ቱርክ ውስጥ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲይን ጳጳስ ተገደሉ።

bishop_pardovese_insideIndependent Catholic News -Thursday, June 3, 2010 - እስከንደሩን በምትባለው አንዲት የቱርክ ከተማ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ሉዪጂ ፓዶቨዜ (63 ዓመት ዕድሜ)  በትላንትናው ዕለት በስለት ተወግተው መገደላቸው ታወቀ። በሜዲትራንያን ወደብ አጠገብ በሚገኘው የበጋ መኖሪያ ቤታቸው ጓሮ ውስጥ በነበሩበት ወቅት ከአራት ዓመታት በላይ መኪና በማሽከርከር ያገለግላቸ በነበረው ሰው ጥቃቱ የተፈጸመባቸው መሆኑም ተገልጿል። የቱርክ ባለሥልጣናት ይህ ሁኔታ ጸረ ክርስቲያን ጥላቻዊ አቋምን ያለመ አይደለም ብለዋል። የቱርክ ፖሊስ ገዳዩን በእስር የያዙት ሲሆን ሰውየው ያልተረጋጋ አእምሮ ያለውና ከበድ ያለ ሥነ ልቦናዊ ችግር ውስጥ መሆኑን አሳውቀዋል።

ትውልደ ጣልያን የሆኑት አቡነ ፓዶቬዘ በአናቶሊያ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ እንደራሴና የቱርክ ጳጳሳት ጉባኤ ኀላፊ የነበሩ ሲሆን ከጥቃቱ በኋላ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል በመወሰድ ላይ ሳሉ ነበር ነፍሳቸው ያለፈችው። ር.ሊ.ጳ. በቆጵሮስ በሚያደርጉ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለአጃቢነት ወደዚያው ሊያመሩ በዝግጅት ላይ ነበሩ።

ይህ ግድያ ምንም እንኳ ሃይማኖታዊ ምክንያት የሌለው ቢመስልም በቱርክ ውስጥ በቅርብ ዓመታት በክርስቲያኖች ላይ የተወሰኑ ጥቃቶች ተሰንዝረዋል። እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. በአገሪቱ ምዕራብ በምትገኘው ኢዝሚር በምትባል ከተማ ልክ ቅዳሴ እንደጨረሱ አንድ የካቶሊክ ካህንን የ19 ዓመት ወጣት ወግቶ ያቆሰላቸው ሲሆን፤ በዚያኑ ዓመት በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ አሳታሚ ድርጅት ውስጥ የሚሠሩ ሦስት ክርስቲያኖች መገደላቸው ሲታወቅ በ2006 ዓ.ም. ደግሞ 16 ዓመት እድሜ ያለው ልጅ አባ አንድሬያ ሳንቶሮ የተባሉትን ካቶሊካዊ ካህን በጸሎት ላይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሳሉ ከጀርባ በኩል ተኩሶ እንደገደላቸውም የሚታወቅ ነው።

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።