Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 96

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 99

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$category_alias in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 102

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 141

"አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አግኝተናል!"

ዛሬ መጋቢት ፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. አመሻሹ ላይ በቫቲካን ከሚገኘው ሲስቲና ቤተ ጸሎት ጭስ ማውጫ ነጭ ጭስ መውጣቱ ለዓለም የአዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን መመረጥ ያወጀ ሲሆን ከዚያም ከአንድ ሰዓት በኋላ አካባቢ በተለመደው ሥርዓት በደብረ ቅዱስ ጴጥሮስ ሕንጻ መስኮት እጩ ከነበሩት 115 ካርዲናሎች ውስጥ 2/3ኛውን ደምጽ ማለትም ከ77 የምርጫ ድምጽ በላይ በማግኘት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ 265ኛው የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ በመሆን በዚህ መንበር ላይ ሆነው እንዲያገለግሉ የተመረጡት ማን እንደሆኑ ተገለጠ።

አዲስ የተመረጡት ር.ሊ.ጳጳሳት አርጀንቲናዊው የቦነስ አይረሱ ጳጳስ ካርዲናል ጆርጅ ማሪዮ ቤርጎሊዮ ሲሆኑ የ77 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ናቸው። በአዲሱ ጴጥሮሳዊ አገልግሎታቸውም ፍራንቼስኮ /ፍራንሲስ/ የሚል ሥያሜን የወሰዱ ሲሆን ከ1300 ዓመታት ወዲህም ከአውሮጳ ውጪ የሆነ ር.ሊ.ጳ. ሲመረጥ እርሳቸው የመጀመሪያው ናቸው። እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከኢየሱሳውያን ማኅበር ለዚህ ኀላፊነት የተመረጡ የመጀመሪያ ር.ሊ.ጳ. ናቸው። ተጨማሪ የሕይወት ታሪካቸውን ይዘን በሌላ ዘገባ እንመለሳለን። እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያኑን አሁንም በመልካም እረኝነቱ ይጎብኝልን ስለ ሰጠንም እረኛ ይመስገን!

Read more: "አዲስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አግኝተናል!"

Comments ()

ከሸገር 102.1 fm ራድዮ "መቆያ" ከሚለው የሰሞኑ ዝግጅት የተገኘውን የቅዱስ አባታችን ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛውን ሕይወት የሚዳስስ ምርጥ ዝግጅት ያድምጡ። ይህን ዝግጅት በሚያዳምጡበት ጊዜ አንዳንድ ጊዜ  ጳጳስ አሊያም ሊቀ ጳጳሳት የሚል ለቤኔዲክቶስ 16ኛው የተሰጠውን መጠሪያ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በሚል እንዲረዱት ይሁን። መልካም ማዳመጥ! ይህን አድራሻ ይጫኑት http://www.ethiocist.org/Audio/Benedict_16.mp3


Read more: የቅዱስ አባታችን ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛውን ሕይወት የሚዳስስ ምርጥ ዝግጅት ያድምጡ

Comments ()

ከቤኔዲክቶስ 16ኛው የአገልግሎት ማቋረጥ በኋላ የመጀመርያው የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ሰኞ ጥዋት በካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ መሪነት በቫቲካን ከተማ በጳውሎስ 6ኛው አደራሽ ተካሄደ፡፡ ከሰዓት በኋላም በአስራ አንድ ሰዓት ሁለተኛው ጉባኤ እንደሚካሄድ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክቷል፡፡ ክቡር አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅድስት መንበር የዜናና የሕትመት ክፍል ኃላፊና የቫቲካን ሬዲዮ…

Read more: ለር.ሊ.ጳ. ምርጫ ዝግጅት የመጀመሪያው የካርዲናሎች ጉባኤ ተካሄደ

Comments ()

የካቲት 4 ቀን 2005 ዓ.ም. - ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው የመንበረ ጴጥሮሳዊ አገልግሎታቸውን ከየካቲት 21 2005 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚያቋርጡ ዛሬ ጠዋት አስታወቁ።

በቫቲካን ለተሰበሰቡ ካርዲናሎች ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ካሰሙት ንግግር ውስጥ "በእግዚአብሔር ፊት በተደጋጋሚ ኅሊናዬን ከመረመርኩ በኋላ ከእድሜዬ እርጅና የተነሣ የመንበረ ጴጥሮስ ኀላፊነቴን ለመወጣት የሚያስችል ጥንካሬ እንደሌለኝ ርግጠኛ ድምዳሜ ላይ…

Read more: ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው የመንበረ ጴጥሮሳዊ አገልግሎታቸውን እንደሚያቋርጡ አስታወቁ።

Comments ()

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብ. አቡነ ብርሃነየሱስ የ2005  ዓ.ም. የጌታችን የልደት በዓል መልእክት


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

''እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ አዳኝ ተወልዶላችኃል፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው፡፡ ምልክቱም ይህ ነው፣ በመታቀፊያ ጨርቅ የተጠቀለለ ሕፃን በበረት፣ በከብቶች መመገቢያ ግርግም ውስጥ ተኝቶ ታገኛላችሁ''፡፡ (ሉቃስ 2፡11-12)

የተወደዳችሁ ምዕመናን…

Read more: ሁላችን በጌታችን ፍቅር ልንሸነፍ ይገባናል!

Comments ()

በቅርቡ የተገኘው የሰባት ዓመቱ ሕፃን ጆሴፍ ራዚንገር  /የአሁኑ ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው/ ለሕፃኑ ኢየሱስ የተጻፈ የገና ደብዳቤ ለቅዱስ ልበ ኢየሱስ ያላቸውን መንፈሳዊነትና ካህን የመሆን ምኞታቸውን ያሳያል፤ እንዲህ ይነበባል፡-

“ውድ ሕፃኑ ኢየሱስ፣ ለሕፃናት ደስታን ታመጣለህና ፈጥነህ ወደ ምድር ና! ለእኔም ደስታን አምጣልኝ። የጸሎት መጽሐፍ፣ አረንጓዴ የቅዳሴ አልባስና የኢየሱስ ቅዱስ ልብን ስዕል ብታመጣልኝ ደስ ይለኛል፤ ጥሩ ልጅም እሆናለሁ።

ሰላም ሁን! ጆሴፍ ራዚንገር


ሕፃኑ ጆዜፍ አረንጓዴ የቅዳሴ አልባስ የጠየቁበትን ምክንያት ካህኑ ታላቅ ወንድማቸው ሞንሲኞር ጆርጅ ራዚንገር ሲያስረዱ ጆሴፍና ወንድሞቻቸው እንደ ካህን በመሆን “እቃቃ” ይጫወቱ እንደነበረና የልብስ ስፌት ባለሙያ የነበሩት እናታቸውም የካህናት ዓይነት ልብስ በመስፋት ይተባበሯቸው እንደነበረ ገልጸዋል።

በደብዳቤው ውስጥ የተጠቀሰው ሌላው ነገር ደግሞ የኢየሱስ ቅዱስ ልብ ሲሆን ይህም ስእሉን መጠየቁ መሆኑንና የመላ ቤተሰቡ ልዩ መንፈሳዊነት እንደሆነ ታውቋል።

ይህ ደብዳቤ ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው ሬገንስበርግ ውስጥ የዩኒቨርስቲ መምህር በነበሩበት ጊዜ ይኖሩበት የነበረ ቤት እድሳት ሲደረግለት ሲሆን በእህታቸው ዘንድ ቆይቶ ይፋ የሆነውም ከአንድ ሳምንት በፊት ታኅሣሥ 9 ቀን ነው። ራዚንገር ይኖሩበት የነበረው ቤት በርሳቸው ስም ትንሽ ሙዚየም የተደረገ ሲሆን የር.ሊ.ጳ. ጸሐፊ እንዳሉት ር.ሊ.ጳ. በደብዳቤው መገኘት ደስ የተሰኙ መሆናቸውና ይዘቱም እንዳስፈገጋቸው ተነግሯል።

ምንጭ፡- http://www.ucatholic.com

 

Read more: በሰባት ዓመቱ ሕፃን ጆሴፍ ራዚንገር /የአሁኑ ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው/ ለሕፃኑ ኢየሱስ የተጻፈ የገና ደብዳቤ

Comments ()

ለአንድ ዓመት የሚቆየው "የእምነት ዓመት" በቅዱስ አባታችን ታወጀ

ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ከትላንት በስትያ ጥቅምት ፩ ፳፻፭ ዓ.ም. የእምነት ዓመት መክፈቻ፣ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ 50ኛው ዓመትና የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ ሰነድ እውን የሆነበትን 20ኛው ዓመት ዝክር ምክንያት በማድረግ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በጠቅላላ በ400 ብፁዓን ጳጳሳት፣ ፓትርያርካት፣ ካርዲናሎችና ካህናት…

Read more: መንፈሳዊ ምድረ በዳነት ባጠቃው ወቅታዊው ዓለም ዳግም ክርስቶስን ማወጅ

Comments ()

የር.ሊ.ጳ. የሰንበት መልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ

ውድ ውንድሞችና እኅቶች

የዛሬው እሁድ ወንጌል የቅዱስ ማርቆስ ምዕራፍ 9 ከቍ 38-41 ሆኖ ክርስቶስ ካከናወናቸው አንዱን አጋጣሚ የሚገልጥ እንደነገሩ አለፍ ሲል የተፈጸመ ቢሆንም ጥልቅ ምሥጢር የያዘ ክፍል ነው፣ ታሪኩ እንዲህ ነው፣ ወጣትና ቀናተኛ የነበረው ዮሐንስ ሐዋርያ የኢየሱስ ተከታይ ያልሆነ አንድ ሰው በኢየሱስ ስም…

Read more: የማይቃወመን እርሱ ከእኛ ጋር ነው!

Comments ()

መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ መካከል የሚደረግ ቀጣይ ውይይት ነው

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የእለተ ረቡዕ ኣጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ

ውድ ወንድሞችና እህቶች፧ ባለፉት ወራት ጸሎትን በሚገባ ለመማር፤ በብሉይ ኪዳን በሚገኙ ታላላቅ የጸሎት ምሳሌዎች በመመልከት እንዲሁም መዝሙረ ዳዊት፤ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክቶችና የዮሐንስ ራእይ በመቃኘት፤ ከሁሉ በላይ ግን ኢየሱስ ከሰማያዊ አባቱ ጋር የነበረው ግንኙነት መሠረታዊና አንድያ የጸሎት ምሳሌ ላይ በማተኰር በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን ተጉዘናል፣ እንደ እውነቱ ከሆነ በልጅነት መንፈስ ከሚያፈቅረው አባቱ ከእግዚአብሔር ጋር ጥልቅና የጋለ አንድነት ሊፈጥር የቻለው ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ የሆነው ክርስቶስ ብቻ ነው፣ ፍቅር በተሞላ ስሜት "አባ! አባታችን" ብለን ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው፣ እንደ ሐዋርያት እኛም ኢየሱስን "ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን" (ሉቃ 11፤1) በማለት ደጋግመን እንደጠየቅነው አሁንም እንጠይቀው፣

ከዚህ ሌላም ከእግዚአብሔር ግላዊ ግንኙነት ለመረዳትና ይህንን በጋለ መንገድ ለመኖር፤ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ አንደኛ ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስ መለመን እንዳለብን ተምረናል፤ ምክንያቱም "መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል"(ሮሜ 8፡26)፣

እዚህ ላይ በቅዱስ መጽሐፍ ተመርኩዘን ስለጸሎት ብዙ የትምህርተ ክርስቶስ ክፍለ ግዜዎች ካየን በኋላ "በመንፈስ ቅዱስ ለመታነጽ…

Read more: የእግዚአብሔር ሕዝብ በደም ትስስር በመሬትና በአገር ድንበር የቆመ አይደለም

Comments ()

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! 

"ሁሉም ነገር የተገኘው ከእርሱ፣ በእርሱና፣ በርሱ ስም ነው፤ ለዘለዓለም ክብር ለእርሱ ይሁን አሜን'' (ሮሜ 11፡ 36)

(ለማዳመጥ ይህን ጽሑፍ ይጫኑ) የተወደዳችሁ ምመናን

ክቡራን የቤተክርስቲያን አገልጋዮች

በሀገር ውስጥና እንዲሁም ከአገር ውጪ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖች"

በጎ ፍቃድ ያላችሁ ሰዎች በሙሉ

ለመላው የአገራችን ህዝቦችና ለካቶሊካውያን ምዕመናን ወገኖች በሙሉ ከሁሉ በማስቀደም እንኳን ለ2005 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት አዲሱ ዓመት የሰላም የጤናና የፍቅር እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን በራሴና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ስም አቀርብላችኃለሁ፡፡

ዛሬ የምናከብረው በዓል የአዲስ ዓመት በዓል ነው፡፡ዓመታት የእግዚአብሔር ናቸው በየዓመቱ የሚሰጠን ጊዜ ከእግዚአብሔር ምህረትና ፍቅር ነው፡፡ የሚሰጡንም ለእኛ በረከትና ለእርሱ ክብር ነው፡፡መዝሙረኛዉ ዳዊት ''በቸርነትህ ዓመትን ትባርካለህ፤ ምድረ በዳዉም ስብን ይጠግባል'' (መዝ 64(65)11) በማለት ለእግዚአብሔር አምላኩ ይቀኛል፡፡ ሰውም በተሰጠው ስጦታ በመጠቀምና ከእርሱም ላይ በመጨመር የእግዚአብሔርን ክብር ማመስገኛ አንዱ መንገድ ነው፡፡

ይህን አዲስ ዓመት ስንቀበል እግዚአብሔር ስላደረገልን ነገር በማመስገን ነው፡፡ በአንጻሩም ምንልባት አንዳንዶች ደስታ ላይኖራቸውና ለምሥጋና ላይበቁ ይችላሉ፡፡ እንደምናውቀው…

Read more: ሊቀ ጳጳሳት ብ. አ. ብርሃነየሱስ የ2005 ዓ.ም ርእሰ ዐዉደ ዓመትን በማስመልከት ለምእመናን ያስተላለፉት መልእክት፡፡

Comments ()

በዛሬው እለት ር.ሊ.ጳ. ቤኔዴክቶስ 16ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ብራሰልስ በሚገኝ ሆስፒታል ሲታከሙ ቆይተው ባለፈው ሰኞ ምሽት መሞትን በተመለከተ ለአገሪቱ ርእሰ ብሔር ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የኀዘን መግለጫ ላኩ። በቴሌግራም የተላከው መልእክትም የሚከተለው ነው።

ለየኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሳዊ ሪፐብሊክ ርእሰ ብሔር ክቡር ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፡-

የጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊን ያልተጠበቀ ሞት በመስማታቸው ቅዱስነታቸው ር.ሊ.ጳ. ቤኔዴክቶስ 16ኛው ለአቶ መለስ ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ልባዊ የኀዘን መግለጫቸውን ያስተላልፋሉ። የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ብዙ ዓመት መሪነታቸውን በማስታወስ ቅዱስ አባታችን ዘላለማዊ እረፍትን ያገኙ ዘንድ ይጸልዩላቸዋል። ለቤተሰቦቻቸውና እርሳቸውን በማጣታቸው ላዘኑት ሁሉ የሁሉን ቻይ አምላክ ቡራኬ መጽናናትንና ተስፋን ይሰጣቸው ዘንድ ጸልየዋል።

ብጹእ ካርዲናል ታርቺዚዮ ቤርቶኔ የአገረ ቫቲካን ጸሐፊ።

ምንጭ፡ http://www.news.va

Read more: ር.ሊ.ጳ. ቤኔዴክቶስ 16ኛው ለጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ህልፈት የኀዘን መግለጫ ላኩ።

Comments ()

በትላንትናው እለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብጹእ ወቅዱስ ጳውሎስ በ76 ዓመት ድሜያቸው በአዲስ አበባ ከዚህ ዓለም በሞት መለየትን ምክንያት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው የሐዘን መግለጫ ቴሌግራም ለቤተ ፓትሪያርክ ማስተላለፋቸውን የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት የሓዘን መግለጫ መልእክት ብጹእ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ጳውሎስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል የጋራ ውይይት እንዲደረግ ያበረከቱትን ዓቢይ አስተዋጽዖ ጠቅሰው፣ እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ቫቲካን ተካሂዶ በነበረው የመላው አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በእንግድነት ተሳትፈው ያሰሙትን ንግግር በማስታወስ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያት ላዘኑት ሁሉ ቅርብ በመሆን ነፍሰ ኄር ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ጳውሎስን እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸው እንደሚጸልዩ መግለጣቸውን የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ፓትሪያርክ ብጹእ ወቅዱስ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ስርዓትም አዲስ አበባ በሚገኘው መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. እንደሚፈጸም ለማወቅ ተችሏል።

ፓትሪያርክ ብጹእ ወቅዱስ ጳውሎስ እ.ኤ.አ. በ2005 ዓ.ም. የብጹእ ዮሐንስ ዳግማዊ ሥርዓተ ቀብር ጊዜ በቫቲካን ተገኝተው የተሳተፉ ሲሆን በቅርቡም በአዲስ አበባ የምሥራቃውያት ኦርቶዶክስና ምሥራቃዊ ሥርዓት ካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የተደረገ ስብሰባን አስተናግደው እንደነበር ይታወሳል።

ምንጭ፡ ራድዮ ቫቲካን , http://www.news.va , ETV

Read more: ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያት የሐዘን መግለጫ መልእክት አስተላለፉ

Comments ()

Subcategories

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።