የመንፈስ ፍላጐቶች

የመንፈስ ፍላጐቶች

የሕግና የጸጋ እቅድ የሰዎች ልብ ከንፍገትና ከቅናት እንዲርቅ የደርጋል መልካሙንም አምላክ እንዲሹ ያደርጋቸዋል፡፡ እንዲሁም ይቅ እቅድ የሰውን ልብ የሚያረኩትን የመንፈስ ቅዱስ ፍላጐቶች ለሰው ልብ እንዲገልጹ ያደርጋል፡፡

የተስፋ ባለቤት የሆነ አምላክ ከመጀመሪያ አንስቶ ሰው “… ለመብላት ያማረ… ለዓይን የሚያስጐመደ… ጥበቡም መልካም” ወደሚመስል መጥመድ እንዳይገባ ምንጊዜም አስጠንቅቆአል፡፡

ለእስራኤል በአደራ የተሰጠ ሕግ ለእሱ ይታዘዙ ለነበሩ ሰዎች መንፃት “እንኳ” በቂ አልነበረም፤ እንዲያውም የ”ምኞት” መሣሪያ ሆኗል፡፡ በመሻትና በማድረግ መካከል ያለው ልዩነት/ክፍተት “የአእምሮዬ ሕግ” በሆነው በእግዚአብሔር ሕግና “በብልቶቼ ላለ ለኃጢአት ሕግ ምርኮኛ ባደረገኝ” ሌላ ሕግ መካከል ያለውን ተቃርኖ ያመለክታል፡፡

“አሁን ግን በሕግና በነብያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፤ እርሱም ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመነ የሚገኘው የእግዚአብሔር ፍድቅ ነው፡፡” ከእንግዲህ ወዲህ የክርስቶስ ምእመናን “ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቅለውታል” በመንፈስ ቅዱስ ይመራሉ፤ የመንፈስ ቅዱስ ፍላጐቶቹም ይከተላሉ፡፡