Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 96

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 99

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$category_alias in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 102

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 141

ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳትና የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት የ2006 ዓ.ም. የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት ለመላው ምዕመናን ያስተላለፉት መልዕክት

በስመ አብ ወወልድ መንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

 "የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከልን" (ገላ 4፡4)

 የተወደዳችሁ ምዕመናን፣ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች፣ ካህናትና ደናግል፣ በጎ ፍቃድ ያላችሁ…

Read more: የሊ. ጳ. ብርሃነየሱስ የ፳፻፮ ዓ.ም. የጌታችን ልደት መልእክት

Comments ()

አዲስ አበባ ታኅሣሥ 16 ቀን 2006 ዓ.ም./ ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰበካዊ ጉባኤ ፍሬ የሆነውን የሰበካው አገልግሎቶች የወደፊት አቅጣጫ ማመላከቻ ሠነድ – ለጉባኤው መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረጉ የቤተክርስቲያን ምሁራን፣ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ መነኮሳት ወንድሞችና እኅቶች እንዲሁም ምእመናን በተገኙበት – ረቡዕ ታኅሣሥ 16 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሴቶች እድገት ማዕከል ተቀብለዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ያጸድቁታል ተብሎ የሚጠበቀው ይኸው ሠነድ በቤተሊቀጳጳሳት አስተዳደርና መዋቅር (Curia) ተግባራዊነት ዙሪያ ጥናት የሚደረግበትን ሁኔታና ከቀኖና ሕግጋት ጋር የሚጣጣምበትን መንገድ ያመላክታል፡፡

የምእመናን ሐዋርያዊ ምክር ቤት እና የቊምስና ሐዋርያዊ ምክር ቤት አወቃቀርና…

Read more: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰበካዊ ጉባኤ ፍሬ የሆነው የሀገረ ስብከቱ አገልግሎቶች የወደፊት አቅጣጫ አመላካች ሠነድ በቅርቡ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Comments ()

በክርስቶስ በጋራ መጓዝ በሚል ርእስ የተካሄደው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰበካዊ ጉባዔ - ሲኖዶስ ተጠናቀቀ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሐዋርዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ቢሮ የእምነት ዓመት መዝጊያን ተመርኩዞ ያዘጋጀው ሰባከዊ ጉባዔ ከኅዳር 26 እስከ 28 ቀናት 2006 ዓ.ም. የሴቶች እድገት ማዕከል ከተናወነ በኋላ ኅዳር 29 ቀን 2006 ዓ.ም በክርስቶስ ንጉሥ በዓል በልደተ ማርያም ካቴድራል በመስዋዕተ ቅዳሴ በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ የሰበካውን ጉባዔ ይዘትና ዓላማ አስመልክተው ባስተላለፉት ጋዜጣዊ መግለጫ "ይህ ሰበካዊ ጉባኤ በራሱ መጨረሻ ሳይሆን የሥራው ጅማሮ ነው፡፡ በክርሰቶስ በጋራ የምናደርገው ጉዞም በሰብአዊ ፣በአእምሯዊ፣ በመንፈሳዊ፣ እና በሐዋርያዊ ማንነታችን በሙላት ለመታነጽ ነው፡፡" ካሉ በኋላ አክለውም "ይህ እውነታ የሀገረ ሰብከታችንን ጉዞ በእምነት፣ በተስፋ እና በፍቅር የታጀበ ያደርገዋል፡፡ ሲኖዶስ የሚካሔደው በጋራ በሚደረግ ጸሎት፣ አስተንተኖ እና ምክክር ወደ መንፈሳዊ ተሐድሶ ለመድረስ ነው፡፡ ይህንን ጉዟችንን እና ሀገረስ ብከታችንን በሙሉ ለኪዳነ ምሕረት እናታዊ ምክር እና ጥበቃ አሳልፈን እንሰጣለን፡፡" ብለዋል፡፡
ሰበካዊ ጉባዔው ባለፈው ዓመት…

Read more: የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰበካዊ ጉባዔ - ሲኖዶስ ተጠናቀቀ

Comments ()

VOA — በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ አዲስ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ እየተገነባ ነው። የኢትዮጵያ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ቅዱስ ቶማስ አኳይናስ አሁን ለጊዜው በካቶሊክ ካቴድራል ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው ያለው። በካቶሊክ እምነት የሚመራው ዩኒቨርሲቲ  አላማ  ሀላፊነት የሚሰማቸው የወደፊት የሀገር መሪዎችን ለማፍራት የታቀደ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው አለም አቀፍ የትምህርት ተቋም እንዲሆን ለማድረግ እንደሆነ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሊቀ-ጳጳሳት አቡነ ብርሀነ-የሱስ ገላጸዋል። 

ዩኒቨርሲቲው የሚሰራው የኢትዮጵያ መንግስት በሰጠው 60 ኤክር መሬት ሲሆን የመጀመርያውን ደረጀ ለመገንባት መሰረተ ልማት የተጣለው ባለፈው አመት ሚያዝያ ወር ላይ ነው።

 አዲስ አበባ የሚመሰረተው ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያው ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚባልውንም ዩኒቨርሲቲ የመሰረተችው ካቶሊካዊት ቤተክስትያን እንደሆነች  አስመራ ላይ የነበረው ዩኒቨርሲትም  በካቶሊክ ቤተክርስትያን እንደተመሰረተ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ብርሀነ-የሱስ አክለዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን አሁን በአዲስ አበባ የምትመሰረተው የመጀመርያው የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ግን በካቶሊክ ቤተክርስትያን የሚመራ እንደሆነ አስገንዝበዋል። ሙሉውን ዝግጅት ያድምጡ።   http://amharic.voanews.com/audio/audio/342599.html

Read more: የመጀመርያው ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ

Comments ()

ጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ክብር አባ ጸጋዬ ቀነኒን የሶዶ ሐዋርያዊ መንበር ተተኪ ጳጳስ አድርገው ሰይመዋል።

አባ ጸጋዬ ቀነኒ የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ካህን ሲሆኑ የነቀምቴ ሐዋርያዊ መንበር ዓቃቤ ሆነውም ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ክቡር አባ ጸጋዬ የተወለዱት በኅዳር 13 ቀን 1936 ዓ.ም. ሲሆን ሐምሌ 6 ቀን 1968 ዓ.ም. ደግሞ ሢመተ ክህነት ተቀብለዋል። አሁን በጵጵስና የተሰየሙበት የሶዶ ሐዋርያዊ መንበር ከአምስት ሚሊየን በላይ የሚሆን ሕዝብ የሚኖርበት አካባቢ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 145 ሺህ የሚጠጉ ካቶሊካውያን በ39 ካህናትበ23 ቁምስናዎች ውስጥ ይገለገላሉ፤ በዚሁ ሐዋርያዊ መንበር 41 ደናግላትና /ሲስተሮች/ 18 ለምስጢረ ክህነት የሚዘጋጁ ወጣቶች ይገኛሉ። 

ምንጭ፡- http://en.radiovaticana.va/news/2013/10/11/a_coadjutor_named_for_soddo_in_ethiopia/en3-736537

Read more: ክብር አባ ጸጋዬ ቀነኒ የሶዶ ሐዋርያዊ መንበር ተተኪ ጳጳስ ሆነው ተሰየሙ

Comments ()

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ 50ኛው የዓለም የጥሪ ጸሎት ቀን መልእክት

"ጥሪ በእምነት የታነጸ የተስፋ ምልክት"

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እኅቶቼ:-

"በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፣ እኔም አውቃቸዋለሁ፣ ይከተሉኝማል እኔም የዘለዓለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ ለዘለዓለምም አይጠፉም፤ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም፡፡ የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፣ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም፡፡ እኔ እና አብ አንድ ነን፡፡" (ዮሓ 10፡27-30)

እነዚህ ቃላት የኢየሱስን ጠቅላላ መልእክት ያዘሉ የወንጌሉ ጭብጥ ናቸው፡፡ እርሱ የሚጠራን ከአብ ጋር ባለው ወዳጅነት ውስጥ ሱታፌ እንዲኖረን ነው፤ ይህም ዘለዓለማዊ ሕይወት ነው፡፡

ኢየሱስ ከወዳጆቹ ጋር ሊመሠርት የሚፈልገው ግንኙነት በእርሱ እና በአባቱ ግንኙነት አምሳል ነው፤ ይህም ግንኙነት በሙሉ እምነት ራስን አሳልፎ የሚሰጥ እና የጠለቀ አንድነት ያለበት ነው፡፡ ይህንን ጥልቅ ምሥጢር እና የወዳጅነት ምሳሌ አድርጎ ይጠቀማል፤ እረኛው ይጠራቸዋል፣እነርሱም ድምፁን ያውቁታል፣ ለጥሪውም ምላሽ በመስጠት ይከተሉታል፡፡ የድምፁ ምሥጢር የሚያሳስበን ነው፤ በእናታችን ማኅጸን ሳለን የእርሷን እና የአባታችንን ድምፅ ለማወቅ ድምፁን እናስተውላለን፤ ድምፁ ይዞት የሚመጣው ፍቅር ወይም ንቀት፣ እንክብካቤ ወይም ቸልተኛነት ሊሆን ይችላል፡፡ የኢየሱስ ድምፅ ግን ይለያል! ለይተን ያወቅነው እንደሆነ ከሞት ጨለማ በላይ በሆነ የሕይወት መንገድ ላይ ይመራናል፡፡

ነገር ግን አንዲት ቦታ ላይ ኢየሱስ በጎቹን ጠቅሶ እንዲህ ይላቸዋል፡-…

Read more: የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ 50ኛው የዓለም የጥሪ ጸሎት ቀን መልእክት

Comments ()

ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት የ2005 ዓ.ም. የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤን በዓል በማስመልከት ለመላው ምዕመናን ያስተላለፉት መልዕክት፡፡

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

 "እርሱ ግን እንዲህ አላቸው አይዞአችሁ አትደንግጡ እናንተ የምትፈልጉት ተሰቅሎ የነበረውን የናዝሬቱን ኢየሱስ እንደሆነ አውቃለሁ እርሱ ተነስቶአል፤ እዚህ የለም የተቀበረበት ቦታ ይኸውላችሁ…

Read more: የብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ የ2005 ዓ.ም የጌታችን ትንሣኤ በዓል መልእክት

Comments ()

የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ስብከት ዘሆሳዕና 2005 ዓ.ም.

1. ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ በርካታ ተከታዮቹ ታላቅ በዓል አደረጉለት፤ ልብሶቻቸውን በፊቱ አነጠፉለት፣ እርሱ ስላደረገላቸው ተዓምራት በብዙ ይነጋገሩ ነበር፣ "በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተመሰገነ ነው፤ ምሥጋና በሰማይ ለእግዚአብሔር ይሁን ሰላምም በምድር በጎ ፈቃድ ላላቸው ይሁን" የሚል ታላቅ የምሥጋና ድምፅ ይሰማ ነበር፡፡ (ሉቃ 19፡38)

ተከታዮቹም በምሥጋና፣ በታላቅ በዓል፣ በበረከት እና በሰላም ተሞሉ፤ የደስታ መንፈስ ሰፈነ፡፡ ኢየሱስ በተለይ በድሆች እና በሚስኪኖች፣ በትሑታን እና በተረሱት ሰዎች ልቦና ውስጥ ትልቅ ተስፋ ቀሰቀሰ፡፡ እነዚህ ሰዎች በዓለም ፊት ለዓይን የማይሞሉ ነበሩ፡፡ እርሱ የሰው ልጆችን ስቃይ ያውቀዋልና የእግዚአብሔርን የምሕረት ፊት አሳያቸው፤ ነፍስን እና ሥጋን ለመፈወስ ሲል ዝቅ አለ፡፡

ይሄ ኢየሱስ ነው፡፡ ይህ ድካማችንን፣ ኃጢአታችንን እንዲሁም እያንዳንዳችንን የሚመለከተን ልቡ ነው፡፡ የኢየሱስ ፍቅር ታላቅ ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ ፍቅር ወደ ኢየሩሳሌም በመግባት አኛን ይመለከተናል፡፡ በጣም ውብ የሆነ ገጽታ ነው፤ በኢየሱስ ልብ ፍቅር ብርኃን የተሞላ ነው፤ በደስታ እና በበዓል መንፈስ የተሞላ ነው፡፡

በቅዳሴያችን መጨረሻ ላይ እኛም ይህንኑ እንደግመዋለን፡፡

ዘንባባችንን እና የወይራ ቅርንጫፎቻችንን እናውለበልባለን፡፡ አኛም ኢየሱስን በቤታችን እንቀበለዋለን፤ ከእርሱ ጋር በመንገዱ ላይ በመገኘታችን የተነሳ ደስታችንን እንገልፃለን፡፡ ቅርባችን መሆኑን በምናውቅበት ጊዜ፣ በማንነታችን ውስጥ በመገኘቱ፣ ጓደኛችን ሆኖ በመቅረቡ፣ ወንድማችን በመሆኑ እና በንጉሥነቱ እንደሰታለን፤ ይህም ለሕይወታችን የሚያበራ በተራራ ላይ ያለ መብራት ነው፡፡ ኢየሱስ አምላክ ነው ነገር ግን ዝቅ ብሎ ከእኛ ጋር ለመጓዝ ራሱን ዝቅ አደረገ፡፡ እርሱ ጓደኛችን እና ወንድማችን ነው፡፡…

Read more: የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ስብከት ዘሆሳዕና 2005 ዓ.ም.

Comments ()

ቤተ ክርስቲያን ልጆችን የምትወልድ እናት እንጂ የምታስተኛ ሞግዚት መሆን የለባትም!

ወንጌልን የማስፋፋት ኃላፊነት የካህናት ብቻ አይደለም ሲሉ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በረቡዕ ጠዋት ስብከታቸው ከመጋቢት ምርጫ ጀምሮ በሚኖሩበት ዶሙስ ሳንክቴ ማርቴ ተብሎ በሚጠራው የቫቲካን እንግዳ ማረፊያ ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ አሳሰቡ።

በዚሁ ቤተ ጸሎት በየእለቱ በሚያሳርጉት ቅዳሴ ላይ…

Read more: ቤተ ክርስቲያን ልጆችን የምታስተኛ ሞግዚት መሆን የለባትም!

Comments ()

"ዓለም ዓይኖቹን ወደ እግዚአብሔር ማንሳት ተስኖታልና" ካቶሊኮች "የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ደስታን" ለዓለም በማሳየት የሰው ልጆችን ያገለግሉ ዘንድ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ አሳሰቡ።

"የእግዚአብሔር ልጆች የመሆናችንን ደስታና በክርስቶስ እንኖር ዘንድ የሰጠንን ነጻነት እናሳይ፣ ወደ አምላክ ማየት ለተወው ዓለም ይህ ውድ የሆነ አገልግሎት ነው" በማለት ትላንትና ረቡዕ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት 40 ሺህ ሰዎች ተናግረዋል።

"ይህ ማለት በእያንዳንዷ ቀን ክርስቶስ ይለውጠንና እርሱን እንዲያስመስለን መፍቀድ አለብን ማለት ነው፤ ይህም ደካማነታችንን እና ጉድለታችንን ብናውቅም እርሱን ለመከተል በመጣር እንደ ክርስቲያኖች ለመኖር መሞከር ማለት ነው" በማለት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ አብራርተዋል።

ሲቀጥሉም "በውድቀቶቻችን ተስፋ ሳንቆርጥ በእርሱ መፈቀራችንን ሊሰማን ይገባል፤ ይህ ሲሆን ሕይወታችን በደስታና በርጋታ መንፈስ የተሞላ አዲስ ይሆናል። እግዚአብሔር ብርታታችን ነው! እግዚአብሔር ተስፋችን ነው!" ብለዋል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ የእግዚአብሔር ልጅነታችንን ከክርስቶስ ትንሣኤና የማዳን ዋጋ ጋር በማስተሳሰር ካቶሊካዊ እምነት በትንሣኤ ላይ የተመሠረተና ከዚህም ውጪ ሲሆን ከንቱና እንደሚፈርስ ቤት መሆኑን አስታውሰዋል።

ር.ሊ.ጳ. የእለተ ረቡዕ አስተምህሯቸውን ሐዋሪያዊ ቡራኬ በመስጠት ከደመደሙ በኋላ ከ15 ደቂቃ በላይ ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅለው በመጨረሻም ለሕጻናትንና አካል ጉዳተኞችን ሰላምታን ሰጥተዋል።

ምንጭ፡- http://www.catholicnewsagency.com/

Read more: ካቶሊኮች የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ደስታን በማሳየት ዓለምን አገልግሉ

Comments ()

"የትሕትና እና የርኅራኄ መንፈስ አውርሰውናል"

ር.ሊ.ጳ. ፍራነቼስኮስ አዲሱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እረኛ ሆነው ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው ጋር ቅዳሜ መጋቢት 14 ጠዋት ተገናኝተዋል።

በዚህ ግንኙነታቸው ወቅት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ "እኛ ወንድማማቾች ነን" ሲሉ ያላቸውን ፍቅር ገልጸዋል። የቅድስት መንበር ፕሬስ ኀላፊ አባ ፌዴሪኮ ሎምባርዲ ለቫቲካን ሬድዮ በሰጡት ምስክርነት…

Read more: ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ከቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው ጋር ተገናኙ

Comments ()

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ማን ናቸው?

የተወለዱት እ.ኤ.አ. ታኅሳስ 1936 ዓ.ም. በአርጀንቲና ዋና ከተማ ቦነስ አይረስ ሲሆን እሳቸውን ጨምሮ ቤተሰቦቻቸው 5 ልጆች አሏቸው

- ወላጅ አባታቸው የባቡር መንገድ መሀንዲስ ነበሩ

- የአሁኑ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቺስኮስ የቀድሞው ሆርኼ ማሪዮ ቤርጎሊዮ የኬሚካል ምህንድስና ምሩቅ ሲሆኑ በኋላ ላይ ግን እ.ኤ.አ. በ1958 ዓ.ም. የJesuit (የኢየሱሳውያን) ማኅበርን የሴሚናሪ /ዘርአ ክህነት/ ማእከል ተቀላቅለዋል

- በ32 ዓመታቸው የኢየሱሳውያን ማኅበር ካህን ሆኑ

- በወጣትነት ዘመናቸው በመተንፈሻ አካላት ባጋጠማቸው ሕመም ምክንያት አንደኛው ሳንባቸው ሊወጣ ችሏል

- እ.ኤ.አ. በጥቅምት 1992 ዓ.ም. በብጹእ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዘመን ጵጵስናን ተቀብለው የቦነስ አይረስ ከተማ ረዳት ጳጳስ በመሆን አገልግለዋል...…

Read more: ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ማን ናቸው?

Comments ()

Subcategories

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።