የልብ ድኽነት

የልብ ድኽነት

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እርሱን ከምንም ነገርና ከማንም አስበልጠው በእንዲመርጡት ይመክራቸዋል፤ ለእርሱና ለወንጌል ሲሉም “ያላቸውን ሁሉ  እንዲተው” ያዛቸዋል፡፡ ከሕማማቱ ጥቂት ቀደም ብሎ አንዲት የኢየሩሳሌም መበለት ሴትን ምንም ደኻ ብትሆን፣ ያላትን በሙሉ መስጠትዋን በርአያነት አቅርቦላቸዋል፡፡ ወደ መንግሥተ ሰማይ ለመግባት ከሃብት የመራቅን ትእዛዝ መቀበል ግዴታ ፡፡

ክርስቲያን ምእመናን “ፍፁም ፍቅርን የመሻት ጉዟቸው በምድራዊ ነገሮች ጥቅምና ወንጌላዊነት ከሚጠይቀው የድህነት መንፈስ በተፃራሪ በቆመው ሃብትን በማሳደድ ፍላጐት እንዳይደናቀፍ መውደዳቸውን በተገቢው አቅጣጫ መምራት አለባቸው፡፡”

“በመንፈስ ድኾች የሆነ ብፁዓን ናቸው፡፡” ማቴ. 5፡3 ብፅዕናዎች የደስታና የጸጋ፣ የውበትና የሰላም ሥርዓትን ይገልጻሉ፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግሥት የእነርሱ የሆነውን ድሆች ደስታ ያከብራል፡፡

ቃል ሰው በሙሉ ፈቃደኛነት የሚቀበለውን ትህትና “የመንፈስ ድኽነት” የሚል ስያሜ ሰጥቶታል፡፡ ሐዋርያም “ለእናንተ ሲለ ድኻ ሆነ” በማለቱ የእግዚአብሔር ድኻነት በምሣሌነት ያቀርባል፡፡

ጌታ በሃብታሞች ያዝናል፤ ምክንያቱም የእነርሱ መጽናኛ የሀብታቸው ብዛት ነውና፡፡ “ትእቢተኛ ምድራዊ ሥልጣንን ይሻል፡፡ በመንፈስ ድኾች የሆኑትን ግን መንግሥተ ሰማያት የእነሱ ናትና ብፁዓን ናቸው፡፡”  ሁሉንም ነገር በሰማይ ላለው አባት መተው ይገባል ምክንያቱም ለነገ ከመጨነቅ ነፃ የሚያወጣ እርሱ ነውና፡፡ እግዚአብሔርን ማመን ለድሆች ብፅዕና የሚያስፈልግ ዝግጅት ነው፡፡ እነርሱ እግዚአብሔርን ያያሉና፡፡