በሚሊየን የሚቆጠሩ ጽንስ የማስወረድ ሕጋዊነትን ተቃዋሚዎች በስፔን

Pro-life

Independent Catholic News - ቅዳሜ ጥቅምት 7 ቀን 2001 ዓ.ም. መንግሥት ጽንስ ማስወረድ የሚመለከተውን የስፔን ሕግ ለማሻሻል ያቀረበውን እቅድ በመቃወም ከአንድ ሚሊየን በላይ የሚሆን ሕዝብ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉ ተዘገበ።

እ.ኤ.አ. ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ እስካሁን በሥራ ላይ ባለው የስፔን ሕግ መሠረት ተገድዶ በመደፈርና አስጊ የሽል ሁኔታዎች ሲከሠቱ ብቻ ውርጃን የሚፈቅድ ሲሆን፤ አካላዊ ወይም ሥነ ልቦናዊ ጤንነትን የሚያሰጋ ሁኔታ ካለም ስፔናዊት ሴት ርግዝናዋን እንድታቋርጥ ይፈቅዳል። ይህ የሁለተኛውን አማራጭበሚመለከት በተግባር ላይ የዋለው ውርጃ ሲታይ ግን እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. ብቻ 112,000 ጽንስ ማጨናገፍ መከናውኑ ታውቋል።

 

 

የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዮዜ ሉይዝ ሮድሪጎ እንደ አዲስ መጨመር የፈለጉት ሕግ ማንኛዋም ሴት የርግዝናዋ 14ኛው ሳምንት ከመድረሱ በፊት ጽንስ ማስወረድን ከፈለገች ያሰበችውን ታደርግ ዘንድ የሚፈቅድ ነው። ይህ ረቂቀ ሕግ በሀገሪቱ የተወካዮች ምክር ቤት መሠረት የ16 እና የ17 ዓምት እድሜ ሴት ልጆች ወላጆቻቸውን ሳያሳውቁ ውርጃን ቢጠይቁ እንዲፈቀድላቸው ይጠይቃል።

መንግሥት ይህን በማድረጉ የውርጃ ሂደት ይበልጥ አስተማማኝ ይሆናል ሲል ከ22 ሳምንታት በኋላ ላለው ጽንስ ግን ውርጃ እንደማይፈቅድ ገልጿል። ሆኖም ግን በቅርብ ዓመታት ለአእምሮአዊ ጤና ስጋት በሚል ሰበብ በስፔን ውስጥ የ8 ወር ነፍሰ ጡር ለሆኑ ሴቶች ሁሉ ጽንስ ማጨናገፍ መደረጉ ይታወቃል። ስለዚህም ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ይህ አዲስ ሕግ ከተተገበረ የውርጃ ቁጥር እንደሚያሻቅብ አስታውቀዋል።

ሰላማዊ ሰልፉ ከ40 በላይ የሚሆኑ ሃይማኖታዊና የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖችን በአንድ ያካተተ ሲሆን መንግሥት የነደፈውን እቅድ እንዲሰርዝ ይጠይቃል። ይህም ሰልፍ ሁሉን የእድሜ ክልል ያካተተ ሲሆን ወላጆችና ልጆች፣ ካህናትና መነኮሳት፣ ስደተኛ ቤተሰቦችና ሌላ የተደራጁ ቡድኖች ከመላ አገሪቱ መሰባሰባቸው ታውቋል።

በመሀል ማድሪድ የተሰባሰቡት በሚሊየን የተቆጠሩት እነኚህ ተቃዋሚዎች የያዙት ግዙፍ የመፈክር ጨርቅ አጭር መልእክት “እያንዳንዱ ሕይወት ዋጋ አለው” የሚል ነው።

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።