Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 96

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 99

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$category_alias in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 102

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 141

ቅዳሜ የካቲት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ መሪነት በተካሄደው የቅርብ አማካሪዎቻቸው ማለትም የካርዲናሎች ስብሰባ ሀያ አዳዲስ ካርዲናሎች የሥያሜያቸው ሥርዓት ተፈጽሞላቸዋል። በዚህም ሥርዓት ታኅሣሥ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ካርዲናለነታቸው የታወጀላቸው በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያን የአዲስ አበባ ኤጳርኪያዊ ሊ.ጳጳሳት ብጹእ አባታችን ብርሃነየሱስሱራፌልና ሌሎች አሥራ ዘጠኝ ካርዲናላት የተለመደው ቀይ ቆብና ልብስ የተሰጣቸው ሲሆን…

Read more: የብጹእ አባታችን ብርሃነየሱስ ሱራፌል ካርዲናልነት ሥያሜ ሥርዓት ተከናወነ

Comments ()

ታኅሣሥ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ከተለመደው የእለተ ሰንበት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ጋር በማያያዝ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ሀያ አዳዲስ ካርዲናላትን የሠየሙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የአዲስ አበባ ኤጳርኪያዊ ሊ.ጳ. ብጹእ አባታችን ብርሃነየሱስ ሱራፌል እንደሚገኙበት ታውቋል።

እነዚህ ሀያ ካርዲናላት ከአምስቱም አህጉራት የተወጣጡና ከአሥራ አራት አገሮች የተመረጡ ሲሆን፤ መጪው የካቲት 7…

Read more: የአዲስ አበባ ኤጳርኪያዊ ሊ.ጳ. ብርሃነየሱስ ሱራፌልን ጨምሮ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ 20 አዳዲስ ካርዲናላትን ሠየሙ

Comments ()

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በፈረንጆቹ የገና በዓል ዋዜማ ላይ በኢራቅ በሚገኘው አንካዋ ተብሎ ወደ ሚጠራው የስደተኞች ካምፕ ስልክ በመደወል፣ ንግግራቸው 

በአካባቢው በሚገኙ ካህን አማካኝነት በአረብኛ ተተረጉሞ መልእክት አስተላልፈዋል።

የስልክ መልእክታቸውን “እንደምን አመሻችሁ” ብለው በመጀመር “በዚህች የገና ምሽት ሁላችሁም ሰላምታየ ይድረሳችሁ። አሁን የገናን በዓል ቅዳሴ ለማሳረግ ዝግጁ ናችሁ፤ እኔም በዚህ መሥዋዕተ…

Read more: ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ለኢራቃውያን ስደተኞች ገና በዓል በስልክ ያስተላለፉት መልእክት

Comments ()


የ81 ዓመት እድሜ ባለጸጋ የነበሩት የቀድሞው የሲታውያን ማኅበር ጠቅላይ አበምኔት ክቡር ማውሮ ኤስቴቫ በአጭር ጊዜ ሕመም ኅዳር 5 ቀን 2007 ዓ.ም. ስፔን በሚገኘው ፖብሌት ገዳማቸው ከዚህ ዓለም ወደ ጌታቸው እቅፍ ተሻግረዋል።

ነፍሰ ኄር ጠቅላይ አበምኔት ማውሮ ኤስቴቫ እንደ መነኮስ ለ55 ዓመታት፣ ከዚህም ውስጥ እንደ ካህን ደግሞ 47 ዓመት ያሳለፉ ሲሆን፤ ከ1963-1991 ዓ.ም. ድረስ የፖብሌት ገዳም አበምኔት፤ በመቀጠልም ከ1987-2003 ድረስ የሲታውያን ማኅበር ጠቅላይ አበምኔት ሆነው አገልግለዋል። የቀብር ሥርዓታቸው ኅዳር 8 ቀን በገዳማቸው ተከናውኗል። 

ነፍሰ ኄር ጠቅላይ አበምኔት ማውሮ ኤስቴቫ በተለየ ሁኔታ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ሲታውያን መነኮሳት ልዩ ቦታ የሚሰጡና ለገዳሞቻችንም ብዙ በማቀድና ያቀዱትም ከግብ እንዲደርስ የሚቻላቸውን የጣሩ ሲሆን እኛም እኚህን አባት ለሰጠን አምላክ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ በቅንነት ያገለገሉት እግዚአብሔር በእቅፉ እንዲቀበልልን ጸሎታችን ነው።

ሀቦ እግዚኦ እረፍተ ዘለዓለም፤ ወአብርህ ሎቱ ብርሃነ ዘለዓለም። ወይኩን እረፍቱ በሰላም አሜን።

 

Read more: የቀድሞው የሲታውያን ጠ. አበምኔት ዜና እረፍት

Comments ()

የክርስትና እምነቷን ትታ ወደ እስልምና እንድትለውጥ ተጠይቃ እምቢ በማለቷ የሞት ፍርድ ተፈርዶባት የነበረችው ሚሪያም ኢብራሂም ትላንትና ሐሙስ ጠዋት ወደ ጣልያን ገብታ በቫቲካን ከር.ሊ.ጳ. ጋር ተገናኝታለች። በዚህም ወቅት ቤተሰቦቻ ማለትም ባለቤቷ ዳንኤል ዋኒ፣ የአንድ ዓመት ተኩል እድሜ ያለው ልጃቸው ማረቲን እና ከሁለት ወር በፊት በእስር ቤት ሳለች የወለደቻት ማያም አብረው ተገኝተዋል።…

Read more: በ"እምነት ክህደት" ሞት ተፈርዶባት የነበረችው ሱዳናዊት ክርስቲያን ሚርያም ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጋር ተገናኘች

Comments ()

ስፖርት የመቻቻልና የሰላም ትምህርት ቤት ነው! ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ዛሬ ለሚጀመረው ለ2006 ዓ.ም. የዓለም ዋንጫ ትላንትና ረቡዕ ለአዘጋጆች፣ ለተጫዋቾችና ለደጋፊዎች የሚሆን የሰላም መልእክት አስተላለፉ።

ር.ሊ.ጳ. ለብራዚሏ ርእሰ ብሔር ዲልማ ረውሴፍ ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ በማንኛውም ደረጃ ዘረኝነትን መዋጋት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። በተጨማሪም ስፖርት አንዱ ከሌላው ጋር…

Read more: ስፖርት የመቻቻልና የሰላም ትምህርት ቤት ነው! ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

Comments ()

..ጳ. ፍራንቼስኮስና የቁስጥንጥኒያ መንበር ፓትሪያርክ የሆኑት በርቶሎሜዎስ ቀዳማዊ ባለፈው እሑድ በኢየሩሳሌም ተገናኝተው ስለ ክርስቲያኖች ኅብረት በአንድ ላይ ሆነው ጸሎት ያደረሱ መሆኑና ስለ ር.ሊ.ጳ. የሦስት ቀናት ቆይታም ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስና የፓትሪያርክ በርቶሎሜዎስ ቀዳማዊ የክርስቲያኖች ኅብረት ጸሎታቸውን ያደረሱት በክርስቲያኖች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት፣ የተቀበረበትና ከሞትም የተነሣበት ነው…

Read more: ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስና ኦርቶዶክሳዊው ፓትሪያርክ በርቶሎሜዎስ ስለ ክርስቲያኖች ኅብረት በኢየሩሳሌም ጸሎት አደረሱ

Comments ()

ቅ.አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቼስኮስ በመካከለኛ ምሥራቅ አገሮች በዮርዳኖስ በፍልስጥኤም እና በቅድስት መሬት በቤተ ልሔም እስራኤል ውስጥ ሐዋርያዊ ዑደት ለማድረግ ግንቦት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ከሮም ተጉዘዋል።
ቅዱስነታቸው ዘወትር እንደሚያደርጉት ከጉዛቸው በፊት ማምሻውን በሳንታ ማሪያ ማጆሬ ዐቢይ ደብር በመሄድ ይህንን ጉዞ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም በማማጠን ጉዞው የተሳካና ፍሬ…

Read more: የቅዱስ አባታችን የመካከለኛ ምሥራቅ አገራት ጉብኝት

Comments ()

በትላንትናው እለት በቫቲካን የሚገኘው የተንጣለለው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አራት የቅዱስ ጴጥሮስ ተኪዎችን ያስተናገደበት ልዩ መንፈሳዊና ታሪካዊ ክስተት ነበር፤ ሁለቱ በእለቱ ቅድስናቸው በይፋ የታወጀላቸው ቅዱሳን ዮሐንስ ፳፫ኛውና ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ የቀድሞው ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛውና ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ናቸው።

ወደ አንድ ሚሊየን የሚጠጋው ሕዝበ ክርስቲያን በስምንት…

Read more: “የእግዚአብሔርን ምሕረት የመሰከሩና ያስተማሩ የ፳ኛው ክ.ዘ. ር.ሊ.ጳጳሳት”

Comments ()

ቅዱስ አባታችን .ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ጥዋት በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ "የጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ ከሚሰጠው ደስታ የሚፈሩና በዚህም ሕይወታቸው ወደ መቃብር የሚጓዙ በሚመስል ሓዘን የተሸፈኑ አንዳንድ ክርስትያኖች አሉ፤ ሆኖም ጌታ ከሙታን ተለይቶ በመነሣት ዘወትር በመካከላችን ስለሚገኝ መደስት አለብን" ሲሉ የጌታ ትንሣኤ ብርሃን ከሚሰጠን ደስታ በመፍራት እንደ…

Read more: የሌሊት ወፍ ክርስቲያኖች ከመሆን ይሰውረን!

Comments ()

የ፳፻፮ ዓ.ም. የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ መልእክተ ሆሣእና ለወጣቶች

የተወደዳችሁ ወጣቶች ሆይ!

በዚህ ዓመት ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5፡1-12ላይ ስለ ብፅዕና የሚዳስሰውን የክርስቶስ የተራራ ላይ ስብከት እናስተነትናለን፡፡ ይህ ስብከት ውብ በሆነው በገሊላ ባሕር አጠገብ በሚገኘው ተራራ ላይ የተደረገ ዘለዓለማዊ ደስታን የሚሰጥ ስብከት ነው፡፡ ከዚህ ማራኪ እና ልብ የሚነካ የክርስቶስ አስተምሕሮ…

Read more: ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለማኝ ነው - ለድሆች ያለንን አመለካከት እንቀይር!

Comments ()

ኢየሱስ ክርስቶስ የሥጋ እና የነፍስ ቋሚ እና ዘላለማዊ ወጌሻ ነው”

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ

ከአርባ ጾም መግቢያ በፊት በነበረው የረቡዕ ዕለት መደበኛው የአስተምሕሮ ጊዜያቸው ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በሮም የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡትን ምእመናን ወደ ንሰሐ ለመሄድ ደፋሮች እንዲሆኑ አበረታተዋቸዋል፡፡ ር.ሊ.ጳ. ፍርንችስኮስ በዚሁ ጊዜ “ሁሉም ሰው እንዲህ ይላል፡-…

Read more: “ንስሐ መግባትን አትፍሩ

Comments ()

Subcategories

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።