወቱ እንደነበረና የልብስ ስፌት ባለሙያ የነበሩት እናታቸውም የካህናት ዓይነት ልብስ በመስፋት ይተባበሯቸው እንደነበረ ገልጸዋል።

በደብዳቤው ውስጥ የተጠቀሰው ሌላው ነገር ደግሞ የኢየሱስ ቅዱስ ልብ ሲሆን ይህም ስእሉን መጠየቁ መሆኑንና የመላ ቤተሰቡ ልዩ መንፈሳዊነት እንደሆነ ታውቋል።

ይህ ደብዳቤ ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው ሬገንስበርግ ውስጥ የዩኒቨርስቲ መምህር በነበሩበት ጊዜ ይኖሩበት የነበረ ቤት እድሳት ሲደረግለት ሲሆን በእህታቸው ዘንድ ቆይቶ ይፋ የሆነውም ከአንድ ሳምንት በፊት ታኅሣሥ 9 ቀን ነው። ራዚንገር ይኖሩበት የነበረው ቤት በርሳቸው ስም ትንሽ ሙዚየም የተደረገ ሲሆን የር.ሊ.ጳ. ጸሐፊ እንዳሉት ር.ሊ.ጳ. በደብዳቤው መገኘት ደስ የተሰኙ መሆናቸውና ይዘቱም እንዳስፈገጋቸው ተነግሯል።

ምንጭ፡- http://www.ucatholic.com