Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 96

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 99

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$category_alias in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 102

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 141

መጋቢት 2 2003 ዓ.ም. “ኢየሱስ ናዝራዊ” የተሰኘው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ሁለተኛ መድበል መጽሐፍ የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ ቅዱስ ማኅበር ተወካይ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦውሌት፣ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ፕሮፈሶር ክላውዲዮ ማግሪስ እና የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ጉዳይ ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ ለንብባብ በቅቷል።…

Read more: የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ . “ኢየሱስ ናዝራዊ” ሁለተኛ ተከታታይ መጽሓፍ

Comments ()

ቫቲካን ራድዮ - መጋቢት 2 ቀን 2003 ዓ.ም. “ኢየሱስ ናዝራዊ” የተሰኘው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ሁለተኛ መድበል መጽሐፍ የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ ቅዱስ ማኅበር ተወካይ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦውሌት፣ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ፕሮፈሶር ክላውዲዮ ማግሪስ እና የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ጉዳይ ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ ለንባብ በቅቷል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. “ኢየሱስ ናዝራዊ” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሐፍ  ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት ለሚፈልግ ሁሉ የሚጠቅም መሆኑ ሲገለጥ፣…

Read more: የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ . “ኢየሱስ ናዝራዊ” ሁለተኛ መድበል መጽሐፍ

Comments ()

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛው ትላንትና ጧት በቫቲካን የሪፐብሊካዊት ሊባኖስ ርእሰ ብሔር ሚሸል ስለይማንን ተቀብለው እንዳነጋገሩ የቅድስት መንበር የማህተምና ዜና ክፍል ካሰራጨው መግለጫ መረዳት ተችሏል። በሊባኖስ በሙስሊሞች እና በማኅበረ ክርስትያን መካከል ያለው ሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ለአገሪቱ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በዓለማችን ክርስትያኖች እና ሙስሊሞች በነጻነት እና ተከባብሮ መኖር የሚል ክቡር መልእክት መሆኑን ቅዱስ አባታችን በመግለጥ፣ ይህን እውነታ ለማረጋገጥ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራ ውይይት እና ትብብር ዘወትር እጅግ አስፈላጊ መሆኑንም አመልክተዋል።

የሃይማኖት መሪዎች እና የመንግሥት የበላይ አካላትና ባለ ሥልጣናት የሕዝባቸውን ኅሊና ለሰላም እና ለእርቅ በማነጽ በሊባኖስ በጉጉት የሚጠበቀው መረጋገት እና ሰላም የሚደግፍ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ፈታኝ ሁኔታዎችን የሚቋቋም መንግሥት እንዲጸና ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል የሚል መልእክት ቅዱስ አባታችን ማስተላለፋቸውን የቅድስት መንበር የማኅተም እና ዜና ክፍል መግለጫ አስታወቋል።
በመጨረሻም በተካሄደው ግኑኝነት ስለ መካከለኛው ምሥራቅ እና በአሁኑ ወቅት…

Read more: ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት

Comments ()

www.ewtn.com - በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. ከ 1999 ዓ.ም. ጋር ተነጻጽሮ የ5 ሺህ አዲስ ካህናት ቁጥር ብልጫ መመዝገቡን ከቅድስት ወንበር የወጣው አኀዛዊ ዘገባ ገለጸ።

ዘገባው በሚያሳየው መሠረት ከ11 ዓመታት በፊት 405, 009 የነበረው የካህናት ቁጥር አምና 410,593 ሲሆን የሰበካ ካህናት ቁጥር በ10 ሺህ ሲጨምር የማኅበራት ካህናት ቁጥር ደግሞ በ5 ሺህ መቀነሱ ታውቋል።

በሰሜን አሜሪካ አውሮፓና ውቅያኖሳውያን ሀገሮች (አውስትራሊያና በዙሪያዋ የሚገኙ ደሴታማ አገሮች) የሰበካም ሆነ የማኅበራት ካህናት…

Read more: የካህናት ቁጥር እድገት አሳየ

Comments ()

ጥር 8 ቀን 2003 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሚገኘው በቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ሁለት የሲታውያን መነኮሳን፤ ማለትም ዲያቆን ሰሎሞን (ተሻለ) ንማኒ ምስጢረ ክህነትን እንዲሁም ወንድም ኃይለገብርኤል (ዓለማየሁ) ነጋሽ ሢመተ ዲቁናን በብፁዕ አባታችን አቡነ ልሳነ-ክርስቶስ ማቴዎስ እጅ ተቀበሉ፡፡

በዕለቱ ከጠዋቱ 1፡30 ላይ ብፁዕ አባታችንና ከሃያ አምስት የሚበልጡ ካህናት በታላቅ ሥነ ሥረዓት በመዘምራን ታጅበው ለሢመት በተዘጋጁት መነኮሳን ቤተሰቦችና በብዙ ምእመናን ወደሞላው ቤተክርስቲያን ከገቡ በኋላ መስዋዕተ ቅዳሴው ተጀመረ፡፡ ቅዳሴው በድምቀት እስከ ወንጌል ቀጥሎ ብፁዕ አባታችን ምስጢረ ክህነትንና ሢመተ ዲቁናን ከሰጡ በኋላ ባሰሙት ስብከተ ወንጌል እነዚህ የቤተ-ክርስቲያን ማዕረጋት ለምእመናን ያላቸውን የአገልግሎት ሚና በሰፊው በማስረዳት ለዚህ አገልግሎት የተመረጡ ሰዎች  የእረኝነት ተልእኮአቸውን ከመስዋዕትነቱ ጭምር በጥልቀት ተረድተው ወደ ኋላ ሳይሉ የክርስቶስ ምስክሮች መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ቀጥሎም ወጣቶች ለጥሪያቸው ተገቢ መልስ መስጠት እንዲችሉ የምእመናን ጸሎትና የወላጆች ክርስቲያናዊ ኩትኮታ ወሳኝ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡

Read more: ምስጢረ ክህነትና ሢመተ ዲቁና በገዳመ ሲታውያን

Comments ()

የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እሑድ ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በቅዱስ ዮሓንስ እጅ የተጠመቀበትን ዕለት አክብራ ውላለች። በዚህ ዓቢይ በዓል ሁሌ በየዓመቱ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት ለሕፃናት እና የክርስትና እምነት ለሚቀበሉ ምሥጢረ ጥምቀት የምትሰጥበት ዕለትም ጭምር መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ትላንትና 14 ሕፃናት ወንዶችና 7 ሕፃናት ሴቶች በደብረ ቅዱስ ጴጥሮስ  በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው መጠመቃቸውን የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስስ 16ኛው እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. ለበዓለ ጥምቀት ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ በመምራት ባሰሙት ስብከት፣ የምንኖርበት ዘመን የሞት ባህል የተንሰራፋበት የሆነው፤ የታጠረ የተደበቀ የተደናገረ ሕይወት የሚኖርበት ጸረ ባህል እና ከተለያዩ ችግሮች ለማምለጥ ሲባል ለተለያዩ አንደንዛዥ እጽዋት እጅ የሚሰጥበት፣…

Read more: በዓለ ጥምቀት ዘእግዚእነ

Comments ()

ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው የጌታችንን ልደት በዓል ምክንያት በማድረግ በቢቢሲ ሬድዮ ለመጀመሪያ ጊዜ መልእክት ማስተላለፋቸው ተገለጠ። በመልእክታቸውም ለሕሙማን፣ ለአረጋውያንና በማንኛውም ዓይነት ችግር ውስጥ ለሚገኙ ሁሉ እንደሚጸልዩ አሳውቀው፤ በቅርቡ በእንግሊዝ አገር አድርገውት የነበረውን ጉብኝት በታላቅ ፍቅር እንደሚያስታውሱትና ይህን የገና መልእክታቸውን ለሚያዳምጡ ሁሉ ዳግም መልካም ምኞት ለመግለጽ በመቻላቸውም ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

"በስኮትላንድ፣ ኢንግላንድና ዌይልስ የምትገኙና የእንግሊዘኛ ተናጋሪ አገር ወዳጆቼ ሆይ!…

Read more: እግዚአብሔር ዘወትር ያስደምመናል!

Comments ()

ለገና በዓል ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄዱትን ምዕመናን ከጥቃት ለመከላከል የኢራቅ መንግሥት በባግዳድና በሞሱል በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዙሪያ እስከ አሥር ጫማ (3 ሜትር አካባቢ) የሚደርሱ ከፍታ ያላቸውን የአርማታ አጥሮችን እየገነባ ነው፡፡ ይህንን እርምጃ ሊወስድ የቻለው ከፊታችን ያለው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ጋር ተያይዞ እየጨመረ ለመጣው በክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እንደታሰበ ለሚያመለክቱ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ የካቶሊክ የዜና ወኪል /CNA/ ከኢራቅ ባግዳድ ዘግቧል፡፡

በተለምዶ እንደነዚህ ያሉ ክብረ በዓላት በአዳራሽና በመናፈሻ ቦታዎች የሚካሄዱ ዝግጅቶችን የሚያካትቱ ሲሆን ዘንድሮ ግን…

Read more: በኢራቅ አብያተ ክርስቲያናት ዙሪያ ትላልቅ ግንቦች እየተገነቡ ነው

Comments ()

 

የሃይማኖት ነጻነት የሰላም መንገድ ነው በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ 44ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን መልእክት ማስተላለፋቸውን የቅድስት መንበር የዜና እና የኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።
እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን የሰላም ቀን በመባል በሚታሰብበት ዕለት በየዓመቱ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት እንደሚያስተላልፍ የሚታወቅ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው ዘንድሮ ለሚከበረው 44ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን የሃይማኖት ነጻነት የሰላም መንገድ ነው በሚል ርእስ ሥር የሚያስተላልፉት መልእክት ትላንትና በቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል የሰላም እና የፍትህ ጳጳሳዊ ምክር ቤተ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲላን ቱርክሶን በተገኙበት መድረክ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቶበት ይፋ ሆነዋል።
ቅዱስነታቸው የሰላሙን መልእክት በዓለማችን…

Read more: “የሃይማኖት ነጻነት የሰላም መንገድ ነው” - የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. መልእክት ለዓለም አቀፍ የሰላም ቀን

Comments ()

 

ራድዮ ቫቲካን - ቅዱስነታቸው በታላቋ ብሪታንያ ያደረጉትን የ4 ቀን ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ትላንትና ወደ ቫቲካን ተመልሰዋል።
ሓዋርያዊ ጉብኝቱ እጅግ ማራኪና ስኬታማ እንደነበረና ሂደቱንም በሙሉ በአካል በብዙ ሺ የሚቆጠር ሕዝብ  እንደተከታተለው፤ እንዲሁም በቴሌቪዥን በኢንተርኔትና በሬድዮም በቀጥታ በብዙ ሚልዮን የሚቈጠር ሕዝብ እንደተከታተለው ብዙ የብዙኃን መገናኛ ገልጠዋል።
ቅዱስነታቸው  ቅዳሜ ዕለት በሃይድ ፓርክ ለንደን ከተማ ውስጥ ከ200 ሺ በላይ በሚሆኑ ምእመናን ታጅበው የካርዲናል ኒውማን የብጽዕና ሥርዓት የዋዜማ ጸሎትን ጥልቅ በሆነ መንፈስ ኣሳርገዋል።
በማግስቱ ጠዋትም ወደ ዊምብልዶን ፓርክ ከተጓዙ በኋላ…

Read more: የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የታላቋ ብሪታንያ ሐዋርያዊ ጉብኝት በሰላም ተፈጸመ

Comments ()
ራድዮ ቫቲካን- ክርስትና የሚያበስረው ደኅንነት የምንወደውን ዘለዓለማዊ ሕይወት እንጂ የማይጨበጥ ደኅንነት ኣይደለም
ቅዱስ ኣባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ ትናንትና ረፋድ ላይ ለዕረፍት ከሚገኙበት ካስተል ጋንደልፎ ሓዋርያዊ አዳራሽ የመልኣከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ‘እመቤታችን ድንግል ማርያም እንደ ክርስቶስ ልጇ ሞትን አሸንፋ በነፍስዋና በሥጋዋ በሁለመናው ሰማያዊ ክብር እንደተጐናጸፈች እናምናለን’ ሲሉ በላቲኑ ሥርዓተ ኣምልኮ ከ5 ቀናት በፊት የተዘከረውን የፍልሠታ በዓል የተመለከተ ትምህርት ሰጥተዋል።
የፍልሠታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚከተለዉን ስብከት ሰብከዋል።…

Read more: ፍልሠታ ለማርያም

Comments ()

ራድዮ ቫቲካን - እሑድ እኩለ ቀን ላይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎትን ሲያሳርጉ ባሰሙት ስብከት፣ የእንተ ላእለ ኵሉ (ካቶሊካዊት) ቤተ ክርስያን ካህናት በሰው ልጅ ታሪክ ለመንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ኅዳሴ መረጋገጥ የደረሷቸው መጻሕፍት፣ የሰጡት አብነት እና አስተዋጽኦ የማይካድ ብቻ ሳይሆን የሚደነቅ መሆኑን   አመልክተዋል።

በመቀጠልም ለአንድ ዓመት በኵላዊት…

Read more: “ካህን ለቤተ ክርስትያን እና ለዓለም ጸጋ ነው”

Comments ()

Subcategories

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።