እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት

የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት

በዘመናዊ ኅብረተሰብ ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በመረጃ ሥርጭት፣ በባሕላዊ እድገትና ቀረጻ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ይህ ሚናቸውም በቴክኖሎጂ እድገት ሳቢያ፣ በሚሰራጨው ዜና ስፋትና ብዛት እንዲሁም በሕዝቡ አስተያየት ላይ ባለው ተጽእኖ የመገናኛ ብዙኃን ሚና እያደገ በመሄድ ላይ ነው፡፡

በመገናኛ ብዙኃን የሚተላለፍ መረጃ ለጋራ ጥቅም የሚውል ነው፡፡ ሕብረተሰብ በሐቅ፣ በነጻነት፣ በፍትሕና በትብብር ላይ የተመሠረተ መረጃን ማግኘት መብት አለው፡፡

“የዚህ መብት በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋል የሚተላለፈው መረጃ ይዘት እውነተኛነት እንዲኖረው ፍትሕንና ፍቅር በደነገጉአቸው ገደቦች መሠረትም የተሟላ እንዲሆን ይጠይቃል፡፡ ይህም ማለት ከዜና አሰባሰብና ሥርጭር አኳያ ምግባራዊው ሕግና ሕጋዊ መብቶች እንዲሁም ሰአብዊ ክብር መጠበቅ አለባቸው ማለት ነው፡፡”

“የሕብረተሰቡ አባሎች በሙሉ በዚህ ዘርፍ የፍትሕንና የፍቅርን ጥያቄዎች መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ጤናማ ሕዝባዊ አስተሳሰብ በመፍጠርና በማስረጽም ረገድ የበኩላቸውን ማበርከት አለባቸው፡፡” ሕብረት የእውነተኛና የትክክለኛ መረጃ ልውውጥ እንዲሁም እውቀትንና ለሌሎች የሚኖርን  አክብሮትን የሚያዳብሩ ሃሳቦች በነጻ የሚንሸራሸሩበት የመገናኛ ብዙኃን ውጤት ነው፡፡

የመገናኛ አውታሮች በተለይም መገናኛ ብዙኃን ከተጠቃሚዎች መካከል አንዳንዶቹን ንቁ ተጠቃሚዎች ከማድረግ ይልቅ የሚሰሙትንና ወይም የሚያዩትን በዝምታ እንዲቀበሉ ተጽእኖ ሊያሳድርባቸው ይችላል፡፡ ሰዎች በዜና ማሰራጫ አጠቃቀም ቁጥብነትንና ሥነ ሥርዓትን ልምድ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ጤናማ ያልሆኑ ተጽእኖችን ይበልጥ በቀላሉ ለመቋቋም በሳልና ትክክለኛ ሕሊና እንደኖራቸው ይሻሉ፡፡

ጋዜጠኞች ከሥራቸው  ባሕርይ በሚመነጭ ዜና ሲያሰራጩ እውነትን የማገልገልና ፍቅርን ያለማጉደል ግዴታ አለባቸው፡፡ ጋዜጠኞች የጉዳዮችን ውስጠ ነገር ሲያብራሩ አንደሁም ግለሰቦችን በተመለከተ ትችታዊ አስተያየቶችን ሲያቀርቡ በሁለቱም አቅጣጫ በኩል ጥንቃቄ ለማድረግ ከፍ ያለ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡ የሌላውን ስም ከማያጐድፍ ማንኛውም ተግባር ለመራቅ ከፍ ያለ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ለጋራ ጥምም ሲባል ለመንግሥት ባለሥልጣናት በዚህ ልዩ ኃላፊነቶች አለባቸው፡፡ እውነተኛና ትክከለኛ የመረጃ ስርጭት ነጻነትን መጠበቅና ማስጠበቅ… የዚህ አካላት ፈንታ ነው፡፡ ሕጐችን በማውጣትና ገቢራዊ መሆናቸውን በመከታተል፣ በመገናኛ ብዙሃን ሕገወጥ አጠቃቀም፣ “ሕዝባዊ ሥነ ምግባርን ማኅበራዊ እድገት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንዳይወድቁ” ባለሥልጣናት ማረጋገጥ ይጠበቅባዋቸል፡፡ ግለሰቦች ክብራቸውንና የግል ሕይወታቸውን ለማስጠበቅ ያሏቸውን መበቶች የሚጥሱትን ሁሉ መቅጣት አለባቸው፡፡ የጋራ ጥቅምን በተመለከተ ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃዎች ማቅረብ ወይም ለሕዝቡ ትክክለኛ ጥያቄዎች ምለሽ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡ በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ሕዝባዊ አስተያየትን ለማዛባት አሳሳች መረጃ መጠቀምን በምንም መልኩ መደገፍ አይቻልም፡፡የሕዝባዊ ሥልጣን ጣልቃ መግባት የግለሰቦችንና የቡድኖችን ነጻነት የሚጐዳ መሆን የለበትም፡፡

እውነትን በዘዴ ወደ ሐሰት የሚለውጡትን፣ መገናኛ ብዙኃን አማካኝነት በአስተሳሰብ ላይ ፖለቲካዊ ቁጥጥር የሚደረጉትን፣ በችሎት ላይ ተከሳሾችንና ምስክሮችን የሚያሳስቱትን “የአስተሳሰብ ወንጀል” ነው ብለው የሚገምቱትን ማንኛውንም ነገር በማነቅና በማፈን አምባ ገነንነታቸውን ለማስጠበቀ እንደሚችሉ የሚያስቡ ፈላጭ ቆራጭ መንግሥታት የሚፈጽሙትን ሰቆቃ ሥነ-ምግባራዊ ፍርድ ሊኰንነው ይገባል፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት