እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

5 አትግደል

አምስተኛይቱ ትእዛዝ

የካቶሊክ ትምህርተ ክርስቶስ ቁጥር 2258-2283 እና 2297-2317

“አትግደል”

“ለቀደሙት አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል፤የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል እኔ ግን እላችኋለሁ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፡፡” ማቴ. 5፡ 21-22

“የሰው ህይወት ቅዱስ ነው፤ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር የፈጣሪነት ስራ የተፈጠረ ሲሆን፣ አሁንም ልዩ በሆነ ግንኙነት ብቸኛና የመጨረሻ ግቡ ከሆነው ፈጣሪው ጋር ለዘላለም ይኖራል፡፡ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ የህይወት ጌታ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ በማንኛውም ምክንያት፣ በምንም አይነት፣ የንጹህ ሰውን ህይወት በቀጥታ የማጥፋት መብት ያለው ከቶውንም አንድም ሰው የለም፡፡”

ሰብአዊ ሕይወትን ስለማክበር

የተቀደሰው ታሪክ ምስክርነት

በቅዱስ መጽሐፍ አቤል በወንድሙ በቃየል ስለመገደሉ እንደተገለጸው የሰው ልጅ ታሪክ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአዳም ሀጢአት ምክንያት በሰው ልብ ንዴትና ቅናት እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ ይህም ሰው የወንድሙ ጠላት ሆነ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር የወንድማማችን ግድያ ክፋት በማስመልከት ለቃየል “ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምጽ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል፤አሁንም የወንድምህን ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ” አለው፡፡ ዘፍ. 4፡1ዐ-11

በእግዚአብሔር እና በሰው ልጆች መካከል ያለው ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ለሰብአዊ ሕይወት በሚለግሰው ስጦታና ሰው ለሚፈጽመው የግድያ አመፅ ማስታወሻዎች የተሳሰረ ነው፡፡

“… ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፤ የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ሰው ይፈስሳል፤ ሰውን በእግዚአብሔር መልክ ፈጥሮታልና፡፡” ዘፍ. 9፡5-6

በብሉይ ኪዳን ደም ሁልጊዜ የህይወት ቅዱስ ምልክት ሆኖ ይቆጠር ነበር፡፡ ይህ አስተምህሮ አስፈላጊነቱ ለሁልጊዜ ያለው ሆኖ እንዲኖር ነው፡፡

ቅዱስ መጽሐፍ በአምስተኛው ትእዛዝ የታገደውን ነገር ያብራራል፡፡ ይኸውም “ንጹሕንና ጻድቃን ሰው አትግደል” የሚል ነው፡፡ ሆን ብሎ በንጹህ ሰው ላይ የሚፈጸም ግድያ ለሰብአዊ ክብር ወርቃዊው ሕግ፣ ለፈጣሪ ቅዱስና ክፉኛ ተቃራኒ ይሆናል፡፡ ይህን ግድያ የሚከላከል ህግ በሁሉም ዘንድ የጸና ነው፡፡ ይህ ሕግ በማንኛውም ጊዜ እና በየትም ስፍራ በሰዎች ላይ ሁሉ አስገዳጅነት አለው፡፡

ጌታ በተራራው ላይ ባሰማው ስብከት “አትግደል” የሚለውን ትእዛዝ ካስታወሰ በኋላ፤ ንዴትን፣ ጥላቻንና በቀልን አወገዘ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ለሚመቷአቸው ሌላውን ጉንጫችውን አዙረው እንዲሰጡአቸውና ጠላቶቻቸውን እንዲያፈቅሩ ያሳስባል፡፡ ጌታ ራሱን ለመከላከል አልሞከረም፤ እንዲያውም ጴጥሮስን “ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ” ሲል ነግሮታል፡፡ ማቴ. 26፡52

ሕጋዊ መከላከል

ሰዎች ኅብረተሰቦች ራሳቸውን ለመጠበቅ የሚያደርጉት ሕጋዊ መከላከል በንጹሐን ላይ ሆን ተብሎ ከሚፈጸም ግድያ መከላከል ተለይቶ አይታይም፡፡ “ራስን ለመከላከል የሚደገግ ግብግብ (ትልግ) ሁለት ውጤቶች አሉት፤ እነርሱም የራስን ሕይወት ከራስ ማዳንና ለመግደል የመጣ አጥቂን መግደል ናቸው፡፡ አንደኛው የታለመ ሲሆን፣ ሁለተኛው ግን ሳይፈለግ የሚደረግ ነው፡፡”

ራስን መውደድ የስነ-ምግባር መሠረታዊ ደንብ ሆኖ ከጥናት ጀምሮ የነበረና አሁንም ያለ ነው፡፡ ስለዚህም በህይወት የመኖር መብትህን ማስከበር ሕጋዊ ነው፡፡ ህይወትን ለማዳን ሲከላከል በአጥቂው እስከ ሞት የሚደርስ ጉዳትን የሚፈጽም ሰው ጥፋተኛ ሆኖ አይቆጠርም፡፡

ሰው የገዛ ራሱን ለመከላከል ሲል አስፈላጊ ከሆነው በላይ ኃይል ቢጠቀም ድርጊቶ ሕጋዊ ድጋፍ አይኖረውም፡፡ የተሰነዘረበትን ጥቃት በተመጣጠነ ኃይል ከመከተ ግን ያደረገው መከላከል ሕጋዊ ነው፡፡ ሌላውን ሰው ላለመግደል ሲባል ራስን ለማዳን የተመጣጠነ እርምጃ ለመውሰድ ደግሞ የሚበጅ አይደለም፤ ምክንያቱም አንድ ሰው ከሌላ ሰው ህይወት ይልቅ ከራሱን ህይወት ለማዳን በይበልጥ የመሞከር ግዴታ አለበትና፡፡

ሕጋዊ መከላከል ለሌላው ህይወት፣ ለቤተሰብ ወይም ለሀረር ደህንነት ተጠያቂነት ላለበት ሰው መብት ብቻ ሳይሆን ታላቅ ኃላፊነትም ጭምር ነው፡፡

የጋራ ጥቅምን መጠበቅ ወራሪው (አጥቂው) ጉዳት እንዳያስከትል መከላከልን ይጠይቃል፡፡ በዚህ የተነሳ ጥንታዊው የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ሕገዊው አስተዳደር ወንጀለኞችን እንደድርጊታቸው  ክብደት የመቅጣት እንዲያም ሲል ያደረሱት ጥፋት እጅጉን የከፋ ከሆነ ደግሞ በሞት እስከ መቅጣት የሚያደርስ መብትና ኃላፊነት እንዳለው በሚገባ ይቀበላል፡፡ በሕጋዊ መንገድ ከስልጣን ላይ የሚገኙ ግለሰቦች ግፈኛ አጥቂ በሚመጣበት ጊዜ በሥልጣናቸው ስር የሚገኝ ማህበረሰብን ለማዳን ሲሉ በጦር መሣሪያ የመጠቀም መብት አላቸው፡፡

የቅጣት ዋና ዓላማ በጥፋት የመጣ ጉዳትን ለማስተካከል መሆን አለበት፡፡ ጥፋተኛው ቅጣቱን በፍቃደኝነት ከተቀበለ ቅጣሉ የሰርየት ዋጋ ይኖረዋል፡፡ ከዚህም በላይ ቅጣት የህዝብንና የግለሰቦችን ደኅንነት ለመጠበቅ ያስችላል፡፡ በሌላም በኩል ክፋ ጠባይን የመፈወስ ጥቅምም አለው በተቻለ መጠን ለጥፋተኛው ወገን መታረም አስተዋጽኦም ሊኖረው ይገባል፡፡

ነገር ግን ያለ ደም መፍሰስ የህዝብን ደኅንነት ከጥቃት መጠበቅ መከላከል ከተቻለ የመንግስት ባለስልጣናት ይህን መንገድ ቢከተሉ መልካም ነው፡፡ ምክንያቱም እንደዚህ ማድረግ ለጋራ ጥቅም የሚበጅ፣ ይልቁንም ደግሞ ለሰብአዊ ክብር ተገቢ የሆነ ዘዴ ነው፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት