Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 96

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 99

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$category_alias in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 102

Notice: Undefined property: Joomla\CMS\Categories\CategoryNode::$introtext in /web/htdocs/www.ethiocist.org/home/plugins/content/spcomments/spcomments.php on line 141

ራድዮ ቫቲካን -  ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛው ከትላንትና በስትያ ለቆጵሮስ ውሉደ ክህነት፣ ገዳማውያን እና ዲያቆናት በኒቆስያ በሚገኘው በቅዱስ መስቀል ቤተ ክርስትያን የቀረበውን መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት፦ ብዙዎች ክርስትያን የስቃይ የእስራት እና የግርፋት ምልክት የሆነውን መሣሪያ እንዴት ያመልካሉ በማለት ይጠይቁ ይሆናል፣ ለኛ ክርስትያኖች ይህ መሣሪያ ስለእኛ ብሎ ውርደታችንን የራሱን…

Read more: የሰው ልጅ በክፋት ላይ ድልን ለመቀዳጀት የክርስቶስ መስቀል ያሰፈልገዋል

Comments ()

Independent Catholic News -Thursday, June 3, 2010 -እስከንደሩን በምትባለው አንዲት የቱርክ ከተማ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ሉዪጂ ፓዶቨዜ (63 ዓመት ዕድሜ)  በትላንትናው ዕለት በስለት ተወግተው መገደላቸው ታወቀ። በሜዲትራንያን ወደብ አጠገብ በሚገኘው የበጋ መኖሪያ ቤታቸው ጓሮ ውስጥ በነበሩበት ወቅት ከአራት ዓመታት በላይ መኪና በማሽከርከር ያገለግላቸ በነበረው ሰው ጥቃቱ የተፈጸመባቸው መሆኑም ተገልጿል። የቱርክ ባለሥልጣናት ይህ…

Read more: ቱርክ ውስጥ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲይን ጳጳስ ተገደሉ።

Comments ()
ቫቲካን ሬድዮ - ትናንትና እሁድ ረፋድ ላይ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይና በአከባቢው ያሉ ጐደናዎችን ያጥለቀለቀ ከሁለት መቶ ሺ በላይ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ የንግሥተ ሰላም ጉባኤ አስተምህሮ አቅርበዋል። ምእመናኑ ከመላው ጣልያን የተሰበሰቡ ሆነው፣ ምክንያቱም በዚሁ ፈታኝ ጊዜ ምእመናን ቅዱስነታቸውን በጸሎትና በአካል እጐናቸው መሆናቸውን በማሳወቅ ድጋፋቸና አጋርነታቸውን ለመግለጥ መሆኑን ከቅድስት መንበር የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።
 
ቅዱስነታቸው የንግሥተ ሰማያት ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ይህንን ትምህርት ሰጥተዋል፦…

Read more: እግዚአብሔርን በቍርጠኝነትና በታማኝነት ማገልግል ያስፈልጋል።

Comments ()

የብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ የአዲስ አበባ ካቶሊካዊ ሰበካ ረዳት ጳጳስ ቅብዓተ ጵጵስና ዕሁድ ሚያዝያ 10 ቀን 2002 ዓ.ም አዲስ አበባ ካቶሊክ ካቴድራል በብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ካቶሊካውያን ዘኢትዮጵያ እጅ በደማቅ መንፈሳዊ ስነሥርዓት ተከናውኗል፡፡

ብፁዕነታቸው ከማለዳው በ1፡15 በብፁዓን ጳጳሳት፣ ቁጥራቸው በርካታ በሆነ ካህናት፣ መዘምራን፣ የብፁዕነታቸው ቤተሰብና ምዕመናን ታጅበው የዑደት ሥነስርዓት የተካሄደ ሲሆን በስነስርዓቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ጢሞቲዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የቅድስት ስላሴ ኮሌጅ ጳጳስ/ዲን ክቡር አቶ ግርማ ብሩ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር፣የተለያዩ ሃይማኖቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ካቶሊካዊ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተው ነበር፡፡

ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ለቀጳጳሳት ካቶሊካውያን ዘኢትዮጵያ ቅብዓተ ጵጵስናውን በሰጡበት ወቅት ባሰሙት ቃለምዕዳን ለእግዚአብሄር ምስጋና ይድረሰው ካሉ በኋላ…

Read more: የብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ቅብዓተ ጵጵስና ተከናወነ

Comments ()

የአዲሱ ሆሳዕና ሀገረስብከት ምስረታ ሚያዝያ 3 ቀን 2002 ዓ.ም በሆሳዕና ካቴድራል በታላቅ ድመቀት ተከብሮ ውሏል፡፡ የሃገረስብከቱ የመጀመሪያ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ወልደጊዮርጊስ ቅብዓተ ጵጵስናም በብፁዕ አቡነ ብርሀነየሱስ ሊቀጳጳሳት ካቶሊካውያን ዘኢትዮጵያ እጅ ተከናውኗል፡፡

 

በዕለቱ ብፁዕ ለቀጳጳሳት ጆርጅ ፓኒኩለም የቫቲካን አምባሳደር በኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት፣ክቡር አባ ፓየስ የአሜሲያ (የምስራቅ አፍሪካ ጳጳሳት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሃፊ፣ ክቡር አባ ሐጎስ ሐይሽ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ቤት ጠቅላይ ጸሐፊ፣ የተለያዩ ሃይማኖቶች ተወካዮች፣ ክቡር ዶ/ር ሺፈራው ተ/ማርያም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር፣ ኩቡር አቶ መለሰ አለሙ የሃዲያ ዞን አስተዳዳሪ፣ አቶ ታደሰ ሮሞ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ኣስተዳዳሪ፣ ከመላዋ ኢትዮጵያ፣ ከሆሳዕናና አካባቢዋ የተውጣጡ፣ ካህናት፣ ደናግልና ምዕመናን እንዲሁም የብፁዕነታቸው ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡

 

በበዓሉ ላይም በሆሳዕናና በኣካባቢዋ የስብከተ ወንጌል እንዴት እንደተጀመረና እንደተስፋፋ የሚያብራራ አጭር ታሪካዊ ዘገባ ቀርበዋል፡፡...…

Read more: የሆሳዕና ሃገረስብከት ምስረታ በታላቅ ድምቀት ተከበረ - የሃገረስብከቱ አዲስ ጳጳስ ቅብዓተ ጵጵስና ተከናወነ

Comments ()

አዲስ አበባ, የካቲት 30 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የካሪታስ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት ካርዲናል ኦስካር ሮድሪጌዝ ማራዲጋን በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

ካርዲናል ኦስካር ሮድሪገዝ ማራዲጋዝ ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች እንዳስታወቁት ውይይቱ በዋናነት ያተኮረው ካሪታስ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ እያከናወነ ባላቸው የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ነበር፡፡ በዚህም ድርጅታቸው ኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ያለችውን ልማት የማገዝ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በተለይም በትምህርት ዘርፍ ኢትዮጵያን ለማገዝ በሚያደርገው ጥረት በኢትዮጵያ የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲን በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የማስፋፋት ፍላጎት አለው ማለታቸውን የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ብርሃነየሱስ በበኩላቸው ካሪታስ ኢንተርናሽናል በመላው ዓለም በ162 አገሮች የልማትና የበጎ አድርጎት ተግባራት ላይ እንደሚሳተፍ ገልጸዋል፡፡

Read more: ፕሬዚዳንት ግርማ የካሪታስ ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንትን አነጋገሩ

Comments ()

ቫቲካን ሬድዮ - ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ አሑድ ዕለት ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ባቀረቡት ትምህርትነበር "ኃጢአትን መቋወም ኃጢአተኛን ግን መንከባከብ አለብን" ያሉት። ቅዱስነታቸው የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመመርኰስም የሚከተለውን ትምህርት ሰጥተዋል:- "ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ ዛሬ 5ኛ የዘመነ ጾም እሁድ ይዘናል፣ የዛሬው ቃለ ወንጌል ስለ በዝሙት የተገኘችውን ሴት ኢየሱስ ከሞት ቅጣት ሲያድናት እንመለከታለን፣ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 8:1-11 የተመለከትን እንደሆነ ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ተቀምጦ ሕዝቡን እያስተማረ ጸሐፊዎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ሕግ ተወግራ መሞት የነበረባትን በምንዝርና የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጥዋት። ኢየሱስ እንዲፈርዳት ፈልገው ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። ይህንን ያሉት ደግሞ የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ነው። ሁኔታው እጅግ ከባድ ነው።...…

Read more: ኃጢአትን መቋወም ኃጢአተኛን ግን መንከባከብ አለብን

Comments ()

ቫቲካን ሬድዮ - በቅድስት መንበር በስደተኞች ጳጳሳዊ ምክር ቤት የተዘጋጀ ጂፕሲ በመባል የሚታወቁ የኤውሮጳ ዘላን ማኅበረ ሰብ ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮን የሚመለከት ዓውደ ጥናት በቫቲካን እየተካሄደ ነው፣ እስከ ነገ ሐሙስም ይቀጥላል። በዓውደ ጥናቱ በኤውሮጳ ጂፕሲዎችን የሚያገልግሉ የየአገሩ ዳይረክተሮችም ተሰብስበው እየተወያዩ ነው።

ጉባኤውን በቅዳሴ የከፈቱት በቅድስት መንበር የስደተኞች ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶንዮ ማሪያ ቨልዮ ሲሆኑ የምክር ቤቱ ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኣጎስቲኖ ማርከቶም ተገኝተዋል።

ብፁዕነታቸው በዓውደ በጉባኤው ባሰሙት ንግግር “ቤተ ክርስይትያን የሰው ልጅ ሕይወት ሰብአዊ እስከሚሆን ድረስ ፍትሕ አልባነት እና የዘር አድልዎን ለማውገዝ የተጠራች ናት። ቤተ ክርስትያን ለጥሪዋና ተልእኮዋ ታማኝ በመሆን ድሆችን በቅንነት ያገለገለች እንደሆነ የኅሊና መርመራ የምታደርግበትም ጊዜ ነው። አሳዛኙ የጂፕሲዎች ታሪክና ሕይወት በመነጠልና በስደት የተሞላ ነው። በዚህ ታሪክ ቤተ ክርስትያንም ቀጥተኛን ተዛዋሪ የሆኑ የራስዋ ጥፋቶች አልዋት፣ እነኚህ ጥቂትም ቢሆኑ ያደረጋቻቸውን ትላላቅ ነገሮች ሊያደፍርሱ ይችላሉ።" ካሉ በሁዋላ በዕርቅና በፍትሕ በመመራት ሮም እና ሲንት የሚባሉ ጂፕሲዎች በቤተ ክርስትያን ሕይወትና ሃብት ተሳታፊ እንዲሆኑ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። ቤተ ክርስትያንም በበኵልዋ በመሀከላቸው በመገኘት አገልግሎትዋና አጋርነትዋን እንድታበረክት አደራ ብለዋል።

Read more: ቤተ ክርስቲያን የዘር አድልዎ እና ፍትሕ አልባነትን ትቃወማለች

Comments ()
ቫቲካን ሬድዮ - “የገዛ ራስህን ድካም መገንዘብ ከሁሉ መቅደም ያለበት ተገቢ ነገር ነው”፣ ይህን ያሉት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ ሮማ  በሚገኘው የቅድስት ሳቢና ባዚሊካ በሥርዓተ ላቲን የጾም ጅማሬ የቅዳሴ ሥርዓተ በመሩበት እና ባሰሙት ስብከት ነው። አያይዘውም ሰው ዳግም ፍትሐዊ መሆን የሚችለው በክርስቶስ በኩል በተገለጠው የእግዚአብሔር ፍትሕ እና ምሕረት…

Read more: የገዛ ራስህን ድካም መገንዘብ

Comments ()
ቫቲካን ሬድዮ - እ.ኤ.አ. የካቲት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በመላው ዓለም 18ኛው የሕሙማን ቀን ይከበራል። ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛው በዕለቱ በሮም ሰዓት አቆጣጠር 10.30 በቫቲካን ባዚሊካ መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ በዕለቱ የሉርድ ብፅዕት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓልም ታውሶ ይውላል።
የዘንድሮው የዕለተ ሕሙማን መሪ ቃል “ቤተ ክርስትያን ለሚሰቃዩት የምታበረክተው የፍቅር አገልግሎት” የሚል ነው ሲሆን ከአሁን በፊት ቅዱስነታቸው በሕመምና በስቃይ የሚገኙ የሰው ልጆች ክብርን አስመልክተው ብዙ ትምህርት ሰጥተዋል። ለምሳሌ እ.ኤ.አ.ታሕሣሥ 2 ቀን 2007 ዓም በቅዱስ ዮሓንስ መጥምቅ ሆስፒታል ሲናገሩ፥ “ለምን እንሰቃያለን? የስቃይ ሕይወት አዎንታዊ ትርጓሜ ሊኖረው ይችላልን? ከስቃይና ከሞት ነፃ ሊያወጣን የሚችል ማን ነው? እነኚህ የኑሮ መሠረታዊ ጥያቄዎች ናቸው። ስቃይ በአእምሮ ሊታወቅ የማይቻል ምሥጢር ስለሚያንሣብን፣ እነኚህ ጥያቄዎች በሰው ልጅ አነጋገር ብዙውን ጊዜ መልስ አይኝላቸውም። ይህ ግን ስቃይ ትርጉም የለውም ማለት አይደለም። በሕመምና በስቃይ በምንገኝበት ጊዜ እግዚአብሔር ምሥጢራዊ በሆነ መንገድ ይጐበኘናል፣ ሁሉመናችንን ለፈቃዱ የተውነው እንደሆነ የፍቅሩን ችሎታ መቅመስ እንችላለን።" ብለው ነበር።
ነገ በሚካሄደው ሥርዓት ቅዱስነታቸው ከሕሙማን ጋር ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ እንዲሁም ሁል ጊዜ በዚህ አጋጣሚ እንደሚያደርጉት 18ኛው ዓለም አቀፍ የሕሙማን ቀንን የሚመለከት መልእክታቸውን ያስተላልፋሉ።

Read more: ስቃይ መልስ የለውም ማለት ትርጉም የለውም ማለት አይደለም!

Comments ()

Independent Catholic News - Tuesday, January 19, 2010 - በ1973 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ላይ የግድያ ሙከራ ያደረገው ቱርካዊ ከእስር ተለቀቀ። ግለሰቡ ከዚህ በኋላ የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ግዳጁን እንደሚፈጽምም የቱርክ መገናኛ ብዙኀን ዘግቧል።

በአሁኑ ሰዓት 52 ዓመት ዕድሜ ያለው መህሜት አሊ አጅካ በር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ ባደረገው…

Read more: ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ላይ የግድያ ሙከራ ያደረገው ቱርካዊ ከማረምያ ቤት ወጣ

Comments ()

የልደተ ክርስቶስ ድባብ በቫቲካን መንበረ ጴጥሮስ አደባባይና ቤተ ክርስቲያን...(ፎቶዎች)

በቫቲካን ከተማ የሚገኘው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ደብር - መንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ - በዓለማችን ካሉ ተጎብኚ ቦታዎች የብዙዎችን ቀልብ በመሳብ ቀዳሚው መሆኑ ይታወቃል። ከአደባባዩ ጀምሮ እስከ ደብሩ ሥነ ሕንፃው ቅርጽና ውበት፣ እንዲሁም በውስጡ ያሉ  ዓለማችን ያፈራቻቸው ታላላቅ ሥነ ጥበብት የሳሏቸውና…

Read more: የልደተ ክርስቶስ ድባብ በቫቲካን መንበረ ጴጥሮስ

Comments ()

Subcategories

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።