Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 96

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 99

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$category_alias in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 102

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 141

www.catholicnewsagency.com - ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛው በዚህ ወቅት የእረፍት ጊዜያቸውን በሚያሳልፉበት ከሮም ውጭ በሚገኘው ካስተል ጋንዶልፎ ሆነው በናዝሬቱ ኢየሱስ ላይ የሚጽፉትን መጽሐፍ ሦስተኛ መድበል ጽፈው መጨረሳቸውን ቫቲካን የማስታወቂያ ቢሮ ገለጸ።

ይህ መድበል በክርስቶስ የሕፃንነት ሕይወት ላይ የሚያተኩር መሆኑ ሲገለጽ የዚህ መጽሐፍ ሁነኛ እትም በጀርመንኛ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ወደተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎም ላይ ይገኛል፤ ይህ በዐበይት ቋንቋዎች የመተርጎሙ ሂደት ሲጠናቀቅም ለሕትመት እንደሚበቃ ታውቋል።

አዲሱ መድበል "የናዝሬቱ ኢየሱስ" በሚል ርእስ በ1999 ዓ.ም. የታተመውና በ2003 ዓ.ም. "የናዝሬቱ ኢየሱስ - ከኢየሩሳሌም መግባት እስከ ትንሣኤ" በሚል ርእስ የወጣው የሁለቱ ሥራዎቻቸው ቀጣይ ሦስተኛ መጽሐፍ ነው። ሁለቱ መጻሕፍታቸው በሰባት ቋንቋዎች በወረቀትና በኤሌክትሮኒክ መልኩ ለሕዝብ የቀረቡ ሲሆን ከአንድ ሚሊዮን ቅጂዎች በላይ መሸጣቸው ታውቋል።

በዚሁ በእረፍት ጊዜያቸው ይህን መጽሐፍ ከማጠናቀቅ ባሻገርም ር.ሊ.ጳ. ከመስከረም 4 እስከ 6 ድርስ በሊባኖስ ለሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝትም ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናቸውና ምናልባትም ከዚህ የመጽሐፍ ሥራቸው በኋላ አራተኛ የሚሆነውን ለመላዪቱ ቤተ ክርስቲያን የሚሆን አንድ የእምነት አንቀጽን የሚመለከት መልእክት Encyclical letter ሊያዘጋጁ እንደሚችሉ ይገመታል።

Read more: ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛውና የእረፍት ጊዜያቸው

Comments ()


ወንድም ዮሴፍ ፍቅረማርያም
ወደ መንዲዳ ዘርአ ምንኩስና የገቡት በ1989 ዓ.ም. ሲሆን ከዚያም በኋላ የተመክሮ ሕይወትን አድርገው ሕይወታቸውን እንደ ሲታዊ መነኩሴ በመሐላ ለእግዚአብሔር በመስጠት የፍልስፍናና የነገረ መለኮት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በመፈጸም ራሳቸውን ለክህነት አገልግሎት ሕይወት ሲያዘጋጁ ቆይተዋል፡፡ እነሆም በእግዚአብሔር ጸጋ በብፁእ አባታችን አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ማቴዎስ እጅ ብዙ ካህናት፣ ደናግላን፣ ምእመናን፣ ቤተሰቦችና ወዳጆች…

Read more: የክህነት የብር ኢዮቤልዩና ሢመተ ዲቁና በማኅበረ ሲታውያን

Comments ()

ከቅድስት መንበር (ቫቲካን) በተገኘው ፈቃድ መሠረት በሲታውያን ማኅበር ጠቅላይ አበምኔት ኀላፊነት በኢትዮጵያ የሚገኘው የሲታውያን ገዳም በአዲስ መልክ የተዋቀረ የመነኮሳን አስተዳደር ሂደት ጀመረ።

የሲታውያን ማኅበር ጠቅላይ አበምኔትና በዚህ ውሳኔ መሠረት የቅዱስ ዮሴፍ ገዳም ሾላ የበላይ ኀላፊ የሆኑት ማውሮ ጁዜፔ የማኅበሩ አስተዳዳሪ የሆኑትን አባ ሜይንራድ ጆዜፍ ቶማንን በመወከል ወደ ኢትዮጵያ ልከው ሰኔ ፭ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በቅዱስ ዮሴፍ ገዳም ኀላፊ መነኮሳት አባቶች ተሰባስበው ውሳኔው ተግባራዊነቱን ጀምሯል። በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ የሚገኘው የቅዱስ ዮሴፍ ገዳም በክቡር አባ ባዘዘው (ወልደ ገብርኤል) ግዛው አባታዊ ኀላፊነት የተቀሩት ገዳማት ማእከል እንዲሆን ተደርጓል።

በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሳእናና በጎንደር የሚገኙት አራት የሲታውያን ገዳማት ስድስት በተመካሪ ደረጃ ላይ ያሉ መነኮሳትን አካትቶ በጠቅላላ ሠላሳ ሦስት መነኮሳት ያሉት ሲሆን በሥሩም ከመዋእለ ሕፃናት እስከ ተግባረ እድ ድረስ የሚያካትቱ በድምሩ ከአምስት ሺህ በላይ ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ አብያተ ትምህርትን ያስተዳድራል፤ በቁምስና ደረጃም ሐዋርያዊ አገልግሎትን በሚመለከት በአራቱ ገዳማት አምስት ቁምስናዎችን የሚያገለግል ማኅበር ነው።

የሲታውያን ገዳም በኤርትራና በኢትዮጵያ እንዴት እንደተጀመረና ከ ፶፮ ዓመታት በፊት የመጀመርያው ገዳማችን የመንዲዳ ደብረ ጽንሰታ ዘሲታውያን ገዳም በምን ዓይነት ሁኔታ እንደተገደ ይበልጥ ለመረዳት ከታች ያለውን ገጽ እንዲጎበኙት እየጋበዝን ለሕይወታችን ቅድስናና ለሐዋርያዊ ሥራ አበርክቷችን በጸሎታችሁ ታስታውሱን ዘንድ አደራ እንላለን። http://www.ethiocist.org/index.php?option=com_content&;view=article&id=284&Itemid=669

Read more: የሲታውያን ገዳም በኢትዮጵያ አዲስ መዋቅር አገኘ

Comments ()

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

ክቡራን ምዕመናን፡-

በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የምትገኙ ክቡራን የቤተክርስቲያን አገልጋዮችና በጎ ፍቃድ ያላችሁ ወገኖች ሁሉ፣


ከሁሉም አስቀድሜ የ2004 ዓ.ም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና በራሴ ስም እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ እላለሁ፡፡ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ምህረትንና ሰላምን ለአደረግልን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፡፡

''በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን በታላቅ ምህረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት የሆነ አምላክ ይመስገን'' (1 ጴጥ 1፡ 3-4)፡፡…

Read more: የብ. አቡነ ብርሃነየሱስ የትንሣኤ መልእክት

Comments ()

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ልበ ኢየሱስ የካቶሊክ መንበረ ጥበብ (ዩኒቨርስቲ) 88ኛው ቀን ምክንያት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዝዮ በርቶነ ፊርማ የተኖረበት ባስተላለፉት መልእክት፣ የክርስትናው እምነት የባህል እርሾ፣ ለመግባባትና ለውህደት ብርሃን፣ የእድገት በጠቅላላ ለሁሉም ለሐቀኛው ሰብአዊ ጥቅም መረጋገጥ ለሚያግዘው አውንታዊው እምቅ ኃይል ግፊት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የአንዲት አገር ተስፋ በወጣት ትውልድ ልብ ዘንድ መሆኑ አብራርተው፣ ኃሴት እና ተስፋ የተሰየመው የሁለተኛው ቫቲካን የውሳኔ ሰነድ ዋቢ በማድረግ፣ "የሰብአዊ መጻኢ መቀመጫው ለነገው ሕይወት ተረካቢው ትውልድ የሕይወትና የተስፋ ምክንያት የማስተላለፍ ብቃት ባላቸው ዜጎች እጅ ነው።…

Read more: የተሟላ የሰብአዊነት አድማስ

Comments ()

"እንግዲህ አሁን በፍፁም ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ ጹሙ አልቅሱ እዘኑ" /ኢዮ 2፡12/

የተከበራችሁ ምዕመናን ከሁሉም አስቀድሜ እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርባ ጾም

ደረሳችሁ በማለት በክቡራን ቆሞሳችሁ በኩል ይህን ሐዋርያዊ መልዕክቴን ላስተላልፍላችሁ እወዳለሁ፡፡

የጾም ጊዜ ከእግዚአብሔር የተሰጠን ፀጋና በረከት ነው፡፡ ከዚህም ጋር ራሳችንን ከክፉ ነገር በመጠበቅ በመግዛትና በመታጠብ በንሰሐ በመመለስም ወደ እግዚአብሔር ደጅ የምንጠናበትና እርሱንም አቤቱ ማረን ይቅር በለን እያለን ወደ እርሱ የምንበረከክበትና ምህረቱን ለማግኘት የምንዘጋጅበት ነው፡፡…

Read more: የብ.አ. ብርሃነየሱስ የ2004 ዓ.ም. የአርባ ጾም መልእክት

Comments ()

በዓለም አቀፍ ደረጃ የካቶሊክ ደናግላን ቁጥር ሲቀንስ በአንፃሩ ግን የካህናት ቁጥር እድገት አሳይቷል

እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. በዓለም ላይ 1 ቢሊየን 181 ሚሊየን የነበረውየካቶሊካውያን ቁጥር በ2010 ዓ.ም. 15 ሚሊየን በመጨመር ወደ 1 ቢሊየን 196 ሚሊየን ከፍ በማለት የ1.3 ከመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት በዓለም ላይ የተጠመቁ ካቶሊኮች አኀዝ በቋሚነት 17.5 ከመቶ አካባቢ ይገኛል፡፡

የካቶሊኮች ቁጥር ከአጠቃላይ የሕዝብ ብዛት አንጻር ሲታይ ከአህጉር አህጉር ይለያያል፡፡ በደቡብ አሜሪካ 28.54 ከመቶ የነበረው ወደ 28.34 ከመቶ ዝቅ ሲል እንደዚሁም በአውሮፖ ከ25.05 ከመቶ ወደ 23.83 ከመቶ ወርዷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ግን ከ15.15 ከመቶ ወደ 15.55 ከመቶ በምሥራቅ እስያም እንደዚሁ ከ10.47 ከመቶ ወደ 10.87 ከመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

የጳጳሳት ቁጥር ከ5,065 ወደ 5,104 አድጓል፡፡ ይህም ከመቶ የ0.77 እድገት ማለት ነው፡ይህም በአፍሪካ 16 አዳዲስ ጳጳሳት፣ በአሜሪካ 15 እንዲሁም በእስያ 12 ሲሆን በአውሮፓ ግን በትንሹም ቢሆን ቀንሷል፡፡ ይኸውም ከ1, 607 ወደ 1, 606 እንደዚሁም በኦሽንያ ከ132 ወደ 129 ዝቅ ብሏል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ የካህናት ቁጥር ወጥ የሆነ እድገት በማሳየት ላይ ይገኛል። በ2010 ዓ.ም. የካህናት ቁጥር 412, 236 ነበር። ከነዚህም ውስጥ 227, 009 የሰበካ ካህናት (diocesan priests) ሲሆኑ 135, 227 የማኅበራት ካህናት (Religious priests) ነበሩ፡፡ ይህ የካህናት ብዛት በ2009 ዓ.ም. 410, 593 የነበረ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 275, 542 ሰበካውያን እና 135, 051 ደግሞ የማኅበራት ካህናት ነበሩ፡፡…

Read more: የካህናት ቁጥር እድገት አሳየ

Comments ()

የላቲን ሥርዓት በምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ወደ በዓለ ትንሣኤ ዘእግዚእነ የሚያሸጋግረው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰሙነ ሕማማት ባለፈው ሳመንት የተከበረ ሲሆን፣ በጸሎተ ሐሙስ የነበረው ሥርዓትና የቅዱስ አባታችን ስብከትእንደሚከተለው ቀርቧል።

ጸሎተ ሐሙስ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የቅብአ ቅዱስ ሥርዓት መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚፈጸምበት ዕለት ሲሆን፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቅዱስ ቁርባን እና ምሥጢረ ክህነት ምሥረታን በማረጋገጥ ለደቀ መዛሙርቱ "እርስ በእርሳችሁ እንድትዋደዱ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ" (ዮሐ. 13፣ 34) በማለት አዲስ ትእዛዝ የሰጠበትና ቋሚ ሥርዓተ ሊጡርጊያ የሚፈጸምበተ ዕለት ሲሆን፤ በዚህ የቅዱስ ቁርባን ምሥረታ ማረጋገጫ የሆነው የጌታ የመጨረሻ እራት ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ ጌታችን ለአርድእቱ የፈጸመው ሥርዓተ ሕጽበተ እግር ምልክት በተለይ በተራ ምሳሌ የሚፈጸምበት ዕለት ነው።…

Read more: በቃሉ የተነካ ልብና አእምሮ

Comments ()

 

ራድዮ ቫቲካን - ቫቲካን በሚገኘው የሲኖዶስ አዳራሽ እ.ኤ.አ. ቅዳሜ ከጥቅምት 20 ቀን እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2011ዓ.ም አለም ዓቀፍ የለመከላከያ ኃይል አባላት ሐዋርያዊ አገልግሎት ኀላፊ ብፁዓን ጳጳሳት እና ለመከላከያ ኃይል አባላት የነፍስ አባቶች ጉባኤ መካሄዱ ሲገለጥ፣ ይህ ለመከላከያ ኃይል አባላት የሚሰጠው ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚመለከት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 24 ቀን 1986 ዓ.ም ይፋ ያደረጉት የመከላከያ ኃይል አባላት መንፈሳዊ እንክብካቤ ሐዋርያዊ መመሪያ ድንጋጌ 25ኛው ዓመት በሚዘከርበት በአሁኑ ወቅት የተከናወነ በመሆኑም የጉባኤው ሂደት ለየት እንዲል እንዳደረገው ቅዳሜ ጧት ለተጋባዦች ቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ጸሎት መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ባሰሙት ስብከት ማስታወሳቸው ተገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ለተጋባዦች ያስተላለፉት ምዕዳን…

Read more: የእግዚአብሔርን የፍቅር ትእዛዝ መከተል

Comments ()

ራድዮ ቫቲካን - ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛው የዘንድሮውን የኤውሮጳውያን ዓመት በአፍሪቃ በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞ፣ በጣልያን አገር በሚያደርጉት ሐውጾተ ኖልዎ እና ሌሎች በመንበረ ጴጥሮስ በሚደረጉ ሥርዓተ አምልኮአዊ አገልግሎቶች እንደሚፈጽሙት ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክቷል። ይህንን ያመለክቱት የቅዱስነታቸው የሥርዓተ አምልኮ ተግባሮች መሪ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጒዶ ማሪኒ ናቸው።

 

ብፁዕነታቸው በሰጡት ማብራርያና በቅዱስነታቸው መርኃ ግብር መሠረት…

Read more: የር.ሊ.ጳ የጥቅምትና የኅዳር ወሮች ፕሮግራም

Comments ()

ቫቲካን ራድዮ - ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛው በትውልድ ሀገራቸው ጀርመን የአራት ቀናት ሐዋርያዊ ጉብኝት የሚታወስ ሲሆን ቅድስነታቸው ከመስከረም 22 ቀን እስከ 25 እ.ኤ.አ. ጀርመን ላይ በሚቆዩበት ጊዜ የተለያዩ ሀገረ ስብከቶችን እንደሚጎበኙና ከሀገሪቱ መንግስት የበላይ ባለስልጣናትም ጋር እንደሚገናኙ መርሃ ዑደታቸው ያመለክታል ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ ሐዋርያዊ ዑደት የሚካሄድባቸው የጀርመን ሀገረ ስብከቶች ርእሰ ከተማ በርሊን፣ ኤርፉርት፣ ፍራይቡርግ እና ኤትዘልስ ባኽ መሆናቸው ታውቋል።
የጀርመን ሕዝብ ብዛት 82 ሚልዮን ሲሆን ከዚህም ውስጥ 25 ሚልዮኑ ካቶሊካውያን መሆናቸው ይታወቃል። ቅዱስነታቸው በቡንደስታግ በጀርመን ፓርላማ ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉም የጀርመን ሐዋርያዊ ዑደታቸው መርሃ ዑደት ያሳያል።
ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ከተሰየሙ ከ2005 እ.ኤ.አ. በኋላ የትውልድ ሀገራቸው የሆነችውን ጀርመንን ሲጐበኙ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ የሚታወስ ነው።
የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛው የጀርመን ሐዋርያዊ ዑደት እግዝአብሔር ባለበት ቦታ መጻኢ አለ ሕይወት አለ በሚል መሪ ቃል እንደሚከናወን የቫቲካን መግለጫ አስታውቋል።  በጀርመን የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል አምባሳደር ብፁዕ አቡነ ጂ ክላውደ ፐሪሰት እንዳመለከቱት፡…

Read more: እግዚአብሔር ባለበት ቦታ መጻኢ ሕይወት አለ

Comments ()

የር.. ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ

ቫቲካን ራድዮ - ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፡- ገና በፍልሠታ በዓለ ብርሃን እያሸበረቅን ነው፣ ይህ በዓል የተስፋ በዓል መሆኑን ገልጨ ነበር። እመቤታችን ድንግል ማርያም መንግሥተ ሰማያት ገባች፣ ለእኛም መድረሻችን ይሄ ነው፣ እኛ ሁላችን መንግሥተ ሰማያት መግባት እንችላለን፣ ዋነኛው ጥያቄ እንዴት? የሚለው ይሆናል፣…

Read more: ፍልሠታ - የተስፋ በዓል

Comments ()

Subcategories

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።