የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት

የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት

ክርስቲያናዊው መገለጥ… የማኅበራዊ ኑሮን ሕግጋት ጠለቅ አድርጐ ለመረዳት ያግዛል፡፡” ቤተ ክርስቲያን ስለሰው እውነቱን ሁሉ ተገልጦ የምታገኘው ከወንጌል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን የመስበክ ተልእኮዋን በምታከናውንበት ጊዜ በክርስቶስ ስም ስለ ሰብአዊ ክብር፣ ስለ ጥሪውና ስለሰዎች ሱታፌ ትመሰክራለች እንዲሁም ለመለኮታዊ ጥበብ በሚስማማ መንገድ ጽድቅን ሰላምን እንደሚሹ ሰዎችን ታስተምራለች፡፡

“መሠረታዊ ለሆነ ለግል መብቶች ወይም ለነፍሳት ደኅንነት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ” ቤተ ክርስቲያን ስለ ኤኮኖሚና ስለ ማኅበራዊ ጉዳይ ሥነ ምግባራዊ አስተያየትን ትሰጣለች፡፡ ሥነ ምግባራዊ ሥርዓትን በሚመለከት ቤተ ክርስቲያን ከፖለቲከኞች የተለየ ተልእኮ አላት፤ የጋራ ጥቅምን ለሚመለከቱት ምድራዊ ሁኔታዎችም ትኩረት ትሰጣለች፤ ምክንያቱም የመጨረሻ ግባችን ለሆነው ለገዢው በጐነት የተሰጡ ናቸውና፤ ምድራዊ ሃብቶችን በተመለከተ፣ ከማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶች አኳያ ትክክለኛ አመለካከቶችን ለመስገኘት ትጥራለች፡፡

የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ አስተምህሮ የተስፋፋው ወንጌል ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ኅብረተሰብ የፍጆታ እቃዎችን ለማምረት የሚያስችሉት አዳዲስ አደረጃጀቶች፣ አዲሰ ኅብረተሰብን የሚመለከት ጽንሰ ሀሳብ፣ መንግሥትና ሥልጣን፣ እንዲሁም አዲሰ የሰራረኛና የባለቤትነት ደንቦች ያለው ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ኅብረተሰብ ይዞ ከፊቱ በተደቀነበት በአሥራ ዘጠነኛው ምእተ ዓመት ነው፡፡ የምጣኔ ሐብትና ማኅበራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የትምህርት ቤተ ክርስቲያን መስፋፋት የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ዘለቄታ ያለው መሆኑን፤ አንዲሁም ሁልጊዜ ሕያውና እጅግ አስፈላጊ ለሆነው ለቤተ ክርስቲያን ትውፊትን ምስክርነቱን ይሰጣል፡፡

የቤተ ክርስቲያን ማህበሪዊ አስተምህሮ ቤተ ክርስቲያን በታሪክ ሂደት የሚከሰቱትን ሁኔታዎች በመንፈስ ቅዱስ ተራዳኢነት በኢየሱስ ክርስቶስ በተገለጸው ምላት አንጻር የምትተረጉምበት አንድ ራሱን የቻለ ትምህርት ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ምዕመናኑ ይበልጥ በእርሱ ለመመራት ዝግጁ በሆኑ ቁጥር አስተምህሮ መልካም ፈቃድ ባላቸው ሰዎች ዘንድ በቀላሉ ተቀባይነትን ሊያገኝ ይችላል፡፡

የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት የማሰላሰያ መርሖዎችን፣ የመመዘኛ ነጥቦችን ያቀርባል፣ የድርጊት መመሪያዎችን ይሰጣል፡፡

ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ሙሉ በሙሉ በኤኮኖሚአዊ እንቅስቃሴዎች የሚወሰንበት ማንኛውም ሥርዓት ለሰብአዊ ፍጡርና ለሥራዎቹ ባህርይ ተቃራኒ ነው፡፡

ትርፍን እንደ ኢኮኖሚ ብቸኛ ጠባይና የእንቅስቃሴዎች የመጨረሻ ግብ አድርጐ የሚወስድ ንድፈ ሃሳብ ከሥነ ምግባር አኳያ ሲታይ ተቀባይነት የለውም፡፡ ለገንዘብ የሚኖር የተዛባ ፍላጐት መጥፎ ውጤቶችን ማስከተሉ አይቀርም፡፡ ማኅበራዊውን ሥርዓት ለሚያውኩ በርካታ ግጭቶች ምክንያት ከሚሆኑ አንዱ አፍቅሮተ ንዋይ ነው፡፡

የግለሰቦችን የቡድኖችን መሠረታዊ መብቶች ለሕብረት ሥራ የሚያስገዛ ሥርዓት ሰብአዊ ክብርን ይፃረራል፡፡ ሰውን እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ትርፍ ማስገኛ መሣሪያ አድርጐ የሚቆጥር ማንኛውም ሥራ ሰውን ባሪያ ያደርጋል፡፡ ገንዘብን ወደማምለክ ያመራል፤ እግዚአብሔር የለም የሚለውን እምነት የማስፋፋት አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ “ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አይችሉም”

አምላክ የመካድ ርእዮተ ዓለማትን ቤተ ክርስቲያን አትቀበልም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ “ካፒታሊዝም”ን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት የሚንፀባረቀውን ግለኝነትንና የገበያ ሕግ በሠራተኛ ላይ ያለውን ፍፁም ቀደምትነትን አትቀበልም፡፡ ኤኮኖሚን በአንድ ማዕከላዊ አስተዳደር ሥር በሚያጠቃልል እቅድ ብቻ መቆጣጠር ማኅበራዊ ትስስርን ከመሠረቱ ያዛባል፡፡ ኤኮኖሚን በገበያ ሕግ ብቻ መቆጣጠር ማኅበራዊ ፍትሕን አያስገኝም፡፡ ምክንያቱም “በገበያ ሊሟሉ” የማይችሉ ብዙ ሰብአዊ ፍለጐቶች አሉና ነው፡፡ ከትክክለኛ የዋጋዎች ተዋረድና የጋራ ጥቅም አንፃር ገበያንና ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በአግባቡ መቆጣጠር የሚገደፍ ተግባር ነው፡፡