እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ሆንብሎ የሚፈጸም ግድያና ጽንስ ማስወረድ

ሆንብሎ የሚፈጸም ግድያ

ሆንብሎ በቀጥታ የሚፈጸም ግድያ ከባድ ኃጢአት ሲሆን በአምስተኛው ትእዛዝ ተከልክሎአል፡፡ ነፍሰ ገዳዩና በፈቃደኝነት በነፍስ ገዳይነት ሥር የሚተባበሩ ሰዎች፣ በቀልን በመሻት ወደ ሰማይ የሚጮኸ ኃጢአትን ይፈጽማሉ፡፡

ሕፃናትን መግደል፣ ወንድምን መግደል፣ አባትን ወይም ዘመድን መግደል፤ እንዲሁም ከባለትዳሮች አንዱ ሌላውን መግደል፣ የቤተሰባዊ ሕይወት ባህሪይአዊ ትስስሮችን ስለሚበጥሱ በጣም ከባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡ ለሚወለደው ልጅ ወይም ለህዝብ ጤንነት አደገኛ የሆነ በሽታ አለበት በሚል ምክንያት በህዝብ ባለስልጣናት የታዘዘ ቢሆንም እንኳን ሰውን መግደል አይፈቀድም፡፡

አምስተኛ ትእዛዝ በተዘዋዋሪ መንገድ ሰውን ለማስገደል የሚከናወን ማንኛውም ነገር ይከለክላል፡፡ ስነ-ምግባራዊ ሕግ ያለከባድ ምክንያት ሰውን ለሞት መጋለጥ፣ እንዲሁም በአደጋ ላይ የሚገኝ ሰውን አለመርዳት ያወግዛል፡፡

ሰዎች በችግር ምክንያት በረሀብ ሲሞቱ እያየ እነርሱን ለመርዳት አንዳችም ጥረት አለማድረግ አንድ ህብረተሰብ ሊፈጽመው የሚችል አሳፋሪ በደልና ጥፋት ነው፡፡ አራጣ በማበደራቸውና እንዲሁም የስግስግብነት መንፈስ የሞላበት ንግዳቸው አማካይነት በኅብረተሰብ ደረጃ በሚኖሩ ወንድሞቻቸው ላይ ረሀብና ሞት እንዲከሰት የሚያደርጉ ሰዎች ሁሉ በተዘዋዋሪ መንገድ የነፍስ ገዳይነትን ሥር ስለሚፈጽሙ በኃላፊነት የሚያስጠይቃቸው ይሆናል፡፡ ያለ ፍላጐት የሚፈጸም ግድያ በስነ-ምግባራዊ አመለካከት ሲታይ ጥፋተኛ አያሰኝም፡፡ ነገር ግን የመግደል ፍላጐት ባይኖረውም እንኳን የተመጣጠነ ምክንያቶች ሳይኖሩት የሰውን ሕይወት ያሳለፈ ግለሰብ ከባድ ጥፋት እንዳጠፋ ያስቆጥረዋል፡፡

ጽንስ ማስወረድ

ሰብአዊ ሕይወት ልክ ከተፀነሰበት ጊዜ ጀምሮ መከበርና መጠበቅ አለበት፡፡ የሰው ልጅ በመጀመሪያ ሕልውናውን ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ መብቶች ያሉት ሰው ሆኖ መታወቅ አለበት፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ ንጹሕ ፍጡር በህይወት እንዲኖር የሚያስችሉት የማይሻሩ መብቶች አሉትና ነው፡፡

“በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፤ በማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፤ ለአሕዛብም በቢይ አድርጌሃለሁ፣”ኤር.1፡5 “እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም፡፡” መዝ. 139፡15

ከአንደኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነው ቤተ ክርስቲያን ማንኛውም ፅንስ ማስወረድ መጥሮ ተግባር መሆኑን ያወጀችው፡፡ ይህ አስተምህሮ ምንም አልተለወጠም፤ የሚለወጥም አይደለም፤ በቀጥታ ፅንስ ማሰወረድ፣ ማለትም ሆንብሎ ፅንስ ማስወረድ ሥነ ምግባራዊ ሕግን እጅግ በጣም የሚቃረን ተግባር ነው፡፡

“ፅንስን በማስወረድ ሕፃንን አትግደሉ፤ ከተወለደ በኋላም አትግደሉት፡፡” “የህይወት ጌታ የሆነ እግዚአብሔር ለሰዎች በጣም የላቀ ሕይወትን የመጠበቅ ተልእኮ ሰጥቶአል፡፡ ተልእኮ ሰብአዊ በሆነ ሁኔታ መፈጸም ያለበት ነው፡፡ ሰዚህ መሠረት ህይወት ከጽንሱ ጀምሮ ታላቅ እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል፡፡ ፅንስን ማስወረድና ሕፃናትን መግደል አስጸያፊ ወንጀል ነው፡፡”

ፅንስን በማስወረድ ተግባር የሚተባበር ግለሰብ ከባድ ወንጀል ይፈጽማል፡፡ ቤተ ክርስቲያን በሰው ህይወት ላይ በሚቃጣው በእንዲህ ዓይነት ወንጀል ላይ የምታስተላልፈው ቀኖናዊ ቅጣት ውግዘት ይባላል፡፡ “ፅንስን የሚያስወርድ ሰው ውግዘት የሚደርስበት” “በደሉን በመፈጸሙ” “በቀኖና ሕጉ ላይ በሠፈረሙ መሠረት” ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን “ስለዚህ ጉዳይ” የምሕረት ወሰን የመከለል ሐሳብ የላትም፡፡ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያን በተግባር የተፈጸመው ወንጀል በተገደለው ንጹሕ ግለሰብ ላይ እንዲሁም በወላጆቹና በመላው ሕብረተሰብ ላይ ያደረሰው ሊካስ የማይቻል ጉዳትን ትገልጻለች፡፡

ለእያንዳንዱ ንጹሕ ግለሰብ በህይወት ለመኖር ያለው የማይገሠሥ መብት የአንድ ሕዝብና የሚተዳደርበት ሕግ የሚመሠረትበት ቁልፍ ቁም ነገር ነው፡፡

የማይገሠሡት የሰው መብቶት በሞላ በሕዝባዊ ሥርዓትና በፖለቲካው መስተዳድር ዘንድ መታወቅና መከበር አለባቸው፡፡ እነዚህ ሰብአዊ መብቶች ለግለሰቦችና ለመላጆች የሚተው አይደሉም፡፡ ወይም በኅብረተሰብና በመንግሥት የሚደረገውን የጋራ ስምምነት የሚወክሉም አይደሉም፡፡ የሰው ልጅ ተፈጥሮ አካል ናቸው፡፡ የሰው መገኛ መሠረት በማድረግ አብረውት የተፈጠሩ ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ናቸው፡፡ አንድ ሰው ከተፀነሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከሚሞትበት ጊዜ ድረስ የመኖርና የአካላዊ ደህንነት መብት ያለው መሆኑን በዚህ አጋጣሚ መጥቀስ ተገቢ ነው፡፡

“ሕግ ሊያጐናጽፋቸው የሚገባውን የደህንነት መብት የተወሰኑ ሰዎች ቢነፈጉ በሕግ ፊት መንግሥት የሁሉንም እኩልነት አይቀበልም ማለት ነው፡፡ መነግሥት ኃይሉ እያለው የእያንዳንዱ ዜጋ መብቶች፣ በተለይም በጣም ደካማ የሆኑ ዜጐችን መበት በማስጠበቅ ላይ የማያውለው ከሆነ በሕግ የቆመው መንግሥት መሠረት  ይናጋል፤ ይዳከማል፡፡ ከጽንሱ ጀምሮ ላልተወለደው ልጅ ሊረጋገጥለት ከሚገባው አከብሮትና ጥበቃ በሚመነጭ ሕጉ ሆን ተብሉ ለሚደረግ ለእያንዳንዱ የልጅ መብት መጣስ ተገቢ ሕጋዊ ክልከላዎችን ሊያበጅ የግድ ነው”

ከተፀነሰበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ሰው መታየት ስላለበት፣ በተቻለ መጠን፣ እንደማንኛውም ሰው፣ ምኑም ሳይነካ በእንክብካቤና በሕክምና መጠበቅ አለበት፡፡

ቅድመ-ወሊድ የሚደረግ ምርመራ “የፅንሱንና የሽሉን ስብዕናና ህይወት እስካከበረና አንድን ግለሰብ ለመጠበቅ ወይም ለመፈወስ የታለመ እስከሆነ ድረስ ሕጋዊ ነው፡፡ እንደ ውጤቱ አስረጅነት፣ ፅንስን ለማስወረድ ታስቦ የተደረገ ከሆነ ግን ሥነ-ምግባራዊ ሕግን ክፉኛ ይቃረናል፤ የሕክምና ምርመራ የሞተ ፍርድ ሊሆን አይገባውም፡፡”

“የአንድን ሽል ህይወትና ማንነት የሚያከብረው፣ ከባድ ጉዳይ የማያስከትለውን ወይም የጤንነቱን ሁኔታ ለማሻሻል የሚደረገውን ወይም ግለሰባዊ የመኖር መብቱን ለማስጠበቅ የሚወሰድን እርምጃ ሁሉ ማንም ሰው ሕጋዊ አድርጐ መውሰድ አለበት፡፡

“ሰብአዊ ሽሎችን በማዘጋጀት እንደሚጣል ሥነ ፍጥረታዊ የምርምር መገለገያ ባልተገባ አገልግሎት ላይ ማዋል ሥነ ምግባር የጐደለው ድርጊት ነው፡፡” “የሰው ዝርያን በሚወስኑ ሕዋሶች ወይም ሕብለ-በራሔዎች ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚደረጉ ምርምሮች ፈውስን ፍለጋ የሚደረጉ ሳይሆን  ጾታን ወይም አስቀድሞ የተወሰነ ዝርያን ተመርኪዞ የተፈለገውን ዓይነት ሰው ለመፍጠር የታለሙ ናቸው፡፡ በዚህ አኳኋን የሚከናወኑ ተግባራት ልዩ የሆኑትንና የማይደገሙትን የሰው ግላዊ ክብር፣ እርሱነቱንና ማንነቱን የሚቃረኑ ናቸው፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት