በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ የመነኮሳውያት ቁጥር ዕድገት ሕንድ ትመራለች

Mother_Theresa_sisters'_novicesIndependent Catholic News - በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመነኮሳውያት (የእማሆዮች) የቅርብ ዓመታት ቁጥራዊ ዕድገት ሕንድ ግንባር ቀደሙን ቦታ መያዟ ተገለጠ።

የ"Catholic Culture" ድረ ገጽ ባደረገው አኀዛዊ ዳሰሳ መግለጫ መሠረት ባጠቃላይ ሲታይ እስያና አፍሪካ እ.ኤ.አ. ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ ጥሩ የመነኮሳውያት ቁጥር መጨመር ሲታይ፤ በአውሮፓ፣ አሜሪካና ኦሺኒያ የቁጥር ማቆልቆሉ ታውቋል።

እ.ኤ.አ. ከ2002-2007 ዓ.ም. በእስያ ውስጥ ሕንድ የ9,838 ፣ ቬትናም የ2,545 እንዲሁም ፊሊፒንስና ደቡብ ኮሪያ እያንዳንዳቸው የ500 መነኮሳውያት ቁጥር ዕድገት አሳይተዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የመነኮሳውያት ቁጥር ዕድገት ካሳዩት ማኅበራት ውስጥ ሦስት በከራላ (ሕንድ) ውስጥ የተመሠረቱና የብፅዕት እማሆይ የፍቅር ልኡካን እህቶች ላቅ ያለውን ስፍራ ይይዛሉ።

የፍራንቸስካውያት ቅድስት ኪያራ፣ የማርያም ደብረ ቀርሜሎስና የቅዱስ ቁርባን ስግደት መነኮሳይት ማኅበራት በቀጣይነት አባላትን በማግኘት ላይ ናቸው።
ዓለም አቀፍ የመነኮሳውያት ቁጥር ማሽቆልቆል ከሚታይባቸው ማኅበራት መካከል ደግሞ...
የሳሌዝያን እህቶች፣ የእመቤታችን ፍራንቸስካውያት ልኡካት እህቶች፣ የቤኔዲክቲን (የቅ.አቡነ ቡሩካውያት) ማኅበራት ይገኙበታል።
በአፍሪካ ታንዛንያና ኮንጎ እያንዳንዳቸው የ1,500፣ ናይጄሪያ፣ ማዳጋስካር፣ ኬንያና አንጎላ ደግሞ ከ500-800 የሚደርስ የመኮሳውያት ቁጥር ዕድገት አሳይተዋል። በመካከለኛው ምሥራቅና ካሪቢያን አገራትም ባጠቃላይ የቁጥር ዕድገት መመዝገቡም ተገልጿል።

ይህም ቢሆን ግን ቅሉ በጥናታዊው ዳሰሳ መሠረት በመላው ዓለም ያለውን የመነኮስውያት ብዛት እ.ኤ.አ. ከ2002-2007 ዓ.ም.በ4.6 በመቶ መቀነስ ሊያስቀረው አልቻለም።

በምዕራቡ ዓለም ግን በጣም ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ቁጥሩ ቀንሷል። ከላይ በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ በጣልያን የ11,156 መነኮሳውያት ቁጥር ሲቀንስ በተመሳሳይ ጊዜም ሰሜን አሜሪካ የ10,454 መነኮሳውያት ቅነሳ ታይቷል።

ጀርመንና ፈረንሣይ ወደ 6000 የሚጠጉ፣ ካናዳና ስፔን እያንዳንዳቸው የ4000 መነኮሳውያት ቁጥር ማሽቆልቆል አስመዝግበዋል። በተጨማሪም ከአውሮፓ አየርላንድ፣ ቤልጅምና ኔዘርላንድስ ከላቲን አሜሪካ ደግሞ አርጀንቲና፣ ብራዚልና ኮሎምቢያ በመቶ የሚቆጠር ቅነሳ ተስተውሏል።
እ.ኤ.አ. ከ1965-1995 ዓ.ም. ባሉት ዓመታት በአሜሪካ 49 በመቶ፣ በካናዳ 46 በመቶ፣ በፈረንሣይ 44 በመቶ፣ በጀርመን 48 በመቶ፣ በእንግሊዝ 43 በመቶ እንዲሁም በኔዘርላንድስ 51 በመቶ መቀነሱ ታውቋል።
በመላው ዓለም ባጠቃላይ 750,000 መነኮሳውያት ያሉ መሆኑም ተመዝግቧል።

 

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።