እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

፫ - “ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን”

    ፫ - “ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን”

አባታችን “ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነቱን እንዲያውቁ ይወዳል፡፡” እርሱ “ማንም እንደይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል፡፡” ትዕዛዙም “እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፣ እንደወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ” የሚል ነው፡፡ ይህ ትእዛዝ ሌሎቹን ትእዛዛት ሁሉ የሚያጠቃልልና የኢየሱስንም ፈቃድ የሚገልጽ ነው፡፡

በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ የፈቃድን ምስጢር አስታውቆናልና፤ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው፡፡ እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን፡፡ ይህን የፍቅር እቅድ በሰማይ እንደሆነው ሁሉ እንዲሁ በምድርም ላይ ሙሉ በሙሉ እውን ይሆን ዘንድ እንለምናለን፡፡

የአብ ፈቃድ በማያዳግም ሁኔታ ሙሉ ፍጻሜ ያገኘው በክርስቶስና በእርሱ ሰብአዊ ፍቃድ ነው፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም ሲመጣ “አምላኬ ሆይ፣ … እነሆ ፈቃድህን ለመፈጸም መጥቻለሁ” አለ፡፡ “እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁ” ማለት የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ በስቃዩ ጊዜ ሲጸልይ ይህን ፈቃድ ሙሉ በሙሉ ይቀበላል፡፡ “የእኔ ፈቃድ አይሁን ያንተ እንጂ” ሲልም ይናገራል፡፡ በዚህም የተነሳ ኢየሱስ “ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለኃጢአታችን ራሱን ሰጠ” “በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል፡፡

“ኢየሱስ ምንም እንኳ ልጅ ቢሆንም ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፡፡” በእርሱ ልጅነትን ያገኘን እኛ ኃጢአተኞች ፍጡራን መታዘዝን እንማር ዘንድ ምን ያህል ዕውቀት አለን! የአባታችን የእግዚአብሔርን ፈቃድና እርሱ ስለዓለም ሕይወት ያለው የድኀነት እቅድ እንዲፈጸም ፈቃዳችንን ከልጁ ፈቃድ ጋር ያዋሕድልን ዘንድ እንለምነዋለን፡፡ እኛ ይህን የማድረግ ችሎታ ፈጽሞ የለንም፤ ይሁን እንጂ ራሳችንን ከክርስቶስና ከእርሱም መንፈስ ቅዱስ ኃይል ጋር ካዋሐድን ፈቃዳችንን ለአብ ማስገዛት እንዲሁም ልጁ ሁልጊዜ የሚመርጠውን ነገር ለመምረጥ- አብን ደስ የሚያሰኝ ነገር ለመፈጸም መወሰን እንችላለን፡፡

ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ለክርስቶስ በመስጠት ከእርሱ ጋር አንድ መንፈስ መሆን ስለምንችል፤ በሰማይ እንደሆነ ሁሉ በምድርም ፍጹም ይሆን ዘንድ ፈቃዱን እንፈጽማለን፡፡

ትሑታን እንሆን ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደሚያስተምረን አስቡ፡፡ መልካም ተግባራችን ፍሬያማ  የሚሆነው ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር በሚሰጠን ጸጋ መሆኑን እንድንገነዘብ በማድረግ ነው፡፡ አምላክ እያንዳንዱ ምእመን በአጠቃላይ ለመላው ዓለም እንዲጸልይ ያዝዛል፡፡ እርሱ “ፈቃድህ በእኔ ወይም በእኛ ይሁን” አላለም፤ ነገር ግን “በምድር ላይ ይሁን” አለ እንጂ፡፡ እንደዚህ ያለበትም ምክንያት፣ ስሕተት በምድር ፈጽሞ እንዲጠፋ፤ እውነት በምድር ላይ ሥር እንዲሰድድ፣ ክፋት በምድር እንደወገድ፣ መልካም ምግባር በምድር እንዲያብብ፣ ምድርም ከሰማይ በምንም ዓይነት የተለየች እንዳትሆን ነው፡፡

በጸሎት “የእግዚአብሔር ፈቃድ” ለይተን ማወቅን እርሱንም የምንፈጽምበት ጽናት ማግኘት እንችላለን፡፡ ኢየሱስ ሰው ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚባው ቃላትን በመናገር ሳይሆን “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ በመፈጸም” እንደሆነ ያስተምረናል፡፡

“እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ብኖር ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል፡፡” ከሁሉም በላይ በመሥዋዕተ ቅዳሴ የሚገለጸው፣ ቤተ ክርስቲያን በጌታዋ ስም የምታቀርበው ጸሎት ኃይል ይህን ይመስላል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ጸሎት ፍፁም ቅድስት ከሆነችው እመአምላክና ፍላጐታቸውን ፈቃዱን ብቻ መፈጸም በመሆኑ ጌታን ደስ ከሚያሰኙት ቅዱሳን ጋር የሚደረግ የምልጃ ሱታፌ ነው፡፡

“ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን” የሚሉትን ቃላት “በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ እንደሆነው በቤተ ክርስቲያንም ይሁን” ወይም “የአባቱን ፈቃድ እንደፈጸመው ሙሽራ ሁሉ ለእርሱ በታጨችው ሙሽራይቱም ይሁን የሚያሰሙ አድርጐ መውሰድ ከእውነቱ ጋር የሚጣረዝ አይሆንም፡፡

/የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ከቁጥር 2822-2827/

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት