ለንጽሕና የሚደረግ ተጋድሎ

ለንጽሕና የሚደረግ ተጋድሎ

ጥምቀት ተጠማቂውን ከኃጢአት ሁሉ የመንጻት ጸጋን ይሰጣዋል፡፡ ይሁንና ተጠማቂው ሰው ከስጋዊ ፍላጐቶችና ከተዛቡ ምኞቶች ጋር የሚያደርገውን መንፈሳዊ ተጋድሎ አያቋርጥም በእግዚአብሔር ጸጋም፣

ራስን መቆጣጠር እኔ በውስጤ መኖራቸውን ካላወቅኋቸው ኃይላት እንማሚመነጭ አስብሁ፡፡ አንተ ካልሰጠኸው በቀር ማንም ቢሆን ራሱን ማቆጣጠር እንደማይችል አለማወቄ … ጅልነት ግሯል፡፡ በውስጣዊ መቃሰቴ ከጆሮህ ደርሶ ሲሆን ኖሮና እኔም ከጥብቅ እምነት ጋር ጭንቀቴን ሁሉ ባንተ ላይ ጥዬ በነበር በእርግጥም ራስን መግዛትን ትሰጠኝ ነበር፡፡

ንጽሕና ራስን የመግዛት ዓይነተኛ አካል የሆነውን ትሕተናን ይጠይቃል፡፡ ትሕትና የሰውን ውስጠት ይጠብቃል፡ ይህም ማለት በምስጥር መጠበቅ የሚገባውን ጉዳይ አለመግለጥ ነው፡፡ በቀላል ስለመጠቃት አለመጠቃቱ ለሚመሠክርለት ለንጽሐ ድንግልናም አገልጋይ ነው፡፡ ትሕትና አንድ ሰው ሌሎችን እንዴት ባለ መንገድ ማየት እንዳለበት፣ ከሰዎች ክብርና ከአንድነታቸው ጋር በሚስማማ መልኩ እንዴት መቀበልና መስተናገድ እንደሚገባው ይመራዋል፡፡

ትሕትና የሰዎችን ምስጢርና ፍቅር ይጠብቃል፡፡ ትሕትና በፍቅር ግንኙነቶች ውስጥ ትእግሥትንና ቁጥብነትን ያጠነክራል፡፡ ትሕትና በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል መከናወን ያለበትን ምሉዕ የእርስ በርስ መሰጣጠት አስፈላጊ የሆነ ሁኔታዎችን መሟላትን ይጠይቃል፡፡ ትሕትና መልካም ፀባይ ነው፡፡ ትሕትና የአለባበስ ምርጫን ይወስናል፡፡ ትሕትና ጤናማ ያልሆነ ጉጉት ስጋት ባለበት ዝምታን ወይም ከመናገር መቆጠብን ያረጋግጣል፡፡ ትሕትና አስተዋይነትም ነው፡፡

የስሜቶች ትሕትና እንዳለ ሁሉ የአካልም ትሕትና አለ፡፡ ትሕትና ለምሳሌ ያህል በአንዳንድ የንግድ ማስታወቂያዎች ላይ ወሲባዊ ስሜትን የሚቀሰቅሱ ትዕይንቶችን ማሳየትን ወይም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ውስጣዊ አካልን በማሳየት ረገድ የሚሄዱበትል ያልተገባ ርቀት ይቃወማል፡፡ አዳዲስ አለባበስንና የወቅቱ ርእዮተ ዓለማት የሚያደርሱትን ተጽእኖ ለመቋቋም የሚያስችል የሕይወት መነገድን ይከተሉ ዘንድ ሰዎችን ያነሳሳል፡፡

የትሕትና መልኮች እንደየባህሉ ይለያያሉ፡፡ ነገር ግን ትሕትና በየትኛውም ሥፍራ ቢሆን ለሰው ልጅ የሚገባውን መንፈሳዊ ክብር መረዳት ሆኖ ይገለፃል፡፡ ትሕትና ራስን ከማወቅ ንቃተ ሕሊና ጋር ይወለዳል፡፡ ለልጆችና ለጐልማሶች ትሕትናን ማስተማር ማለት ለሰው ልጅ የሚገባ አክብሮትን በልባቸው መቀስቀስ ማለት ነው፡፡

ክርስቲያናዊ ንጽሕና የማኀበራዊውን ሁኔታ ንጽሕናን ይጠይቃል፡፡ ትሕትና የመገናኛ ብዙኃን የሚያቀርቧቸው ዝርጅቶች አክብሮትንና ቁጥብነትን ግምት ውስጥ የስገቡ እንዲሆኑ ይጠይቃል፡፡ የልብ ንፅሕና ከተስፋፋው የፍትወተ ሥጋ ምኞት ሲያላቅቅ ወሲባዊ ፍላጐትን ከሚያነሳሱና ከማይጨበጡ አይነት የጊዜ ማሳለፊያዎች ይርቃል፡፡

የሥነ ምግባር ቸልተኝነት በመባል የሚታወቀው ሁኔታ በተሳሳተ ነፃነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ለእውነተኛ ነፃነት እድገት በቅድሚያ ሥነ ምግባራዊ ሕግን ለመማር ፈቃደኛ መሆን ይሻል፡፡ ወጣቶች እውነትን፣ ልባምነትን የሰውን ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ ክብር የሚጠብቁ እንዲሆኑ መስተማር ያለባቸው መሆኑን መገመት አግባብ ያለው ሀሳብ ነው፡፡

“የክርስቶስ ብስራት (ወንጌል) የወደቀውን ሰው ሕይወትና ባሕል በየጊዜው ያድሳል፤ ሁል ጊዜ የማይጠፉትንመ ከኃጢአት አሳሳችነት የሚመነጩትን ስሕተትንና ክፋትን ይዋጋል፤ ያስወግዳልም፡፡ ወንጌል የሕዝቦችን ግብረ ገብነት ከማንፃትና ወደ ላቀ ደረጃ ከማድረስ አይቦዝንም፤ የሕዝቡንና የየዘመኑን መንፈሳዊ ልዕልናና ስጦታዎች በመውሰድ በላቁ ባህርያዊ ሃብቶች በመጠቀም ከውስጥ እንዲያብቡ ያደርጋቸዋል፤ በክርስቶስ ያበረታቸዋል ፍጹም የደርጋቸዋል፤ ወደነበሩበትም ይመልሳቸዋል፡፡”