Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 96

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 99

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$category_alias in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 102

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 141

ልደተ ክርስቶስ ታኅሣሥ  2002 ዓ.ም.

የክርስቶስ ልደት የኛ /የሰውልጆች/ ልደት ነው፡፡

ቃል በመጀመሪያ ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ይህም ቃል እግዚአብሔር ነበረ፡፡ (ዮሐ.1:1)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ፍጹም አምላክ ማለት ደግሞ ስለ እግዚአብሔርነቱ ምንም የማይጎደለው ማለት ነው፡፡

የእግዚአብሔር ሰው ሆኖ መወለድ ፍጹም ስጦታ ነው፤እግዚአብሔር በእግዚአብሔርነቱ ራሱን ሙሉ…

Read more: የክርስቶስ ልደት የኛ ልደት ነው፡፡

Comments ()
ቫቲካን ሬድዮ - (03-01-2010) - ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ምእመናንና ነጋድያን የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ “የሰው ልጅ ታሪክ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ጥበብ ስለሚመራ ትርጉም አለው” በማለት ታሪካችን አቅጣጫና ዓላማ ያለው እንጂ በዘፈቀደ የሚሄድና በጥንቈላዊና በምጣኔ ሃብታዊ ትንቢቶች የሚወሰን አለመሆኑን አብራርተው የመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎትን አሳረገዋል።

ትምህርታቸውም እንደሚከተለው ነው፣ ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፦...…

Read more: ተስፋችን እግዚአብሔር ነው

Comments ()

ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትናንትና በቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በየዓመቱ ለነዳያን በሚያዘጋጁት የምሳ ግብዣ ላይ ከ2000 ድኆች ጋር ምሳ በልተዋል። ተጋባዦቹ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት የመጡ ስደተኞችና ምንም የሌላቸው የሮማ ድኆች ናቸው። ቅዱነታቸው እቦታው በደረሱበት ጊዜ የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር የማኅበሩ መሥራች ፕሮፈሰር ኣንድረያ ሪካርዲ የማኅበሩ ሊቀ መንበር ማርኮ ኢምፓጝልያዞ ከአንድ ሮም ሴትና የሰነጋል ስደተኛ ወጣትና የተርኒ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓጝልያ እና ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ሞረቲ ከድኆቹ አብረው ተቀብለዋቸዋል፣

ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ በእንኳን ደህና መጡ ንግግራቸው፣ “ብፁዕ አባታችን ይህንን ቦታ እንደቤታቸው ከሚቈጥሩት የዚህ ልዩ ኅብረተሰብ ጓደኛ በመሆን ከእኛ አብረው ሲበሉ፣ እርስዎን በቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር ማእድ ከእኛ ጋር ማየት ትልቅ ደስታ ይሰማናል”፣ ሲሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጠው በቦታው በየቀኑ ከአንድ ሺ በላይ እንደሚመገቡ፣ ሰዎቹም በተለያዩ ችግሮች የተጠቁ መሆንቸውን አልደበቁም፣ እንደ ቤተሰብ ሆነው መግብ ብቻ ሳይሆን በፍቅርና በጓደኝነት እንደሚኖሩም ኣብራርተዋል። የድኆች ጓደኛና አለኝታ መሆን ክርስትያንን ያሳድጋል በማለት ትልቁ ጎርጎርዮስ ድኆችን በማገልግል ኃይልና ብርታት እንደሚገኝ ያስተማረውን አስታውሰዋል።

ቅዱስነታቸው ከተለያዩ ኣገሮች ከመጡ ስደተኞች በተለይም በማኅበሩ ብተደራጀ የጣልያነኛ ቋንቋ ትምህርት የሚከታተሉትን ትንሽ ቡድን ሲያነጋገሩ፣ “ቋንቋ በአንድነት ለመኖርና አንድ ቤተ ሰብ ለመሆን የመዋሃሃድ ቍልፍ ነው፣ በቋንቋ ባህልና የባህል ታሪክ እንዲሁም የባህሉ ዕጣ ፈንታ ተደብቆ ይገኛል፣ ይህንን የቋንቋ ትምህርት ዕድል ላበረከተላችሁ የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር አመሰግናለሁ”፣ ሲሉ የተሰጣቸውን ዕድል እንዲጠቀሙበት አደራ ብለው፣ ካበረታቱ በኋላ ማኅበሩ የሠራውን የቤተ ሰቡ የልደት የቤተ ልሔም ግርግም አይተው ምሳ በልተዋል። በምሳ ጊዜ ከቅዱስነታቸው የተለያየ ችግር ያላቸውና ከተለያዩ ወገኖች የመጡ 12 ሰዎች በአንድ ጠረጲዛ ተመግበዋል።

ቅዱስነታቸው እንደ ኢየሱስ ልዩ ጓደኞች የጠርዋቸው የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበረሰብ አብረው በመመገባቸው የተሰማቸውን ደስታና እርካታ ገልጠዋል። ግብረ ሠናዩንም እንዲህ ሲሉ አመጕሰውታል፣ “ኢየሱስን በሚከተሉ የዘመናችን ሓዋርያት በሚደረግ ግብረ ሠናይ እግዚአብሔር በመጀመርያ እንደወደደንና ገናም እንደሚወደን የሚያሳይ እውነት ግልጽ ይሆናል፣ ለዚህም መልስ የምንሰጠው በፍቅር ነው፣ ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ይህንን ምግባረ ሠናይ ለማን መሆኑን ለመግለጽ ደግሞ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል። እነዚህን ቃላት ስንሰማ ኢየሱን ከሚያመለክቱ ከተቸግሩት ጋር አጋርነት እንድናሳይ አይቀሰቅስምን፣ ጓደኝነትና ኣጋርነት ብቻ ሳይሆን ቤተ ሰብ መሆናችንስ አይሰማንምን” ብለዋል።

ስደትና ችግርን አስመልክተውም፣ የኢየሱስ ቤተሰብም ችግር አጋጥሞታል፣ ገና ቤተሰብ ለመመሥረት ሲጀምሩ በቤተልሔም የሚቀበላቸው አጥተዋል፣ ወደ ግብጽ እንዲሰደዱ ተገደዋል፣ እናንተ የስደትን ችግር ጥሩ ኣርጋችሁ ታውቃላችሁ፣ በችግርና በመከራ ብትገኙም እዚህ እናንተን ለማንከባከብና ለማገልገል የተዘጋጁ የእግዚአብሔር ፍቅር ምልክት የቅዱስ ኤጅድዮ ማኅበር አለላችሁ፣ ዛሬ እዚህ በየቤታችሁ ልታገኙት የምትችሉትን ታገኛላችሁ። ይህ የእውነተኛ ቤተ ሰብ ቤት ነው፣ በቤተሰብ እኔ የሚለው በእኛ ይተካል፣ ማኅበር ይቆማል፣ የፍቅር ማኅበር ስለሆነም እግዚአብሔር ማሃከላችን ይገኛል።

ኢየሱስ የሚሰቃዩትንና ችግር ያላቸውን ሰዎች የሱ ጓደኞች እንደሚያደጋቸውና እንደሚወዳቸው በመረዳት እሱን በመከተል ለሁሉም በተለይም ለተጐዱትና ረዳት ለሌላቸው ለመርዳት ዝግጁነታችን ማረጋገጥ እንድለብን አሳስበዋል፣ “ማንም ሰው ብቻው እንዳይሆን፣ ማንም ሰው እንዳይነጠል፣ ማንም ሰው ተጥሎ እንዳይቀር” ሲሉም አደራ በልዋል።

ቫቲካን ራድዮ - ቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር የልደት በዓልን ምክንያት የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር በየዓመቱ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በየዓመቱ ለነዳያን በሚያዘጋጀው የምሳ ግብዣ ላይ በመገኘት ቅዱስ አባታችን .ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትላንትና ከ2000 ነዳያን ጋር ምሳ በልተዋል። ተጋባዦቹ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት የመጡ ስደተኞችና ምንም የሌላቸው በሮማ የሚኖሩ ነዳያን ናቸው። ቅዱነታቸው በስፍራው በደረሱበት ጊዜ የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር መሥራች ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ፣ የማኅበሩ ሊቀ መንበር ማርኮ ኢምፓግልያዞ፣ የሰኔጋል ስደተኛ ወጣትና የተርኒ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓግልያ እና ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ሞረቲ ከተቀሩት ነዳያን ጋር በመሆን አብረው ተቀብለዋቸዋል፣

ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ በእንኳን ደህና መጡ ንግግራቸው፣ “ብፁዕ አባታችን ይህንን ቦታ እንደቤትዎ በመቁጠርና የዚህ ልዩ ኅብረተሰብ ጓደኛ በመሆን ከእኛ ጋር አብረው በመሳተፍዎና እርስዎን በቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበር ማእድ ከእኛ ጋር በማየታችን ትልቅ ደስታ ይሰማናል”፣ ሲሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጠው በቦታው በየቀኑ ከአንድ ሺ በላይ ነዳያን እንደሚመገቡ፣ ሰዎቹም በተለያዩ ችግሮች የተጠቁ መሆንቸውን ገልጠው፣ እንደ ቤተሰብ ሆነው መመገብ ብቻ ሳይሆን በፍቅርና በጓደኝነት እንደሚኖሩም ኣብራርተዋል። የድኆች ጓደኛና አለኝታ መሆን ክርስትያንን ያሳድጋል በማለት ትልቁ ጎርጎርዮስ ነዳያንን በማገልግል ኃይልና ብርታት እንደሚገኝ ያስተማረውንም አስታውሰዋል።

ቅዱስነታቸው ከተለያዩ ኣገሮች ከመጡ ስደተኞች በተለይም በማኅበሩ በተደራጀ...…

Read more: ማንም ሰው ብቻውን እንዳይሆን፤ ማንም ሰው እንዳይነጠል፤ ማንም ሰው ተጥሎ እንዳይቀር

Comments ()

Independent Catholic News - በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመነኮሳውያት (የእማሆዮች) የቅርብ ዓመታት ቁጥራዊ ዕድገት ሕንድ ግንባር ቀደሙን ቦታ መያዟ ተገለጠ።

የ"Catholic Culture" ድረ ገጽ ባደረገው አኀዛዊ ዳሰሳ መግለጫ መሠረት ባጠቃላይ ሲታይ እስያና አፍሪካ እ.ኤ.አ. ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ ጥሩ የመነኮሳውያት ቁጥር መጨመር ሲታይ፤ በአውሮፓ፣ አሜሪካና ኦሺኒያ የቁጥር ማቆልቆሉ ታውቋል።

እ.ኤ.አ. ከ2002-2007 ዓ.ም. በእስያ ውስጥ ሕንድ የ9,838 ፣ ቬትናም የ2,545 እንዲሁም ፊሊፒንስና ደቡብ ኮሪያ እያንዳንዳቸው የ500 መነኮሳውያት ቁጥር ዕድገት አሳይተዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የመነኮሳውያት ቁጥር ዕድገት ካሳዩት ማኅበራት ውስጥ ሦስት በከራላ (ሕንድ) ውስጥ የተመሠረቱና የብፅዕት እማሆይ የፍቅር ልኡካን እህቶች ላቅ ያለውን ስፍራ ይይዛሉ።

የፍራንቸስካውያት ቅድስት ኪያራ፣ የማርያም ደብረ ቀርሜሎስና የቅዱስ ቁርባን ስግደት መነኮሳይት ማኅበራት በቀጣይነት አባላትን በማግኘት ላይ ናቸው።
ዓለም አቀፍ የመነኮሳውያት ቁጥር ማሽቆልቆል ከሚታይባቸው ማኅበራት መካከል ደግሞ...…

Read more: በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ የመነኮሳውያት ቁጥር ዕድገት ሕንድ ትመራለች

Comments ()

ቫቲካን ሬድዮ - በኢራቅ የአናሳ ሃይማኖቶች ህልውና ላደጋ በመጋለጡ ምክንያት ዐቢይ የደኅንነት ጥበቃ እንደሚያስፈልገው የነዚህ አናሳ ሃይማኖቶች ተጠሪዎች የጸጥታ እና የደኅንነት ጥበቃን ጥሪ በማቅረብ በተለይ ደግሞ እ.ኤ.አ. ጥር ወር 2010 ዓ.ም. በአገሪቱ በሚካሄደው ሕዝባዊ መርጫ ወቅት ተገቢ የጸጥታ እና የደኅንነት ዋስትና ያገኙ ዘንድ ለአገሪቱ መንግሥት ጥሪ አስተላልፈዋል።

በኢራቅ አናሳ ሃይማኖቶች ለተለያዩ አደጋዎች በመጋለጣቸው ምክንያት መፍትሔው ራስን ለማዳን አገር ጥሎ መሰደድ ብቻ በመሆኑ የተያያዙት ስደት እንዲወገድ ከመንግሥት የጸጥታ እና የደህንነት ዋስትና መረጋገጥ ይኖርበታል። በኢራቅ አናሳ ከሚባሉት ሃይማኖቶች ውስጥ የእስልምና እና የክርስትናን አንዳንድ የእምነት ሥርዓቶችና ትምህርተ ሃይማኖትን በአንድ በማቀላቀል የሚያስተምር 300 ሺሕ ኢራቃውያን የሚከተሉት የሻባክ ሃይማኖት አንዱ ሲሆን፣ ሌላው የያዚዲ ሃይማኖት፣ የከለዳያን ሥርዓት የምትከተል ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን፣ የኦርቶዶስክ፣ የአሲሪያ፣ የአርመን፣ የአንግሊካን አቢያተ ክርስትያን የሚመለከት ጉዳይ ሲሆን፣ በኢራቅ በመንግሥት ደረጃ ሳይሆን በአቋም ስነ ሓሳብ የተደገፈ ጸረ የአናሳ ሃይማኖት ተግባር እየተስፋፋ መሆኑ ይነገራል።

Read more: በኢራቅ የአናሳ ሃይማኖቶች ህልውና

Comments ()

Independent Catholic News - ቅዳሜ ጥቅምት 7 ቀን 2001 ዓ.ም. መንግሥት ጽንስ ማስወረድ የሚመለከተውን የስፔን ሕግ ለማሻሻል ያቀረበውን እቅድ በመቃወም ከአንድ ሚሊየን በላይ የሚሆን ሕዝብ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉ ተዘገበ።

እ.ኤ.አ. ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ እስካሁን በሥራ ላይ ባለው የስፔን ሕግ መሠረት ተገድዶ በመደፈርና አስጊ የሽል ሁኔታዎች ሲከሠቱ ብቻ ውርጃን የሚፈቅድ ሲሆን፤ አካላዊ ወይም ሥነ ልቦናዊ ጤንነትን የሚያሰጋ ሁኔታ ካለም ስፔናዊት ሴት ርግዝናዋን እንድታቋርጥ ይፈቅዳል። ይህ የሁለተኛውን አማራጭበሚመለከት በተግባር ላይ የዋለው ውርጃ ሲታይ ግን እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. ብቻ 112,000 ጽንስ ማጨናገፍ መከናውኑ ታውቋል።

Read more: በሚሊየን የሚቆጠሩ ጽንስ የማስወረድ ሕጋዊነትን ተቃዋሚዎች በስፔን

Comments ()

ራድዮ ቫቲካን - ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሑድ ከሐዋርያዊ አዳራሽ መስኮት በመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  ከተሰበሰቡት በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩት ምእመናን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመድገማቸው በፊት ዕለቱ የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ቀን የሚዘከርበት እሁድ መሆኑን አስታውሰው፣ ቤተ ክርስትያን ለመላው ሰው ዘር ወንጌልን መስበክ እንደሚጠበቅባትና ቤተ ክርስትያን የምትኖረው የወንጌል የተስፋ መልእክትን ለማስተላለፈ መሆኑን አሳስበዋል። በቅርቡ በብራዚል የተገደሉት ልኡከ ወንጌል ኣባ ሩቮለቶ እና በፊሊፒንስ የታገቱት አባ ሲኖት በማስታወስም በጸሎት እና በመንፈስ እንደሚዘክሩዋቸው አረጋገጠዋል።

Read more: ቤተ ክርስትያን የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ቀንን አስታውሳ ዋለች

Comments ()
ቫቲካን ሬድዮቅ. አ. ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ  በቫቲካን በመካሄድ ላይ ባለው ሁለተኛው ይፋዊ የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ በእንግድነት በመሳተፍ ላይ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ለየት ባለ መልክ ሰላምታ ሲያቀርቡ፣ “በዚህ የአፍሪቃው ሁለተኛ በእንግድነት እንዲሳተፉ ያቀረብኩሉዎትን ጥሪ ተቀብለው አወንታዊ ምላሽ ሰጥተው እዚህ በመገኘትዎት በእኔ እና በሁለተኛው የአፍሪቅ ብፁዓን ጳጳሳት አበው ስም ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርብልዎታለሁ። የእርስዎ እዚህ መገኘትም የአፍሪቃ ጥንታዊት እና በባህል ሃብታም ለሆነቸው ቤተ ክርስትያን አንደበተ ርቱዕ እና ስሜት የሚነካ ሕያው ምስክርነት ነው። በግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ 8 ከቁጥር 26 እስከ 40 እንደምናነበው በሐዋርያት ጊዜ የክርስቶስ የድህነት መልእክት ቀርበው ከሐዋርያት አንደበት ያዳምጡ ከነበሩት አሕዛብ ውስጥ ከኢትዮጵያ የመጡ ጭምር ይገኙባቸው እንደነበርም እንረዳለን፣ የዚህ ሕዝብ ለወንጌል ያለው ታማኝነት አሁንም ቀጣይ ሆኖ ለእግዚአብሔር የፍቅር ትእዛዝ ታዛዥ መሆኑ እና እርስዎም ቀድመው እንዳሉት ይኽ ሕዝብ ስደትና መከራን ተሻግሮ ስለ ክርስቶስ ሰማዕትነትንም በመቀበል እምነቱን በመመስከር እምነቱን ጠብቆ ይኖራል”።...…

Read more: ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያቀረቡት ሰላምታ

Comments ()
ቫቲካን ሬድዮ- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ በእንግድነት ተገኝተው ንግግር ማሰማታቸው ከሲኖዶስ አዳራሽ የተላለፈልን ዜና ገለጸ።
የፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ንግግር:- "በስም አብ ወወልድ ወንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፣...…

Read more: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ ያሰሙት ንግግር

Comments ()

ቫቲካን ሬድዮ - ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ.ቤኔዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ረፋድ እንደወትሮኣቸው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሱት በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ምእመናንና ነጋድያን (መንፈሳዊ ተጓዦች) የተለመደውን ሳምንታዊ የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ኣቅርበዋል። 

ጉባኤውን በጸሎት ከከፈቱ በኋላ የሚከተለው ቃለ እግዚአብሔር ከመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አንድ ተነበበ።

1 በክፉ ሰዎች ምክር የማይሄድ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ የማይቆም፥ በፌዘኞች ወንበር የማይቀመጥ የተባረከ ነው። 2 እንዲህ ያለ ሰው፣ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም ቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል። 3 ስለዚህም እርሱ፣ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ በፈሳሽ ውኃ ዳር እንደ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሥራ ሁሉ ይሳካለታል። 4 ክፉዎች ግን እንዲዚህ አይደሉም፥ እነርሱ ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው። 5 ስለዚህ ክፉ ሰዎች፣ በፍርድ ቀን ጸንተው አይቆሙም፥ ኃጢአተኞችም በጻድቃን መካከል አይገኙም። 6 ምክንያቱም እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች። 

በመቀጠልም ቅዱስነታቸው በዛሬ ትምህርታቸው ከነገ ወዲያ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 9 ቀን 2009 ዓ.ም. የሚታወሰው ቅዱስ ዮሓንስ ሌዮናርዲ ከሞተ አራት መቶ ዓመት መሙላቱን በማስታወስ በርሱ ሕይወት ዙሪያ አስተምህሮ አደረጉ። ከዚህ በታች በተለያዩ ቋንቋዎች ካቀረቧቸው ትምህሮቶች ለእንግሊዘኛ ተናገሪዎች የሰጡትን ትምህርት እናቀርብላችኋለን።…

Read more: የሰው ልጅ ሁሉ መመዘኛ ክርስቶስ ነው

Comments ()

ቫቲካን ሬድዮ - የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ የሚከናወነው ዕርቅ ፍትሕና ሰላም በሚመለከቱ የአህጉሩ ጉዳዮች ላይ በማትኮር ሲሆን፣ ቅድመ ዝግጅቱ ኣልቆ ትናንት እሁድ ጥዋት በሮም ሰዓት አቆጣጠር ልክ ዘጠኝ ሰዓት ተኵል ቅ.ኣ.ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ባሳረጉትና በመሩት ደማቅ የመሥዋዕተ ቅዳሴ ሥርዓት በይፋ ተጀመረ።

ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ ከበጋው ዕረፍት ካስተንጋደልፎ ሓዋርያዊ አደራሻቸው ወደ ቫቲካን የተመለሱት ባለፈው ቅዳሜ ጥዋት ሲሆን፣ የቫቲካን ረድዮና ተለቪዥን የአፍሪቃ ጳጳሳት ልዩ ሁለተኛ ሲኖዶስ መክፈቻ ቅዳሴ ሥርዓት ከቦታው በቀጥታ ለዓለም ሕዝብ አስተላልፈዋል።

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሁድ የልዩ ሁለተኛ አፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ጉባኤ በይፋ ለመክፈት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሰሙት ስብከት እንደሚከተለው ነው።…

Read more: የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ተጀመረ

Comments ()
ራድዮ ቫቲካን - ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ በቼክ ሪፐብሊክ አገር አቀፍ አሥራ ሦስተኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ከትናንትና በስቲያ ወደ ካስተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ መንበራቸው መመለስቻው ታውቋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ ከቼክ ሪፐብሊክ ርእሰ ከተማ ፕራግ አውሮፕላን ማረፍያ ሲነሡ አሸናኘት ላደረጉላቸው የቼክ ሪፐብሊክ የሃይማኖት እና የመንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ ከአውሮፕላን ማረፍያ ሲነሡ መለኮታዊ ቁንጅና ለዓለም እንዲያንጸባርቅ ለእውነት ክፍት ትሆኑ ዘንድ እመኛለሁ ብለዋል ።
ቼክ ሪፐብሊክ የተባረከች ሃገር ናት ምክንያቱም አንጋፋዎች ሚስዮናውያን እና ሰማዕታትን ያበቀለች ቅድስት የክርስትያን እሴቶች አቀፍ ሀገር ናት ሲሉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ ቼክ ሪፐብሊክን አወድሰዋል።
ቼክ ሪፐብሊክ በኮሚኒስት አገዛዝ ሥር በነበረችበት ወቅት የተገደለችው ቅድስት አኘሰ ዘቦኤሚያ እና በስታራ ቦስላቭ ሰማዕት የሆነውን ቅዱስ ቬንሰስላው አስታውሰዋል።…

Read more: ለእውነት ክፍት መሆን ይገባል

Comments ()

Subcategories

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።