Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 96

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 99

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$category_alias in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 102

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 141

(Independent Catholic News) - ከዛሬ 19 ዓመታት በፊት የጥንቆላን ነገሮች በመቃወሙ የተገደለው ደቡብ አፍሪካዊ ካቶሊክ መምህር ቤኔዲክት ዳስዋ የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ቅዱስ የመሆን ሂደት ላይ መሆኑ ተዘገበ።

ብፅዕናው ይታወጅ ዘንድ የሚያግዙ 850 ገጽ ያላቸው ሰነዶች ከአምስት ዓመት በላይ ሲዘጋጁ ቆይተው የተከናወኑ ሲሆን የቅድስና ጉዳይን ወደ ሚመለከተው የቫቲካን ክፍል መንበር ኃላፊ ሊቀ…

Read more: ግብረ ጥንቆላን በመቃወሙ የተገደለው አስተማሪ ቅድስና

Comments ()

{gallery}news{/gallery}

(ZENIT.ORG/Ewtn.com) - ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ለዕረፍት በተጓዙበት በሰሜን ጣልያን በሚገኘው አኦስታ ሐምሌ 9 ቀን ምሽቱ ላይ በደረሰባቸው ቀላል የመውደቅ አደጋ የእጅ ስብራት ያጋጠማቸው ሲሆን እዚያው በሚገኘው ኡምቤርቶ ፓሪኒ በሚባል ሆስፒታል ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው ከቫቲካን የወጣው ዘገባ ገለጸ።
የቫቲካን ማስታወቂያ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ኢየሱሳዊ አባ ፈዴሪኮ ሎምባርዲ ሁኔታውን ሲያስረዱ ር.ሊ.ጳ. ቀዶ ሕክምናውን ለማድረግ ወደ ሆስፒታል ከማምራታቸው በፊት በጠዋቱ ቅዳሴያቸውን ቀድሰውና ቁርስ አድርገው ነበር ካሉ በኋላ ለር.ሊ.ጳ. ቀላል የቀዶ ጥገና ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ የቀኝ እጃቸው መታሸጉን ገልጸዋል።

ከጠዋቱ 3:45 በሆስፒታሉ ሲደርሱ ር.ሊ.ጳ. ራጅ ለመነሣት ከርሳቸው ቀድመው የነበሩትን ሰዎች ተራ አክብረው መጠበቅን የመረጡ መሆኑንና በኋላም የቀዶ ጥገና ሕክምናው 20 ደቂቃ የፈጀ እንደነበር ታውቋል። የግል ሐኪማቸው ፓትሪሲዮ ፖሊስካ ር.ሊ.ጳ. በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም አሳውቀዋል።

ር.ሊ.ጳ. ቢኔዲክቶስ የ16 ቀን ዕረፍት ለማድረግ ወደ አኦስታ የተጓዙት ያለፈው ሐምሌ 6 ቀን መሆኑ ይታወሳል።


 

 

Read more: ር.ሊ.ጳ. የእጅ ስብራት ሕክምና አደረጉ

Comments ()

(ቫቲካን ራድዮ) ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ በቅርቡ በኢራቅ ክርስትያን የአምልኮ ሥፍራዎች ላይ የተፈጸመው የጥቃት ተግባር በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ገልጠው፣ ይህ ዓይነቱ የአመጽ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም የኢራቅ መንግሥት ባለ ሥልጣናትን በአጽንኦት አሳሰቡ።

የአመጹ ተግባር ሆን ብሎ የተደረገ ወንጀል ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል። ቅዱስነታቸው በቅ. መንበሩ ዋና ጸሓፊ በብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ በኩል ወደ ከለዳዊት ባቢሎን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አማኑኤል ደሊ ሦስተኛ በላኩት መልእክት የአመጹ ጠንሳሾች ልብ እንዲለወጥ ጸሎት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጠው፣ በመንፈስም ከኢራቁ ካቶሊካዊ እና ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረ-ሰብ ጎን መቆማቸውን አረጋግጠዋል።

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በመልእክታቸው የኢራቅ መንግሥት ባለሥልጣናት ለሁሉም የኢራቅ ዜጎች አብሮ ተቻችሎ በሰላም መኖርን እና ፍትሕን እንዲያሰፍኑ የተቻላቸውን ሁሉ እንዲጥሩ መክረዋል። 

Read more: በኢራቅ አብያተ ክርስትያናት የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ

Comments ()

 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው በቤተክርስትያን፣ በሥነ ቁጠባ እና በሥነ ምግባር መካከል ያለውን ግኑኝነት የሚዳስስ “ካሪታስ ኢን ቨሪታቴ” ማለትም "ፍቅርን በእውነት"  በሚል ርዕስ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት (encyclical letter) ነገ በይፋ ለንባብ እንደሚቀርብ ተገለጠ።

 

ቤተክርስትያን እና ሥነ ቁጠባ ለመጪው የዓለም ሥነ ቁጠባዊ ትስስር ያለው ኃላፊነትን በልዩ የሚያብራራ፣ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 23 ቀን 1985 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ሆነው ከመሾማቸው በፊት እዚህ ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ ኡርባኒያኑም መንበረ ጥበብ (የልኅቀት ማእከል - ዩኒቨርስቲ) ተገኝተው የሰጡት አስተምህሮ እ.ኤ.አ. በ1986 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ኮሙኒዮ ዩኤስኤ በተሰኘው መጽሔት ታትሞ በኢጣሊያ በ 2009 ዓ.ም. ዳግም የታተመውን የሚያንጸባርቅ ሥነ አመለካከት ዋቢ ያደረገ መሆኑም ተገልጧል።

ዓዋዲ መልእክቱም ቤተ ክርስትያን እና ሥነ ቁጠባ በሚል ርእስ ሥር ለዓለም ማኅበረሰብ እጅግ አስጊ የሆነው እና ለአደጋ የሚያጋልጠው በሰሜንና በደቡብ የዓለማችን ክፍል ያለው ያልተመጣጠነ የእድገት ልዩነት ምንኛ አደገኛና ህልውናን የሚቀናቀን መሆኑ በስፋት ተብራርቶ ለመፍትሔውም ተግባራዊ ለማድረግ አስቸጋሪ መስሎ የሚታየው ሥነ ምግባራዊ ተሃድሶ ወሳኝ መሆኑን ያበክራል። ምናልባት ቤተ ክርስትያን እና ሥነ ቁጠባ ምን ያገናኛቸዋል የሚል ተገቢ ጥያቄ ሊነሣ ይችላል፣ ሆኖም ግን ቤተ ክርስትያን በዚህ ምድር የምትጓዝ በማኅበራዊ፣ ሥነ ቁጠባዊና ፖለቲካዊ ተጨባጭ ጉዳዮች እውነትን መሠረት የሚያደርግ ግኑኝነት እንዳላት መገንዘቡ አስፈላጊ ነው።

 …

Read more: “ካሪታስ ኢን ቨሪታቴ - ፍቅርን በእውነት” - አዲሱ ዓዋዲ መልእክት

Comments ()

  ቫቲካን ራድዮ - (2009-07-07) - ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እሁድ ዕለት እኩለ ቀን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመምራታቸው በፊት እና በኋላ ባስተላለፉት መልእክት በዓለማችን በአመጽና በፍትሕ አልቦነት የሚፈሰው ደም ይቁም ሲሉ ተማጥነዋል።

የክርስቶስ ደም እግዚአብሔር ለሰው ዘር ያለው ታማኝ ፍቅር ዋስትና ነው። በምድራችን በተለያዩ ክፍሎች የሚፈሰው ደም ለሚያሰማው የጩኸት ድምፅ እግዚአብሔር መልስ የሚሰጠው በልጁ ደም ነው።

የመጨረሻ የስቃይ ጩኸት ድምፅ የሰማነው ዛሬ ጠዋት በፊሊፒንስ አገር በኮታባቶ ካተድራል በራፍ በፈነዳውና የብዙ ሰው ሕይወት ባጠፋው የግብረ ሽበራ የጥፋት ድርጊት ሰበብ የተፈጠርው ነው በማለት ስለ አደጋው የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን ገልጸው የሽበራ ድርጊት የችግር መፍትሔ አለመሆኑን በማረጋገጥ በአጽንኦት የአምጹን ተግባር ኮንነዋል።

Read more: ሰዎች ሕይወት ቅዱስ መሆኑን የሚያውቁት መች ይሆን?

Comments ()

ኦፓም በመባል የሚጠራው ከዓለማችን መሃይምነትን በማጥፋት ተልእኮ አገልግሎት የሚሰጠው እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. የተቋቋመው ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያን እና ዓለማውያን ምእመናንን ያካተተው የወንድማማችነት ልኡካን በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ማኅበር በሚሰጠው አገልግሎት አማካኝነት የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚመሰክር መሆኑን የማኅበሩ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አልዶ ማርቲኒ ገለጹ።…

Read more: መሃይምነትን በማጥፋት ክርስቶሳዊ እውነትን መመስከር

Comments ()

(ሬድዮ ቫቲካን) - 2009-06-27 - ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ ትናንትና ረፋድ ላይ በአኅጽሮተ ቃል ሮአኮ በመባል የሚጠራው የምሥራቅ አብያተክርስቲያናት ተራድኦ ማኅበር አባላትን ተቀብለው አነጋገሩ። 

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በዚሁ ግኑኝነት እንደገለጹት የመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው ጠቅሰው የቅድስት ሀገረ ጳለስጢና ቤተክርስቲያን ከእስራኤል ፍሊስጤም ግጭት የተሳሰረ መሆኑ ማመልከታቸው ተገልጠዋል።

የመካከለኛው ምስራቅ ታሪካዊ እና አሳዛኝ ግጭት መቀረፍ የሰላም እምነ መሠረት መሆኑ ያሰመሩበት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፡ በአሁኑ ወቅት ጋዛ ሰርጥ ከሁሉም በመገለል ህዝብዋ ለችግር መጋለጡ አመልክተዋል። …

Read more: ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲሰፍን በድጋሚ አሳሰቡ

Comments ()

(ቫቲካን ሬድዮ)-2009-06-24- ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16 በዓመተ ክህነት መክፈቻ ላይ ባሰሙት ስብከት የክርስቶስ አካል ለሆነችው ቤተ ክርስትያን እውነተኛ እረኞች ያልሆኑና የበጎች ሌቦች ከሆኑ የካህናቶችዋ ክፍል ኃጢኣት በላይ የሚያሳዝናትና የሚያሳቃያት ምንም የለም። የዓመተ ክህነቱ ርእሰ ጉዳይ የክርስቶስ ታማኝነት የካህናት ታምኝነት ነው፣ ይህም ክርስቶስ ለአባቱ እስከ ሞት ታማኝና ታዛዥ ሆኖ በመሥዋዕቱ ዓለምን እንደአዳነ ሁሉ ቤተ ክርስትያንም ምእመናንን የእግዚአብሔር ምሕረት ፍቅር ቀምሰው እስከመመሥከር የሚረድዋቸው እረኞች ቅዱሳን ካህናት ያስፈልግዋታል።...…

Read more: ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን ካህናት ያስፈልጓታል

Comments ()

 ቅዱስ ኣባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሁድ ሞንተካሲኖን ማለት የቅዱስ በነዲክቶስና የእህቱ የቅድስት እስኮላስቲካ አገርን መጐበኘታቸው ተመለከተ። ቅዱስነታቸው ትናንት እዚህ ጣሊያን አገር ላዚዮ ክፍለሃገር ውስጥ የምትገኘውን የሞንተ ካሲኖ ከተማና ሰበካ በጐበኙበት ጊዜ በከትማዋ ዋና አደባባይ ፒያሳ ሚራንዳ ከሃያ ሺ በላይ ምእመናን የተሳተፉበት መሥዋዕት ቅዳሴ አቅርበው ስብከት አሰምተዋል፣ የንግሥተ ሰማያት ማርያማዊ ጸሎትም መርተዋል።

በዋና አደባባዩ ላይ ባሳረጉት ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት በተለይ ሞንተካሲኖ የሁለተኛ ዓለም ጦርነት ሰለባ ከተማ መሆኑዋን ጠቅሰዋል።

Read more: ር.ሊ.ጳ የሞንተካሲኖን ገዳም ጐበኙ

Comments ()

ቫቲካን ራድዮ - 2009-06-20- ባለፉት ዝግጅቶታችን እንዳመለከትነው የካህናት ዓመት ዛሬ በጸሎተ ሠርክ ዘጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ በይፋ ተጀመረ። ይህ እ.አ.አ ከዛሬ ሰኔ 19 ቀን ጀምሮ እስከሚመጣው ሰኔ 19 2010 ዓ.ም. የሚቆይ የጸሎት የአስተንትኖና የመታደስ ጊዜ በመሆን ካህናት ለዛሬው ዓለም ሕያው የወንጌል ምሥስክርነት እንዲሰጡ የሚቀሰቅስ ነው።

 

ለዚህ የክህነት ዓመት ማወጅ ምክንያት የሆነው በትሕትናው እና በቅድስናው የካህናት ኣብነት የቅዱስ ዮሓንስ ቫያነይ የዕረፍት 150ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ነው። የቅዱስ ዮሓንስ ቫያነይ ሕይወትና የክህነት ጥሪ ልክ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው ኣንደኛ መልእክቱ ምዕራፍ ኣንድ ላይ “እግዚአብሔር ጥበበኞችን ለማሳፈር በዓለም እንድ ሞኞች የሚቈጠሩትን ሰዎች መረጠ፣ ብርቱዎችንም ለማሳፈር በዓለም እንደ ደካሞች የሚቈጠሩትን መረጠ፣ በዓለም ሰዎች ዘንድ ክቡር ሆኖ የሚታየውን ነገር ለማጥፋት በዓለም የተዋረደና የተናቀ ከንቱም መስሎ የሚታየውን ነገር መረጠ።” እንደሚለው ነው። በጊዜው በነበሩት ሰዎች ሚዛን ቅዱስ ዮሓንስ ቫያነይ ለምንም ብቃት የሌለው ተብሎ የተገመተ ብዙ የተጋለ የእግዚአብሔር ሰው ነበር፣ ሆኖም ግን እግዚአብሔር መሣርያው እንዲሆን ስለመረጠው ለክህነት አዲስ ትርጉም ሰጠው፣ ክህነት የጥቀ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ ፍቅር ነው በማለት ሌት ተቀን በቅዱስ ቍርባን ፊት ተደፍቶ በመጸለይ በአብነቱ ብዙ ሰዎች ወደ ጌታ እንዳቀረበና ከጊዜው ከነበሩ ካህናት የበለጠ እረኛ ከመሆን አልፎ የዓለም ሙሉ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ቆሞሶች ጠበቃ ሆነዋል።…

Read more: የክህነት ዓመት ዛሬ በይፋ ተጀመረ

Comments ()

 በካቶሊክ እና በሂንዱ ሃይማኖት መካከል ለሚካሄደው ግኑኝነት አንድ አዲስ ምዕራፍ መከፈቱ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚካሄደውን ግኑኝነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊ ቱራን በህንድ ሓዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው በተመለሱበት ወቅት ይፋ ማድረጋቸው ተገለጠ።

ብፁዕ ካርዲናል ቱራን በህንድ ኦሪሳ ክልል አክራሪያን የሂንዱ ሃይማኖት ምእመናን ጸረ ክርስትያን አመጽ ከማነሳሳታቸው ቀደም ብሎ እ.ኤ.አ. ባለፈው 2008 ዓ.ም. ሓዋርያዊ ጉብኝት አካሂደው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ የሂንዱ አክራሪያን ጸረ ክርስትያን አመጽ መሠረታዊው ምክንያት ለይቶ ለማወቅ ብፁዕ ካርዲናል ታውራን የሂንዱና የካቶሊክ ሃይማኖት ዓበይት መንፈሳዊ መሪዎች ጋር በመገናኘት ሀሳብ ለሀሳብ እንዲለዋወጡ ያቀረቡት ጥሪ እ.ኤ.አ. ባለፈው ሰኔ 12 ቀን 2009 ዓ.ም. በህንድ ቦምበይ ከተማ ዝግ በሆነ ጉባኤ እውን መሆኑ ተገልጠዋል። …

Read more: በሃማኖቶች መካከል በመደረግ ላይ ያለው ግኑኝነት

Comments ()

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ በቅ.ጴጥሮስ ባዚሊካ አደባባይ ለተሰበሰቡት ብዙ ምእመናን ባሰሙት አስተምህሮ በቅርቡ ወደ ቅድስት መሬት አድርገውት ስለ ነበረው ሐዋርያዊ ጉብኝት በሰፊው ገልጠው ምእመናን ለመካከለኛው ምሥራቅ ቤተክርስትያን እና አገራት ሰላምና ብልጽግና አብረዋቸው እንዲጸልዩ ጠይቀዋል፣ ለጉብኝቱ መሳካት ለተባበሩትና ለረዱት ሁሉም ከልብ አመስግነዋል።…

Read more: የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተምህሮ

Comments ()

Subcategories

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።