እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ሰባተኛይቱ ትእዛዝ - አትስረቅ

አትስረቅ

ሰባተኛው ትእዛዝ የባልንጀራህን ሃብት በኃይል መውሰድ ወይም ማስቀረትንና በማንኛውም መንገድ ንብረቱን በሚመለከት እርሱን መበደልን ይከለክላል፡፡ ሰባተኛው ትእዛዝ ምድራዊ ሃብቶችንና በሰው ጉልበት የሚመረቱ ምርቶችን በመጠበቅ ረገድ ትክክለኛነትንና ፍቅርን ይጠይቃል፡፡ ለጋራ ጥቅም ሲባል ሰባተኛው ትእዛዝ የሃብቶችን ሁሉ የጋራ መሆን እንዲሁም የግል ሃብት ባለቤትነት መብት መከበርን ይጠይቃል፡፡ ክርስትያናዊ ሕይወትም እነዚህን ምድራዊ ሃብቶች ለእግዚአብሔርና ለወንድማዊ ፍቅር አገልግሎት እንዲውሉ ይጥራል፡፡

የተፈጥሮ ሃብቶች ለሁሉም መሰጠት እና የግል ሀብት ባለቤትነት

መጀመሪያ ላይ እግዚአብሔር ምድርንና የያዘቻቸውን ሃብቶች የሰው ልጅ በጋራ እንዲጠብቃቸው፣ በሥራ አማካይነት እንዲቆጣጠራቸው ፍሬዎቻቸውንም እንዲበላ በአደራ ሰጥቶታል፡፡ የፍጥረት ሃብቶች በጠቅላላው ለሰው ሁሉ ጥቅም የታቀዱ ናቸው፡፡ ነገር ግን ሰዎች በድኽነት ሥጋትና በአመፃ ፍራቻ ከመከበባቸው የተነሳ የሕይወታቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ ምድርን በመካከላቸው ተከፋፈሏት፡፡ የሃብት ክፍፍል የሰዎችን ነፃነትና ክብር ለማረጋገጥ እያንዳንዱን ሰው በኃላፊነቱ ሥር የሚገኙ ሰዎችንና የራሱን ፍላጐት ያሟላ ዘንድ የሚያስፈልግ አሰራር ነው፡፡ ክፍፍሉ በሰዎች መካከል ባሕርይአዊ ትብብር እንዲሰፍን የሚያስች መሆን አለበት፡፡

ሰርተው ያፈሩትን ይሁን ከሌሎች በውርስና በስጦታ ያገኙት ሃብት ባለቤት የመሆን መብት መሬት መጀመሪያ ላይ ለሰው ልጅ ሁሉ በስጦታነት መሰጠቷን አይሽርም፡፡ ምንም እንኳ የጋራ ጥቅምን ማጐልበት የግል ሃብት የማፍራትና ባለቤት የመሆን መብትን መከበር የሚጠይቅ ቢሆንም የሃብት የሁሉም መሆን በመጀመሪያ የነበረ ነው፡፡

“ሰው በነገሮች በሚገለገልበት ወቅት፣ የግሉ የሆኑ ውጫዊ መገልገያዎች በህጋዊ መንገድ የእርሱ ቢሆንም እንኳን፣ የእርሱን እንደሚጠቅሙት ሁሉ ሌሎችም እንደሚጠቅሙ በማሰብ፣ የእርሱ የራሱ ብቻ ሳይሆኑ የጋራም እንደሆኑ አድርጐ ማየት አለበት፡፡” የየትኛውም ንብረት ባለቤትነት ባለ መብቱን ያምላክ አቃቢ ያደርገዋል፤ ንብረቱን የሚያለማና ጥቅሙን ለሌሎች በተለይ መጀመሪያ ለቤተሰቡ የማካፈል ሃላፊነት ይሰጠዋል፡፡

ቁሳዊ ወይም ቁሳዊ ያልሆኑ የምርት መገልገያዎች ማለትም እንደ መሬት፣ ፋብሪካዎች ገቢራዊ ወይም ጥበባዊ ችሎታዎች የመሳሰሉ ነገሮች ባለቤቶቻቸው ብዙሃኑን በሚጠቅሙ መንገዶች ይገለገሉባቸው ዘንድ ያስገድዳቸዋል፡፡ የምርት ውጤቶችን ለአገልግሎትና ለፍጆታ ለሚያከማቹ ባለሃብቶች የተሻለውን ክፍል ለእንግዶች፣ ለህሙማንና ለድሆች በማኖር እየመጠኑ ሊገለገሉባቸው ይገባል፡፡

ለጋራ ጥቅም ሲባል የፖለቲካ ስልጣን የባለንብረትነትን መብት ሕጋዊ አተገባበር የመቆጣጠር ኃላፊነትና መብት አለው፡፡

ሰዎችንና ንብረቶቻቸውን ማክበር

ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በሚመለከት ሰብአዊ ክብርን ለመጠበቅ ለዚህ ዓለም ንብረት የሚኖረንን መሻት እራሳችንን በመቆጣጠር እንገታ ዘንድ ይጠይቃል፤ እንደዚሁም ሁሉ የባልንጀሮቻችንን መብቶች ለመጠበቅና የሚገባውን ለመስጠት ምግባረ-ጽድቅ ያሻናል፤ ወርቃማው ህግ በሚያዘው መሰረትና “ሀብታም ሲሆን … በርሱ ድህነት ባለጠጐች ትሆኑ ዘንድ ስለእናንተ ድሀ ሆነ” በማለት ቃሉ እንደሚመሰረክረው የጌታ ልግስና በመፈተን ግብራዊ በሚሆን አንድነት ይህንኑ መፈጸም አለብን፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት