Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 96

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 99

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$category_alias in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 102

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 141

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት እሁድ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከመምራታቸው በፊት ዕለቱ በዛ ባሉት አገሮች ኮርፑስ ዶሚኒ በዓለ (ቅዱስ ቍርባን) ተከብሮ የሚውልበት ቀን መሆኑን አስታውሰው መላው ዓለም በረሃብ በመሰቃየት ላይ ያሉትን በሚሊዮናት የሚገመቱ ሕዝቦች ጉዳይ መረሳት እንደሌለበት አሳሰቡ።

ቅዱስነታቸው በፊታችን ሰኔ ሃያ አራትና ሃያ ስድስት በኒዮርክ ስለ ምጣኔ ሃብትና ገንዘብ መቃወስ ችግር መፍትሔ ለመሻት ሊካሄድ ታቅዶ ያለውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ ጠቅሰው የረሃቡ ክስተት ጉዳይ ጨርሶ ተቀባይነት የሌለው ምክንያት አልባ ክስተት መሆኑን አስጠነቅቀዋል። በመጨረሻም ምእመናን በፊታችን ዓርብ ስለ ሚጀመረው የክነት ዓመት እንዲጸልዩ ጠይቀዋል። 

Read more: ፍቅር “ይኖራል፣ በመኖሩም ነገሮችን ይለውጣል”

Comments ()

ቅዱስነታቸው ዛሬ በተለያዩ ቋንቋዎች ያስተማሩትና የገለጡት በንጉሥ ካርልማኝ ዘመን ስለኖረው እና ከፍተኛ ተደማጭነት ስለነበረው፣ ከቤተ ክርስትያን አበውና ጸሓፍት አንዱ ስለሆነው ዮሐንስ ስኮቱስ ኤሪጂና ነው። በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያቀረቡት እንደሚከተለው ነው።

“ኤሪጂና ስለ ምሥራቁ ሃይማኖተ አበውና ትምህርተ አበው ወይም ነገረመለኮት የነበረው ፍቅርና ስሜት በተለይ ስለ ዲዮናስዩስ ኣጥንቶ ፤ ጽሑፎቹን ሁሉ በዝርዝርና በጥንቃቄ ወደ ላቲን ቋንቋ እንዲ ተረጉም ገፋፋው። እንድ ኤሪጂና እምነት ኣማኝ የሆነው ሁሉ በመለኮትነት ባህርዩን የምንሳተፈውን ኣምላክ ተመስጦአዊ ስግደት ወይም አምልኮ ማቅረብ እስክሚቻለው ድረስ ሐቅን መፈለግ ወይም መሻት የግድ ይለዋል፤ የሚል ነበር ነገር ግን የዚህ ዓይነቱ ስግደት እና አምልኮ ተመክሮ በቃላት ሊገለጥ ስለማይቻል የኤሪጂና ተዮሎጊ ቀጣይነት የሚያገኘው በአታፋሲስ ማለት ኣስቀድሞ ኣምላክ ያልሆነውን ነገር በማወቅና በማረጋገጥ ነው”።

Read more: የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የዕለተ ሮቡዕ አስተምህሮ (እ.አ.አ. ሰኔ 10 ቀን 2009)

Comments ()

 

የብፁዕ አቡነ ኪዳነማርያም ፀሎተ ፍትሐት ሐሙስ ግንቦት 27 ቀን 2001 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በ11፡30 በአዲስ አበባ ልደታ ማርያም (ካቴድራል) ቤተክርስቲያን ወዳጅ ቤተዘመዶቻቸው በተገኙበት ተከናውኗል፡፡

 

የፍትሐት ሥነስርዓቱን የመሩት ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሲሆኑ በሥነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት፣ ብፁዕ ሊቀጳጳሳት ጆርጅ ፓኒኩለም በኢትዮጵያ የቅድስት መንበር ተወካይ፣ ክቡር አቶ ስዩም መስፍን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ሌሎች የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተወካዮች፣ ቤተዘመዶቻቸው፣ በርካታ ካህናት፣ ደናግልና ምእመናን ተገኝተዋል፡፡…

Read more: የብፁዕ አቡነ ኪዳነማርያም ጸሎተ ፍትሐት

Comments ()

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የቼክ ሬፐብሊክ መንግሥት መሪ ፕሬዝዳንት ቫክላቭ ክላዉስ እና የሀገሪቱ ረኪበ ጳጳሳት ባደረጉላቸው ግብዣ መሠረት፣ እኤአ ፊታችን መስከረም ወር 26 ቀን በረፓብሊክ ቸክ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የቫቲካን ማኅተም ክፍል መገለጫ አስታውቀዋል።

በዚሁ መግለጫ መሠረት፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በረፓብሊክ ቸክ ቆይታቸው ርእሰ ከተማ ፕራግ ብርኖ ስታራ፡ በለስላቭ ይጐበኛሉ።…

Read more: ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቼክ ሬፐብሊክን ይጐበኛሉ

Comments ()

 

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ባወጁት መሠረት ከሁለት ሳምንታት በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዓመተ ክህነት መከበር እንደሚጀመር በቅድስት መንበር ይፋ መግለጫ ተሰጥተዋል። በቅድስት መንበር የቤተ ክህነት ቅዱስ ማኅበር ዋና ሐላፊ ብፁዕ ካርዲናል ክላውድዮ ሁመስ አራት መቶ ሺ ለሚሆኑ ካህናት ባስተላለፉት መልዕክት እንዳመለከቱት፡ ካህናት በሙያቸው ብቻ ሳይሆን ሁለንትናችው እጅግ በጣም አስፈላጊዎች እና ውድ ናቸው። ምእመናን ካህናትን በሐዋርያዊ ሙያቸው ደስተኞች እና ቅዱሳን እንዲሆኑለት እንደሚፈልግ ብፁዕ ካርዲናል ክላውድዮ ሁመስ ለካህናቱ በጻፉት መልዕክት መግለጣቸውም ተመልክተዋል።…

Read more: ከሁለት ሳምንታት በኋላ ዓመተ ክህነት መከበር ይጀመራል፡

Comments ()

 ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ኣሥራ ስድስተኛ ዛሬ ረፋድ በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ አደባባይ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ስለ ነበረው ትልቁ የምንኵስና አብነት የሆነው ራባኑስ ማውሩስ ላይ ያተኮረ ጉባኤ አስተምህሮ አቅርበዋል። ቅዱሱ አባታችን ጉባኤ አስተምህሮውን በጸሎት ከከፈቱ በኋላ የሚከተለው ከመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 25 ከቍ. 4-10  

 

 …

Read more: የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የዕለተ ሮቡዕ አስተምህሮ (እ.አ.አ. ሰኔ 3 ቀን 2009)

Comments ()

 በኢራቅ በተለይ ደግሞ በባግዳድ የሚኖሩት የአገሪቱ ማኅበረ-ክርስትያን ላይ ምክንያቱ ገና እውን ያልሆነ ለድጋፍና እርዳታ ለማቅረብ እየተባለ በአንዳንድ ግለ ሰዎች የክርስትያን ሕዝብ የብዛት የንብረት ቆጠራ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑ በመጥቀስ የአገሪቱ ከለዳውያን ብፁዓን ጳጳሳት፣ ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢና ሕልውናን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ገሃድ አድረገዋል።

ይህ ጉዳይ ምን ያስከትል ይሆን ለሚለው ጥያቄ…

Read more: የኢራቅ ማኅበረ ክርስትያን

Comments ()

የምሥራቅ አቢያተ ክርስትያናት ጥበቃ ቅዱስ ማኅበር ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ለዮናርዶ ሳንድሪ እዚህ በቫቲካን ባለፈው ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. የሳሌዚያን (ዶን ቦስኮ) ማኅበር ባከበረው ዓመታዊ የማርያም ረዳኢተ ክርስትያን በዓል ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ በመምራት ባሰሙት ስብከት፣ “ቅድስት ድንግል ማርያም ስለኛ በጌታ ፊት የምትማጠን የሁላችን ረዳት እናት ነች። የእግዚአብሔር የማዳን እቅድ በሙላት የፈጸመው ልጅዋ ቅርብ በመሆን፣ የእርሱ ሙሉ ኃይል ወሮታ ሆኖልናል፣ ማርያም ስለኛ ኃጢአት ምሕረትን የምትማጠን የሐጥአን ጠበቃ ነች” ብለዋል።…

Read more: ረዳኢተ ክርስትያን

Comments ()

በቀዳሚው ዘመን በነበረችው ቤተክርስትያን ታሪክ ቀደምት የእምነት ሰማዕት ተብለው ከሚጠቀሱት ቀደምት ሰማዕታት ቅድስት ካተሪና ዘ አለክሳድሪያ መሆኗ የቤተክርስትያን ታሪክ የሚገልተው ሲሆን። በዚህ የእምነት ሰማዕት ስም የሚጠራው አዲስ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስያን እ.ኤ.አ. እሁድ ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በሮማ ከተማ መባረኩ ተገለጠ።…

Read more: በሮማ አዲስ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን

Comments ()

 ኬኒያ የሞምባሳ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቦኒፋቸ ለለ “የአገሪቱ መንግሥት የአገሪቱ ሕዝብ የተደቀነበት አደገኛው ዘርፈ ብዙ ችግሮችን መፍትሔ እንዲገኝ ለማድረግ መከባበር እንዲሁም ሚዛናዊና ትክክለኛ ወይይት በማስቀደም ብቻ ነው የሚያስፈልገው” በማለት በቅርቡ አገሪቱን በመምራት ላይ ባለው በቅይጡ የፖለቲካ ሠልፍ የተመለመለው መንግሥት እያጋጠመው ያለው አለ መግባባት እና እየከፋ በመሄድ ላይ ያለው ችግር በመጥቀስ ባስተላለፉት መልእክት ማብራራታቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።…

Read more: የሞምባሳ ሊቀ ጳጳሳት መልእክት

Comments ()

 የመገናኛ ብዙኀን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ኀላፊነት መሠረት "Pope2you" በተሰኘው መጠሪያ ለወጣቶች ያቀና አዲስ ድረ ገጽ ላገልግሎት እንደሚውል ተገለጠ። ይህ አዲስ ድረ ገጽ ግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ታስቦ በሚውለው 43ኛው ዓለመ ዓቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ቀን ምክንያት በማድረግም ጳጳሳዊ የመገናኛ ብዙኀን ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት በይፋ እንደሚያስተዋውቀው፣ የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ ትላትና በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።…

Read more: የቫቲካን አዲስ ድረ ገጽ

Comments ()
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ በቅ.ጴጥሮስ ባዚሊካ አደባባይ ለተሰበሰቡት ብዙ ምእመናን ባሰሙት አስተምህሮ በቅርቡ ወደ ቅድስት መሬት አድርገውት ስለ ነበረው ሐዋርያዊ ጉብኝት በሰፊው ገልጠው ምእመናን ለመኸከለኛው ምሥራቅ ቤተክርስትያን እና አገራት ሰላምና ብልጽግና አብረዋቸው እንዲጸልዩ ጠይቀዋል፣ ለጉብኝቱ መሳካት ለተባበሩትና ለረዱት ሁሉም ከልብ አመስግነዋል።…

Read more: የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተምህሮ

Comments ()

Subcategories

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።