እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ቤተሰብና ሕብረተሰብ

ቤተሰብና ሕብረተሰብ

ቤተሰብ የማህበራዊ ህይወት መሠረታዊው ኅዋስ ነው፡፡ ቤተሰብ ባልና ሚስት በፍቅርና በህይወት ስጦታ ራሳቸውን እንዲሰጡ የተጠሩበት ተፈጥሮአዊ ሕብረተሰብ ነው፡፡ በቤተሰብ ውስጥ የሚጀመሩት፤ ኃላፊነትን የመሸከም ሥልጣን፣ ጽኑ አቋምና የግንኙነት ሕይወት በሕብረተሰብ ውስጥ የነፃነት፣ የዋስትና የወንድማማችነትን መሠረት ይጥላል፡፡ ቤተሰብ፤ ሰው ከሕፃንነት ጀምሮ የሥነ መግባርን ጥቅም የሚማርበት፣ እግዚብሔርን የሚያከብርበትን ነፃነትን በመልካም ተግባር ላይ የሚያውልበት ማሕበር ነው፡፡ ቤተሰባዊ ሕይወት ወደ ማሕበራዊ ሕይወት መሸጋገሪያ ነው፡፡

ቤተሰብ አባላት በችግር ላይ የሚገኙ ወጣቶችን፣ አረጋውያንን፣ ሕሙማንን፣ አካለ ስንኩሎችንና ድሆችን የመርዳት ኃላፊነት ለመቀበል የሚማሩበትን አርአያነት ያለውን ሕይወት መኖር አለበት፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ምክንያት ይህን እርዳታ ማበርከት የማይቻላቸው ቤተሰቦች ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህም እነዚህን ችግሮኞች በድጐማ መልክ መርዳት ሌሎች ሰዎችን፣ ቤተሰቦችንና ኅብረተሰቦችን ይመለከታል፡፡ “ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ድሀ አደጐችን መበለቶችን በመከራቸው መጠየቅ፣ በዓለምም ላለመቆሸሽ ራስን መጠበቅ ነው” ያዕ. 1፡12

ቤተሰብ ተገቢ በሆነ ማሕበራዊ እርምጃዎች ድጋፍና ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል፡፡ ቤተሰቦች ኃላፊነታቸውን መወጣት የሚያቅታቸው ጊዜ ሌሎች ማሕበራዊ አካላት የቤተሰብን ተቋም የመርዳትና የመደገፍ ግዴታ አለባቸው፡፡ ታላላቅ ማሕበረሰባት የድጐማን መመሪያ ሽፋን በማድረግ አለአግባብ በቤተሰቦች መብት ከመጠቀም ወይም በእነርሱ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ ከመግባት መቆጠብ አለባቸው፡፡

ቤተሰብ የሕብረተሰብ ሕይወትና ደህንነትን የማጐልበት ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ ሕብረተሰብ ጋብቻንና ቤተሰበን የመደገፍና የማጠናከር ዓይነተኛ ኃላፊነት አለበት፡፡ ማንግስት “የጋብቻንና የቤተሰብን እውነተኛ ባሕርይ ለይቶ የማወቅና የመጠበቅ፣ የማሳደግ፣ የሕዝበን ግብረገብነት የመንከባከብ፣ የቤተሰብን ብልጽግና ከፍ የማድረግ” ታላቅ ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን መገንዘብ አለባቸው፡፡

ፖለቲካዊ ማኅበራዊ ቤተሰብን የማክበር፣ የመርዳት በተለይም ከዚህ በታች የተመለከቱንት ጉዳዮች የማሟላትና የማረጋገጥ ግዴታ አለበት፡፡

  • ቤተሰብን የመመስረት፣ ልጆችን የማፍራትና የራሱ ሥነ ምግባራዊ፣ ሃይማኖታዊ እምነት በሚፈቅዱት መሠረት የማሳደግ ነፃነት፤
  • የጋብቻን ትስስር ጽናተና የቤተሰብን ተቋም መጠበቀ፤
  • ሃይማኖትን በነፃነት መግለጽ፤
  • የግል ንብረት ባለቤትነት፣ የነፃ ንግድ ድርጅቶችን የማቋቋም፣ ሥራንና መኖሪያ ቤትን የማግኘት እንዲሁም የመሰደድ መብትን ማግኘት፣
  • የአገሪቷ ተቋማትን አቅም በሚፈቅዱት መሠረት ሕክምናን የማግኘት የአረጋውያን እንክብካቤ የማግኘት፣ የቤተሰብ ጥቅማ ጥቅሞች የመከበት መብት፤
  • ጸጥታና ጤንነትን መንከባከብ፣ በተለይ አደንዛዥ ዕፅችን፣ ሥነ-ምግባር የጐደላቸው ሥነ ጽሑፎችን (ፐርኖግራፊ) የመጠጥ ሱሰኛነት ከሚያስከትሉአቸው አደጋዎች መከላከል፤
  • ከሌሎች ቤተሰቦች ጋር ማሕበራትን የማቋቋም ነፃነትና በመንግስት ውስጥ ውክልናን የማግኘት መብት ናቸው፡፡

አራተኛው ትእዛዝ በሕብረተሰብ ውስጥ ያሉ ሌሎች ግንኙነቶችን ያብራራል፡፡ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ስንመለከት የወላጆቻችንን ልጆች እናያለን፡፡ የአጐቶቻችንንና የአክስቶቻችንን ልጆች ስንመለከት የአያቶቻችንን የልጅ ልጆች እናያለን፤ ዜጐች ወንድሞቻችንን ሰንመለከት የአገራችንን ልጆች እናያለን፣ የተጠመቁትን ባየን ጊዜ ደግሞ የእናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ልጆችን እናስተውላለን፡፡ ማንኛውንም ሰው ስናይ ደግሞ “አባታችን ሆይ!” ተብሎ መጠራት የሚሻውን የእርሱን ወንድ ወይም ሴት ልጅ እንመለከታለን፡፡ በዚህም መሠረት ከባልንጀሮቻችን ጋር ያሉን ግንኙነቶች በባሕርይአቸው ግላዊ ናቸው፡፡ ባለንጀራ በሕዝብ ጥርቅም መካከል የሚገኝ “ነጠላ” አይደለም፡፡ እሱ ተለይቶ በሚታወቅባቸው መገኛዎቹ አማካይነት ልዩ ጥንቃቄ ከበሬታ የሚገባው “አንቱ” የተሰኘ ነው፡፡

የሰብአዊ ማኅበራት መሠረት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱን በተገቢው መንገድ ማስተዳደር፣ መብቶችን በማረጋገጥና ውልን የመሳሰሉ ግዴታዎችን በመስፈጸም ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ በአሠሪዎችና ሠራተኞች፣ በአስተዳዳሪዎችና በዜጐች መካከል ያሉ ትክከለኛ ግንኙነቶች ፍትሕንና ወንድማማችነትን አስመልክቶ የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር ጋር የሚሄድ የተፈጥሮ መልካም ፈቃድን ይጠይቃሉ፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት