እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

፮ - “ወደ ፈተናም አታግባን"

    ፮ - “ወደ ፈተናም አታግባን"

ኃጢአቶቻችን በፈተና ከመውደቃችን የሚመነጩ ስለሆኑ ይህ ልመና ከቀደመው መንስኤ ጋር ተያያዥነት አለው፡፡ ስለዚህም አባታችንን ወደ ፈተና “እንዳያስገባን” እንለምነዋለን፡፡ የግሪኩን ግሥ በነጠላ /በአንድ የእግሊዝኛ ቃር መተርጐም ያስቸግራል፤ የግሪኩ ቃል “ወደ ፈተና እንገባ ዘንድ አትፍቀድ” እና “በፈተና እንድንወድቅ አታድርግ” የሚል ሁለት ትርጉም አለው፡፡ “እግዚአብሔር በክፉ አይፈትንም፤ አርሱ ራሱ ማንንም አይፈትንም፡፡” ይልቁንም በተፃራሪው ከክፉ ነገር ነጻ ሊያወጣን ይፈልጋል፡፡ ወደ ኃጢአት የሚመራንን መንገድ እንከተል ዘንድ እንዳይፈቅድ እንለምነዋለን፡፡ “በሥጋና በመንፈስ” መካከል በሚካሄድ ጦርነት ውስጥ እንገኛለን፤ ይህ ልመና የማወቅንና የብርታትን መንፈስ ይማጸናል፡፡

መንፈስ ቅዱስ ለውስጣዊው ሰው ዕደገት በሚያስፈልጉት መከራዎች እንዲሁም ወደ ኃጢአትና ሞት በሚመራው ፈተና መካከል እንድንለይ ያደርገናል፡፡ በመፈተንና በፈተና በውደቅ መካከል ያለውን ሁኔታ ለይተን ማወቅ አለብን፡፡ በመጨረሻም ውጤቱ ሞት ሆኖ ሳለ ዓላማው “ዓይንን የሚያስደስት” መልካምና ተፈላጊ መስሎ የሚታየውን የፈተናን ሐሰተኝነት ማስተዋል እርቃኑን ያስቀረዋል፡፡

እግዚአብሔር ነጻ ፍጡራንን ይሻል እንጂ መልካሙን እንድንቀበል አያስገድደንም፡፡ ፈተና የሚሰጠን አንዳንድ ጥቅም አለው፡፡ ነፍሳችን ከእግዚአብሔር የተቀበለችውን ነገር ከአምላክ በስተቀር እኛም ራሳችን ብንሆን እንኳ አናውቀውም፡፡ ነገር ግን ፈተና እኛ ራሳችንን ማወቅ እንችል ዘንድ ይህንኑ ይገልጽልናል፤ በዚህም መሠረት እኛ ክፉ ዝንባሌያችንን እናውቃለን፤ ስለሆነም ፈተና ስለገለጸልን በጐነት ሁሉ ምሥጋና ልናቀርብ ይገባናል፡፡

“ወደ ፈተና አታግባን” የሚለው ሐረግ የልብን ውሳኔ ያመለክታል፡፡ “መዝገብን ባለበት ልብህም በዚያ ይሆናል… ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፡፡” ማቴ 6፡21-24 “በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ እንመላለስ፡፡” ገላ 5፡25 ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሚሆን በዚህ ስምምነት አብ ጥንካሬን ይሰጠናል፡፡ “ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅዱ እግዚአብሔር የታመነ ነው፤ ትታገሱም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል፡፡” 1ቆሮ 1ዐ፡13

እንዲህ ዓይነት ተጋድሎ እንዲህ ዓይነት ድል ሊገኝ የሚችለው በጸሎት ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ተልአኮውን በይፋ ሲጀምርና በመጨረሻ ስቃዩ ባደረገው ትግል ፈታኙን ድል የነሣው በጸሎት ነው፡፡ ለሰማያዊው አባታችን በምናቀርበው በዚህ ልመና ክርስቶስ ከተጋድሎውና ከስቃዩ ጋር አንድ ያደርገናል፡፡ እርሱ ከእርሱ ልብ ጋር ንቃት አንዲኖረን ይጠራናል፡፡ ንቃት “የልብ ጠባቂ” ነው፤ ኢየሱስም አብን ስለ እኛ ሲለምን “በስምህ ጠብቃቸው” ዮሐ 17፡11 ይላል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ዘወትር ነቅተን እንድንጠባበቅ ይሻል፡፡ በመጨረሻም ይህ ልመና በምድራዊ ተጋድሏችን ከሚሆነው ከመጨረሻው ፈተናችን ጋር በተዛመደ መልኩ ልዩ ትርጉሙን ያገኛል፡፡ የመጨረሻውን ጽናት ይጠይቃል፡፡ “እነሆ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ነቅቶ የሚጠባበቅ ሰው ምስጉን ነው፡፡” ራዕ 16፡15

/የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ከቁጥር 2846-2849/

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት