እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ሰላምን መጠበቅና ጦርነትን ማስወገድ

ሰላምን መጠበቅ

ሰላም

ጌታችን “አትግደል” የሚለውን ትእዛዝ በማስታወስ የልብ ሰላም እንዲኖር ይጠይቃል፤ የግብረገብነት ተቃራኒ የሆኑ እስከ መግደል የሚደርሱ ቁጣና ጥላቻን ያወግዛል፡፡ ቁጣ መበቀልን መሻት ነው፡፡ “ሰውን ስለበደለ እሱን ለመጉዳት የሚደረግ የመበቀል ምኞት ተገቢ አይደለም” ነገር ግን “ክፋትን ለማረምና ፍትሕን ለማጽናት” ካሳ እንዲከፍል ማድረግ የሚመስገን ሥራ ነው፡፡ ቁጣ ሆን ብሎ ባልንጀራን ለመግደል ወይም እሱን ክፉኛ ለማቁሰል ወደሚገፋፋ ፍላጐት ከደረሰ በፍቅር ላይ ከባድ አመጽ እንደፈጸመ ይቆጠራል፣ ድርጊቱ ታላቅ ኃጢአት ነው፡፡ ጌታም “… በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል” ይላል፡፡ ማቴ. 5፡22

ሆነብሎ የሚፈጸም ጥላቻ ፍቅርን ይጻረራል፡፡ ባልንጀራን መጥላት ማለት በእርሱ ላይ ጉዳት እንዲደርስ ሆን ብሎ መመኘት ነው፡፡ “እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ፣ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ ለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ” ማቴ.5፡ 44-45

የሰብአዊ ህይወት ክብርና እድገት ሰላምን የሻል፡፡ ጦርነት ባለመኖሩ ወይም የባለጋራዎች ኃይል በለመመጣጠኑ ሰላም አለ ማለት አይደለም፡፡ የሰዎች ጥቅምና በሰዎች መካከል የሚካሄዱ ነፃ ግንኙነቶች በሚገባ ካልተጠበቁ፣ ለሰዎች ሰብአዊ ክብርና ለሕዝቦች ከበሬታ ካልተሰጠ እንደሁም በሰዎች መካከል የጋለ ወንድማማችነት ካልተመሠረተ፣ በምድር ላይ ሰላም ሊገኝ አይችልም፡፡ ሰላም “የሥርዓት ርጋታ” ማለት ነው፡፡ ሰላም የጽድቅ ሥራና የፍቅር ውጤት ነው፡፡

ምድራዊ ሰላም መሢሐዊው “የሰላም አለቃ” የሆነው የክርስቶስ ሰላም አምሳሉና ፍሬው ነው፡፡ እርሱ በመስቀሉ ደም “ጥልን በሥጋው ገድሎ” ኤፌ 2፡16 ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር በማስታረቅ ቤተክርስቱያኑን የሰው ልጅ አንድነትና ከእግዚአብሔር ያለው ሕብረት ምሥጢር አደረጋት፡፡ “እሱ ሰላምችን ነው፡፡” ኤፌ 1፡14 “የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው” ማቴ. 5፡9 ሲልም አውጇል፡፡

ሰብአዊ መብቶችን ለማስጠበቅ፣ የአመፅን ሥራና የደም መፋሰስን የሚያወርዙ ሁሉ በተለይም በጣም ደካማ የሆኑ ወገኖች ያላቸውን መከላከያ በመጠቀም ወንጌላዊውን ፈቅር የመሰክራሉ፡፡ ቢሆንም ይህን ማለት የምንችለው ድርጊቱ የሌሎች ሰዎችና ሕብረተሰቦች መብቶችን የማይጐዳ እስከሆነ ድርስ ነው፡፡ ሰዎቹ ከሚያስከትለው ጥፋትና ሞት ጋር ወደ አመፃ መመለስ ሊያደርስ ስለሚችለው አካላዊና ሞራላዊ አደጋ ክብደት ተቀባይነት ያለው ምሥክርነትን ይሰጣሉ፡፡

ጦርነትን ማስወገድ

አምስተኛው ትእዛዝ ሆን ብሎ የሰውን ነፍስ ማጥፋትን ይከላከላል፡፡ ጦርነት ሁሉ ክፋትንና በደልን ስለሚያስከትል መለኮታዊው በጐነት ከጥንታዊ የጦርነት ባርነት ነፃ ያወጣን ዘንድ ቤተ ክርስቲያን እያንዳንዱ ሰው እንዲጸልይ በጥብቅ ታሳስባለች፡፡

ዜጐች ሁሉ፣ እንደሁም መንግሥታት ሁሉ ጦርነት የወገድ ዘንድ  የመሠራት ግዴታ አለባቸው፡፡ ሆኖም “በዓለም አቀፍ ደረጃ የጦርነት አደጋን ማገድ  የሚችል በቂ ችሎታ ያለው ዓለም አቀፍ አካል ከሌለ፣ ሰላማዊ ጥረቶች ሁሉ ከከሸፉ መንግሥታታ ራሳቸውን የሚከላከሉበት ሕጋዊ መብት ሊነፈጋቸው አይችልም፡፡”

በወታደራዊ ኃይል እራስን መከላከል ጥብቅና ቅልቅ ግምገማ ይጠይቃል፡፡ እንደዚህ አይነቱ ከባድ ውሳኔ ሥነ ምግባራዊ ሕጋዊነትን የሚመለከቱ በርካታ ጉዳዮችን ያገናዘበ መሆን አለበት፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሁኔታ፡-

-    ወራሪን በአገር ወይም በሕብረተሰብ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት፤ ዘላቂ የከፋና እርግጠኛ መሆኑን ማረጋገጥ፤

-    ይህን ወረራ  ለማቆም የተደረጉ ጥረቶች ሁሉ እንደመከኑ ወይም ፍሬ አልባ እንደሆኑ መረጋገጥ፤

-    ድልን የማግኘት ተስፋው ከፍተኛ መሆን፤

-    ጥቅም ላይ የሚውለው መሣሪያ እንዲቆም ከተፈለገው ጥፋት ውጤት የከፋ ቀውስ ማስከተል የለበትም፡፡ ይህን ጉዳይ በመወሰን ረገድ የዘመናውያኑ የጥፋት መሣሪያዎች ኃይል ከግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል፡፡

እነዚህ መሠረታዊ ነጥቦች በተለመደውና “ሕጋዊ ጦርነት” በሚለው ትምህርት ንድፈ ሃሳብ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙ ናቸው፡፡

ከሥነ ምግባራዊ ሕጋዊነት አኳያ እነዚህን ሁኔታዎች የመገምገሙ ኃላፊነት የጋራ ጥቅምን በተመለከተ ኃላፊነት ላለባቸው ሰዎች አስተዋይ ፍርድ የተተወ ነው፡፡

በዚህ ዓይነት አጋጣሚ የመንግሥት ባለሥልጣናት ለአገር መከላከያ የሚያስፈልጉ ግዴታዎችን ሁሉ እንዲፈጽሙ ዜጐቻቸውን የማዘዝ መብትና ኃላፊነት አለባቸው፡፡ የጦር ኃይል ባልደረቦች በመሆን አገራቸውን ለማገልገል ቃል የገቡ ሰዎች የሕዝቦቻቸውን ፀጥታና ነፃነት አገልጋዮች ናቸው፡፡ ስለዚህ ተግባራቸውን በሚገባ ካከናወኑ እነርሱም በበኩላቸው ሰላምን ለመመሥረትና ለጋራ ጥቅም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በሚገባ ያበረክታሉ፡፡

የሕዝብ ባለሥልጣናት ወታደር በመሆን የጦር መሣሪያ ለመታጠቅ ኅሊናቸው ለማይፈቅድላቸው ሰዎች ሌላ ተገቢ ደንብ ሊያወጡላቸው ይገባል፡፡ ሆኖም እነዚህ ሰዎች በሌላ መስክ በመሰማራት ማህበረሰቡን የማገልገል ግዴታ አለባቸው፡፡

ቤተክርስቲያን ሰብአዊ አእምሮ በጦርነት ጊዜም ቢሆን የሥነ ምግባር ሕግ ተፈጻሚነት እንዳለው ያረጋግጣሉ፡፡ “በአሳዛኝ መልኩ ጦርነት ቢከፈትም በሁለት ተዋጊዎች መካከል የሚበረገው ሁሉ ሕጋዊ ነው ማለት አይደለም፡፡

ቡርጊሶች/ሲቪሎች፣ የቆሰሉ ወታደሮችና ምርኮኞች ከበሬታና ሰብአዊ ርኅራኄ በተሞላበት ሁኔታ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ የመንግሥታትን ሕግና መሠረት ያደረጋቸውን ዓለም አቀፍ መርሖዎች የሚቃወሙ ድርጊቶች እንዲሁም እነዚህን ድርጊቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ የሚያደርግ ትእዛዝም ጭምር ወንጀሎች ናቸው፡፡ ጨፍን ታዛዥነትን ሽፋን በማድረግ እነዚህን ድርጊቶች የሚፈጽሙ ሰዎችን ከተጠያቂነት አያመልጥም፡፡ በዚህ መሠረት አንድን ሕዝብ፤ ብሔር ወይም ሕዳጣን ጐሣዎችን ፈጽሞ ማጥፋት ከባድ ኃጢአት በመሆኑ መወገዝ አለበት፡፡ማንም ቢሆን ሕዝብን የማጥፋት ትዕዛዝን ይቃወም ዘንድ ግብረ-ገብነት ያዛል፡፡

“ያለምንም ልዩነትና አስተያየት ከተሞችን ወይም ሰፋፊ አካባቢዎችን ከነነዋሪዎቻቸው ለመደምሰስ የታቀደ ማናቸውም የጦርነት ሥራ በእግዚአብሔርና በሰዎች ላይ የሚፈጸም ወንጀል ሰለሆነ ያለአንዳች ማመንታትና መጠራጠር በጥብቅ መወገዝ አለበት፡፡” የዘመኑ ጦርነት አደጋ የሳይንሳዊ መሣሪያዎችን ባለቤት የሆኑ ወገኖች፣ በተለይም መርዛም የሆኑ የአውቶሚክ፣ የባዮሎጂካል ወይም የኬሚካል መሣሪያዎች ባለንብረት በመሆናቸው ይህም መሰሉ ወንጀል የመፈጸም ዕድል ሊፈጥርላቸው ይችላል፡፡

ብዙ ሰዎች እንደሚገምቱት የጦር መሳሪያዎችን ማከማቸት ባለጋራዎችን ለጦርነት እንዳይነሳሱ ለመግታታ የሚያስችል ዘዴ ነው፡፡ እንደነሱ አስተያየት ይህ ዘዴ በመንግሥታታ መካከል የሰላም ዋስትናን የሚያስገኝ ስልት ነው፡፡ ይህ ጦርነትን የማስቀረት ስልት ጠንከር ያለ ሥነ ምግባራዊ ቅሬታን ፍጥሮአል፡፡ ጦር መሣሪያ የማምረት እሽቅድምድም ከቶውንም የሰላም ዋስትና አይሆንም፡፡ ይልቁንም የጦርነትን መንስዔዎችን ከማጥፋት ይልቅ ሊያባብሳቸው ይችላል፡፡ በይበልጥ ዘመናዊ የሆኑ መሣሪያዎችን ለማምረት ከፍተኛ መዋዕለ-ንዋይ ማፍሰስ የተቸገሩ ሕዝቦችን ለመርዳት የሚደረገውን ጥረት በየሰግክላል፡፡ የሕዝቦችን ዕድገት ይጐዳል ከመጠን በላይ ዘመናዊ መሣሪያዎችን መጠቀም ለፍጥጫ መንስዔ ከመሆን ባሻገር ሁኔታውን ያባብሳል፡፡

የጦር መሣሪያዎችን ማምረትና መሸጥ የመንግሥታትና የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ የጋራ ቅጥም ይጐዳል፡፡ ስለዚህም የሕዝብ በባለሥልጣናት እነዚህን ሁኔታዎች የመቆጣጠር መብትና ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ዘለቄታ የሌላቸው ግላዊ ወይም የጋራ ጥቅሞች በሕበክቦች መካከል አመጻንና ግጭትን የሚያስፋፋ እንዲሁም የአለም አቀፋዊውን የሕግ ሥርዓት አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን ተገቢ ሊያሰኙ ወይም ሕጋዊነትን ሊያላብሱ አይችሉም፡፡

በሰዎችና በንግሥታታ መካከል የሰፈነው ግፍ፣ ከጠን ያለፈ የኤኮኖሚና የማህበራዊ ፍትሕ መዛባት፣ ቅናት፣ አለመተማመነና ትዕቢት ያለማቋረጥ የሰላም ጠንቅ ሲሆኑ፣ ጦርነቶችም ያስከትላሉ፡፡ እነዚህን ሕውከቶች የሚያነሳሱ ሁኔታዎችን ለማስወገድ የሚደገግ ማንኛውም ነገር ሰላምን ለማስፈንና ጦርነትን ለማስቀረት ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

ሰዎች በኃጢአተኛነታቸው እስከቀጠሉ ድረስ ክርስቶስ ዳግም እስኪመጣ ድረስ በጦርነት ስጋት ውስጥ ይኖራሉ፤ ሆኖም በፍቅር እርስ በርሳቸው ከተባበሩ ኃጢአትን ድል ሥያደርጋሉ አመፃም ይሸነፋል፤ ያኔ “ሰይፋቸውንም ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሳም፤ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም፡፡” የሚል ቃል ይፈጸማል፡፡ ኢሳ. 2፡4

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት