እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ሁሉን ቻይ

አንቀጽ 3 - ሁሉን ቻይ

ከመለኮታዊ ባሕርያቱ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃያልነት ብቻ ነው በጸሎተ ሃይማኖት ውስጥ የተጠቀሰው፤ በዚህ ኃይል መማን በሕይወታችን ላይ ታላቅ ለውጥ ያመጣል፡፡ ኃይሉም ሁሉን አቀፍ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ምክንያቱም ሁሉንም ነገር የፈጠረ አምላክ ሁሉንም ይገዛል፤ ሁሉን ማድረግ ይችላል፡፡ የአምላክ ኃይል ፍቅር ነው፤ እርሱ አባታችን ነውና፡፡ ምስጢራዊም ነው፤ ምክንያቱም ኃይሉን “በድካም ፍጹም አደርጎ የሚገልጠው እምነት ብቻ ነውና፡፡”

“እርሱ በፈቃዱ ሁሉ ያደርጋል”

ቅዱሳት መጻሕፍት በተደጋጋሚ እግዚአብሔር ሁሉን አቀፍ ኃይል መሆኑን ያስተምራሉ፡፡ እርሱ “የያዕቆብ ክንድ” ፣ “የሠራዊት ጌታ”፣ “ብርቱና ኃያል” በመባል ይጠራል፡፡ እግዚአብሔር “በሰማይም በምድርም” ሁሉን መቻሉ እርሱ ስለፈጠራቸው ነው፡፡ ሥራዎቹንም እንደ ፈቀደው ማድረግ ለሚችለው ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም፡፡ ሥርዓታቸውን የመሠረተና ሙሉ በሙሉ ለእርሱ ተገዢ የሆኑ፣ በእርሱ ቀጥጥር ሥር ያሉ እንደ ፈቀደ የሚያደርጋቸውም ስለሆኑ እርሱ የምድርና የሰማያት ጌታ ነው፡፡ እርሱ የታሪክ ባለቤት፣ ልብንና ሥራን እንደ ፍቃዱ የሚገዛ ነው፡፡ “እንደ ወረደች እንደ ጠል ጠብታም በፊትህ የተናቀ ነውና የጸናች ሥልጣንህን የሚቃወማት ማን ነው?” ጥበብ 11፡23

“አንተ ሁሉን የምትችል ነህና ሁሉን ይቅር ባይ ነህ”

አባትነቱና ኃይሉ አንዱ ሌላውን ይገልጣልና እግዚአብሔር ሁሉን የሚችል አባት ነው፡፡ እግዚአብሔር ፍላጐታችንን በሚያሟላልን መንገድ አባታዊ ኃይሉን ያሳያል፤ ሁሉን የሚችል ጌታ “እኔ አባታችሁ እሆናለሁ እናንተም ወንዶችና ሴት ልጆቼ ትሆናላችሁ” 2ቆሮ 6፡18 ባለን መሠረት እኛን ልጆቹ አድርጎናል፡፡ በመጨረሻም በማያልቀው ምሕረቱ ኃጢአቶቻችንን በነፃ አስወግዶልን የኃይሉን ታላቅነት አሳይቶናል፡፡

ሁሉን የሚችለው የእግዚአብሔር ሥልጣን በምንም ዓይነት ሁኔታ በዘፈቀደ የሚሆን አይደለም፡፡ “በእግዚአብሔር ዘንድ ኃይል፣ ውስጣዊ ባሕርይ፣ ፈቃድ፣ ዕውቀት፣ ጥበብ እና ጽድቅ ሁሉም አንድ ናቸው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔር ኃይል በእርሱ በጐ ፈቃድ ወይም ጥበብ ያልታቀፈ ምንም ነገር የለም፡፡”

የእግዚአብሔር ደካማ የመምሰል ምስጢር

ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔ አብ ያለን እምነት በክፋትና መከራ ሊፈተን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር የሌለና ክፋትን ማቆም የተሳነው ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን እጅግ ምስጢራዊ በሆነ መንገድ እግዚአብሔር አብ ልጁን በፈቃደኝነት ውርደትን እንዲቀበል በማድረግና ከሞት በማስነሣት ክፋትን ድል የመታበት ታላቅ ናኀይሉን ገልጦልናል፡፡ ስለዚህ የተሰቀለው ክርስቶስ “የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ ነው፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሞኝነት ነው ተብሎ የሚታሰበው ነገር ከሰዎች ጥበብ ይልቃል፤ የእግዚአብሔር ደካማነት ነው ተብሎ የሚገመተውም ነገር ከሰዎች ኃይል ይበልጣል፡፡” 1ቆሮ 1፡24-25 ክርስቶስን ከሞት በማስነሣቱና በክብር በቀኙ በማስቀመጡ አብ “በእኛ በምናምነው ውስጥ ያለው ኃይል ምን ያህል ታላቅ መሆኑን አሳይቶናል፡፡” ኤፌ 1፡19-22

ሁሉን የሚችል የእግዚአብሔር ኃይል ምስጢራዊ መንገድ ማሳየትየሚችለው እዋነት ብቻ ነው፡፡ ይህ እምነት የክርስቶስን ኃይል ያገኝ ዘንድ በድክመቱ ይከብራል፡፡ ድንግል ማርያም የዚህ እምነት ዋና ተምሳሌት ናት፡፡ ምክንያቱም “ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም” ብላ አምናለች፤ “ኃያሉ እግዚአብሔር ትልቅ ነገር ስለ አደረገልኝ ስሙ ቅዱስ ነው” በማለትም ጌታን አመሰገነች፡፡ ሉቃስ 1፡37፣ 49፡፡

“ለእግዚአብሔር የሚሳነው ምንም ነገር እንደሌለ በአእምሮአችን ቀርፀን ከማኖር የበለጠ እምነታችንንና ተስፋችንን የሚያረጋግጥልን ምንም ነገር የለም፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን የሚችል ኃይል የመሆኑን ሐሳብ አእምሮአችን አንዴ ከጨበጠ /ጸሎተ ሃይማኖት/ እንድናምን የሚያቀርብልን ነገር ሁሉ - ነገሩ ከተለመዱት የተፈጥሮ ሕግጋት በላይ ታላቅና አስደናቂ ቢሆንም እንኳ በቀላሉና ያለማወላወል ይቀበላል፡፡

Write comment (0 Comments)

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት