ቤተ ክርስቲያን ልጆችን የምታስተኛ ሞግዚት መሆን የለባትም!

ቤተ ክርስቲያን ልጆችን የምትወልድ እናት እንጂ የምታስተኛ ሞግዚት መሆን የለባትም!

Babysitterወንጌልን የማስፋፋት ኃላፊነት የካህናት ብቻ አይደለም ሲሉ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በረቡዕ ጠዋት ስብከታቸው ከመጋቢት ምርጫ ጀምሮ በሚኖሩበት ዶሙስ ሳንክቴ ማርቴ ተብሎ በሚጠራው የቫቲካን እንግዳ ማረፊያ ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ አሳሰቡ።

በዚሁ ቤተ ጸሎት በየእለቱ በሚያሳርጉት ቅዳሴ ላይ ቫቲካን ውስጥ የሚሠሩ የተለያዩ ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን በዚህኛው የረቡእ ቅዳሴ ላይ የተገኙት የቫቲካን ባንክ ሠራተኞች ነበሩ፤ ር.ሊ.ጳ. ለእነርሱ ባስተላለፉት መልእክት የእለቱን የሐዋርያት ሥራ ንባብ 8፡1-8 ያለውን ጠቅሰው የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ብርቱ ስደቶችን ሲሸሹ የእግዚአብሔርን ቃል በየሄዱበት ይሰብኩ እንደነበር አስታውሰዋል። "ከተጠመቁ ገና አንድ ዓመት ወይም ትንሽ በለጥ ያለ ጊዜ ብቻ የነበራቸው ተራ አማኞች የነበሩ ቢሆንም እየሄዱ ቃሉን ለማወጅ ብርታት ነበራቸው፣ ይታመኑና ተአምራትንም ያደርጉ ነበር" ብለዋል።

በማያያዝም ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ሚሽነሪዎች በ17ኛው ክ.ዘ. ከተባረሩበት ጊዜ ጀምሮ ለ200 ዓመታት ያለካህናት ያሳለፉትን የጃፓናውያን ካቶሊኮች ታሪክ አውስተው በኋላ ሚሽነሪዎች ተፈቅዶላቸው ወደ ጃፓን ሲመለሱ በዚያ የነበሩት ካቶሊኮች በሥርዓቱ የተጠመቁ፣ ትምህርተ ክርስቶስ የተከታተሉና በቤተ ክርስቲያን ፊት የተጋቡ ሆነው መገኘታቸውን ተናግረዋል።

ር.ሊ.ጳ. ዛሬ በምስጢረ ጥምቀት ኃይል ይህን መሰል እምነት ምእመናኖች ያላቸው እንደሆን ጠይቀዋል። የተጠመቅን ሁላችን "ኢየሱስን በሕይወታችን፣ በምስክርነታችንና በቃላችን" ማወጅ እንዳለብን አሳስበዋል። "ይህንንም ስናደርግ ቤተ ክርስቲያን ልጆችን የምትወልድ እናት ትሆናለች፤ በአንጻሩም ይህን ካላደረግን ቤተ ክርስቲያን ልጅን የምትወልድ እናት ሳይሆን ልጆችን ለማስተኛት የምትጠብቅ ሞግዚት ትሆናለች!" በማለት ስብከታቸውን አጠቃለዋል።

ምንጭ፡- http://www.catholicherald.co.uk

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።