Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 96

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 99

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$category_alias in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 102

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 141

VATICAN CITY, SEPT. 22, 2009 (Zenit.org).-ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ባለፈው ቅዳሜ ብራዚል ውስጥ በተገደሉት ጣልያናዊ ሚስዮናዊ አባ ሩጄሮ ሩቮሌቶ ሞት ምክንያት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ። ለማናዎስ ሊቀ ጳጳሳት ሉይስ ሶዋሬስ በላኩት የቴሌግራም ኀዘን መግለጫቸው ውስጥ ይህን "ሰላማዊ የወንጌል አገልጋይ ላይ ደስ የማይልና የጭካኔ ድርጊት" በጥብቅ በማውገዝ በጸሎት መንፈሳዊ አብሮነታቸውን ገልጸዋል።…

Read more: ር.ሊ.ጳ. በሚስዮናዊው መገደል የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ

Comments ()

Independent Catholic News - ኢየሱስ መንገድን ሊያሳየን ያውም ወደ ሕይወት የሚያደርሰን መንገድን እንጂ ፍልስፍና ሊያስተምረን አልመጣም፤ ይህ መንገድ የእውነተኛ እምነት መገለጫ የሆነው ፍቅር ነው" በማለት ነበር ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ከካስተልጋንዶልፎ ባለፈው እሑድ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አስተምህሯቸው መጀመሪያ ላይ የዕለቱን ወንጌል መልእክት ማካፈል የጀመሩት።

በመቀጠልም "የእግዚአብሔር ቃል ሁለት ወሳኝ ጥያቄዎችን ያቀርብልናል፦ የናዝሬቱ ኢየሱስ ላንተ ማነው? የሚልና እምነትህ ተግባራዊ ሆኗል ወይስ አልሆነም? የሚለው ናቸው።" ካሉ በኋላ ር.ሊ.ጳ.…

Read more: የናዝሬቱ ኢየሱስ ላንተ ማነው?

Comments ()

ቫቲካን ሬድዮ - ባለፈው ዓርብ በፓኪስታን ፑንጃብ መንደር ሙስሊሞች የዓርብ ጸሎት አድርሰው በመመለስ ላይ እያሉ በማበር ባንድ ክርስትያን ምእመን እና ባንዲት ሙስሊም መካከል የተፈጠረው ወዳጅነት እና ፍቅር በመቃወም በክልሉ አቅራቢያ የሚገኘውን ቤተ ክርስትያን በእሳት ማጋየታቸው ሲገለጥ፣ በዚህች አገር አክራሪያን ሙስሊሞች በተከታታይ የሚፈጽሙት ጸረ ክርስትያን አመጽ ገና እንዳልተገታ ለማወቅ ተችሏል።

በመቀጠልም አክራሪያኑ...…

Read more: ጸረ ክርስትያን አመጽ በፓኪስታን

Comments ()

CASTEL GANDOLFO, Italy, AUG. 30, 2009 (Zenit.org) - ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው የተለመደውን የሰንበት እኩለ ቀን መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ሲያደርሱ ባለፈው ኀሙስ የተከበረችውን የቅዱስ አውጎስጢኖስ እናትን ማለትም የቅድስት ሞኒካን አብነታዊ ሕይወት በመንተራስ አስተምህሯቸውን አድርገዋል። ይህች ቅድስት የክርስቲያን ወላጆች ባልደረባ እንደመሆኗ መጠን ልጆች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማግኘት በሚያደርጉ ጥረት የክርስቲያን ወላጆች ለሚጫወቱት ሚና አመስግነዋል።…

Read more: ልጇን ሁለት ጊዜ የወለደች እናት - ቅድስት ሞኒካ

Comments ()

(Independent Catholic News) - ከሰሜን አፍሪካ ባህር አቋርጠው ወደ አውሮጳ የሚመጡ ስደተኞችን በመታደግ የጣልያን መንግሥት የጤና እገዛና ድጋፍ ያደርግ ዘንድ ቫቲካን አሳሰበች። ይህን መልእክት ያስተላለፈችው ከሊቢያ ተነሥተው ባህር ሲያቋርጡ የነበሩ ከሰባ በላይ ኤርትራውያን ስደተኞች ለሦስት ሳምንታት ከተጎሳቀሉ በኋላ  በረሃብና ጥም መሞታቸው ከታወቀ በኋላ ነው። ላምፔዱዛ ከሚባል ሲሺሊያ አጠገብ ከሚገኝ ደሴት ከዚሁ ጀልባ የተረፉትን አምስት ስደተኞች የጣልያን ፖሊስ ማዳኑ ተዘግቧል።…

Read more: እያንዳንዱ ስደተኛ የማይገረሰስ መሠረታዊ መብት ያለው ሰው ነው!

Comments ()

ገዳመ ሲታውያን ማርያም ናዛዚት ማርታኖ ከሚገኝ ምስል የተወሰደ ፎቶ።

Read more: ቅዱስ በርናርዶስ

Comments ()
ከካስተል ጋንዶልፎ የበጋ ማረፊያቸው ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው የዕለቱን ወንጌል ማለትም ኢየሱስ በቅዱስ ቁርባን ሥጋውና ደሙ እንደሚገኝ ሲነግራቸው አይሁዳውያንና ደቀ መዛሙርቱ እንዳልተቀበሉት የሚገልጸውን የዮሐንስን ወንጌል ምዕ.6 ተመርኩዘው የተለመደው የእሑድ መልአከ እግዚአብሔር አስተምሯቸውን አስተላልፈዋል። የክርስቶስ ተከታዮች ትምህርቱን ለዘመኑ በሚመች ሁኔታ ከማስማማት ይልቅ ፈታኝ ለሆነው ለርሱ ትምህርት በሙሉ ሕይወታቸው መመለስ አለባቸው ብለዋል።…

Read more: በክርስቶስ ትምህርት ዛሬም ሰዎች ይደናቀፋሉ

Comments ()

 

(AsiaNews) - 2009-08-09 - ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ክርስቲያናዊ ሰውን ማፍቀር ኢአምላካዊ ከሆነው ሰውን ማፍቀር የሚለይ መሆኑን ያሳዩን ምስክሮች  መሆናቸውን በተከታዮቹ ሳምንታት የሚከበሩ ቅዱሳንን በማውሳት  ከካስትል ጋንዶልፎ ባደረሱት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት መልእክት ገለጹ።

በተለይም ቅዱስ ማክሲሚላን ኮልቤና ቅድስት ኤዲት ስቴይን ለሁሉም ነገር ትርጉምን የሚያሳጣው የዘመኑን አስተሳሰብ በሚጻረር መልኩ በናዚ ማጎሪያ ካምፕ ውስጥ ስለሌሎች በሰማዕትነት እንዳለፉ በማስታወስ "የናዚ ማጎርያ ካምፕ እንደማንኛውም የሞት ካምፕ ሁሉ የትልቅ ክፋት ምልክት፤ ሰው እግዚአብሔርን መርሳት ሲጀምር፣ አምላክን በሌላ በመተካት የእግዚአብሔር የሆነውን ሕይወትን የመስጠትና የመውሰድ፣ ክፉንና ጥሩን የመወሰን ሁኔታዎች ወደ ሰው ስናዞር  በምድር ላይ የሚመጣ ገሃነም ነው።... የሚያሳዝነው ግን ይህ ክስተት በጣም የተስፋፋ እውነታ መሆኑ ነው" ብለዋል።…

Read more: ፍቅር ከሞት ይበረታልና!

Comments ()

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ ለመጪው ዓመት ማለትም 2010 እ.ኤ..አ ጥር አንድ ቀን የሚያስተላልፉት ዓለም አቀፍ መልእክተ ሰላም ፡"ሰላምን ለማፍራት ከፈለግክ አከባቢህን ጠብቅ" የሚል መሆኑ በቅድስት መንበር የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት አስታወቀ።


መልእክተ ሰላሙ የዚች የምንኖርባት ምድር መጻኢ ዕድል በዓለም አቀፍ ደረጃ ኃለፊነት በመውሰድ እንድትጠበቅ የሚጠይቅና ሰላም ከሰው ክብር እና ከአከባቢ ጋር የተሳሰረ መሆኑን የሚያመለክት መልእክተ ሰላም መሆኑም ተመልክቷል። 

በቅርቡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ የጻፉት “ካሪታስ ኢን ቨሪታቴ” - ፍቅርን በእውነት- የሚለውን ሐርያዊ መልእክት ስንመለከት መልእክቱ ለአከባቢ ጥበቃ ትኩረት የሰጠ መሆኑ የሚታወስ ነው ። …

Read more: ሥነ ሕይወት በክርስትያናዊ አመለካከት

Comments ()

 

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሑድ ለበጋው ዕረፍታቸው ከሚገኙበት በለኮምበስ መንደር መኖሪያ ቤታቸው አጠገብ ከሚገኘው አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት መምራታቸው እና መንፈሳዊ መልእክት ማስተላለፋቸው ተመለከተ።

 

 

ቅዱስነታቸው ትናንትና የላቲን ሥርዓት በምትከተለው ቤተ ክርስትያን ዕለቱ የቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና የኢየሱስ አያቶች ማለት የቅድስት ድንግል ማርያም ወላጆች በዓል መሆኑን አስመልክተው በዓለም ዙሪያ ለሚገኙት አያቶች ሁሉ ለልጅ ልጆቻቸው በማስተማር ዘርፍ ላላቸው ኃላፊነት እና ለሚሰጡት ከፍተኛ ክቡር አገልግሎት አመስግነዋል። 

 

Read more: ር.ሊ.ጳ. ስለ ኢየሱስ አያቶች

Comments ()

(Independent Catholic News) - እ.ኤ.አ. በ1994 ዓ.ም. በሩዋንዳ 800,000 ሰዎችን ሰለባ ባደረገው የጅምላ ጭፍጨፋ ወቅት ሌሎችን ከሞት ለመታደግ ላደረጉት ትልቅ አስተዋፅኦ ባለፈው ሳምንት ታላቅ አክብሮት ከተቸራቸው አሥር ሰዎች መካከል አንድ ጣልያናዊ ሚሲዮናዊ አንዱ መሆናቸው ታውቋል። 

በአሁኑም ሰዓት እዚያው ሩዋንዳ ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙት አባ ማሪዮ ፋልኮኒ የቱትሲ ጎሣ አባላትን በምሥራቅ ሩዋንዳ ሙሁራ ውስጥ በሚገኘው የቁምስና ቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ በማስጠጋትና በመደበቅ በወቅቱ ከ3,000 በላይ የሆኑ ሰዎች ሕይወት መታደጋቸውን የሩዋንዳ ሬድዮ ዘግቧል።…

Read more: ሦስት ሺህ ሰዎችን በማዳናቸው ሚሲዮናዊው ተመሰገኑ

Comments ()

Subcategories

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።