እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ዘጠነኛይቱ ትእዛዝ - የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፣ የባልንጀራህን ሚስት፣ ሌሎችንም፣ ገረዱንም፣ በሬውንም፣ አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ

ዘጠነኛይቱ ትእዛዝ

"የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፣ የባልንጀራህን ሚስት፣ ሌሎችንም፣ ገረዱንም፣ በሬውንም፣ አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ” ዘጸ. 2ዐ፡17

“ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም፣ ያን ጊዜ በልቡ ከርሷ ጋር አመንዝሯል” ማቴ. 5፡28

ቅዱስ ዮሐንስ የሥጋ ምኞት፣ የዐይን አምሮት፣ በገንዘብ መመካት በማለት ሦስት ዓይነት ምኞቶችን ወይም ፍትወቶችን ለይቶ ያስቀምጣል፡፡ እንደ ካቶሊካዊ ትምህርተ-ክርስቶሳዊ ወይም ፍትወቶችን ለይቶ ያስቀምጣል፡፡ ምኞትን፣ አስረኛው ደግሞ የሌላውን ንብረት መመኘት ይከለክላል፡፡

በቃሉ አመጣጥ መሠረት “ምኞት / ፍትወት” የትኛውንም የሰውን ጽኑ ፍላጐት ሊያመለክት ይችላል፡፡ ክርስቲያናዊ ትምህርት መለኮት የሰውን አእምሮአዊ አሰራር የሚፃረር ፍላጐት የል ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም “ሥጋ” በ “መንፈስ” ላይ የሚያነሣው ዓመፅ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ የሥጋ ምኞት የሚመነጨው አዳም ባለመታዘዙ ካመጣው ኃጢአት ነው፡፡ ሥጋዊ ምኞት የሰውን ሥነ ምግባራዋ ክህሎቶች ያዛባል፤ በራሱ በደል ባይሆንም፣ ሰውን ለኃጢአት ሥራ ይገፋፋል፡፡

ሰው የመንፈስና የሥጋ ጥምረት ውጤት በመሆኑ በውስጡ ብርቱ ውጥረት አለ፤ ማለትም በ “በመንፈስ” እና በ “ሥጋ” መካከል አንድ ዓይነት የዝንባሌዎች ትግል ይካሄዳል፤ ሆኖም ይህ ትግል የአዳም ኃጢአት ውርስ ነው፡፡ ይህ ትግል የኃጢአት ውጤት ከመሆኑም በላይ የኃጢአት መረጋገጫ ነው፡፡ ይህ ትግል በየእለቱ በየሚያጋጥሙ መንፈሳዊ ውጊያዎች አንዱ ነው፡፡

ለሐዋርያው ጉዳይ ለመንፈሳዊው ነፍስ ጋር የሰውን ባሕርይ እና ግላዊ አመለካከት አጣምሮ የያዘውን ሥጋ የመጥላት ወይም የመኮነን ጉዳይ አይደለም፡፡ ይልቁንም እርሱ የሚያተኩረው ከሥነ ምግባር አኳያ በበጐ ወይም በክፉ ሥራዎች ወይም በተሻለ አገላለጽ፣ ዘለቄታ ያላቸው ባህርያት በጐ ምግባርና ክፋት /በመጀመሪያው ሁኔታ/ የመንፈስ ቅዱስ የማዳን ሥራ መቀበል አልያም /በሁለተኛው ሁኔታ/ ያለመቀበል ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ሐዋርያው “በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ” ሲል ጽፏል፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት