ቤተ ክርስቲያን የዘር አድልዎ እና ፍትሕ አልባነትን ትቃወማለች

ቫቲካን ሬድዮ - በቅድስት መንበር በስደተኞች ጳጳሳዊ ምክር ቤት የተዘጋጀ ጂፕሲ በመባል የሚታወቁ የኤውሮጳ ዘላን ማኅበረ ሰብ ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮን የሚመለከት ዓውደ ጥናት በቫቲካን እየተካሄደ ነው፣ እስከ ነገ ሐሙስም ይቀጥላል። በዓውደ ጥናቱ በኤውሮጳ ጂፕሲዎችን የሚያገልግሉ የየአገሩ ዳይረክተሮችም ተሰብስበው እየተወያዩ ነው።

ጉባኤውን በቅዳሴ የከፈቱት በቅድስት መንበር የስደተኞች ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶንዮ ማሪያ ቨልዮ ሲሆኑ የምክር ቤቱ ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኣጎስቲኖ ማርከቶም ተገኝተዋል።

ብፁዕነታቸው በዓውደ በጉባኤው ባሰሙት ንግግር “ቤተ ክርስይትያን የሰው ልጅ ሕይወት ሰብአዊ እስከሚሆን ድረስ ፍትሕ አልባነት እና የዘር አድልዎን ለማውገዝ የተጠራች ናት። ቤተ ክርስትያን ለጥሪዋና ተልእኮዋ ታማኝ በመሆን ድሆችን በቅንነት ያገለገለች እንደሆነ የኅሊና መርመራ የምታደርግበትም ጊዜ ነው። አሳዛኙ የጂፕሲዎች ታሪክና ሕይወት በመነጠልና በስደት የተሞላ ነው። በዚህ ታሪክ ቤተ ክርስትያንም ቀጥተኛን ተዛዋሪ የሆኑ የራስዋ ጥፋቶች አልዋት፣ እነኚህ ጥቂትም ቢሆኑ ያደረጋቻቸውን ትላላቅ ነገሮች ሊያደፍርሱ ይችላሉ።" ካሉ በሁዋላ በዕርቅና በፍትሕ በመመራት ሮም እና ሲንት የሚባሉ ጂፕሲዎች በቤተ ክርስትያን ሕይወትና ሃብት ተሳታፊ እንዲሆኑ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። ቤተ ክርስትያንም በበኵልዋ በመሀከላቸው በመገኘት አገልግሎትዋና አጋርነትዋን እንድታበረክት አደራ ብለዋል።

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።