እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ባለሥልጣናትና የዜጎች ግዴታ

ባለሥልጣናት

የእግዚአብሔር አራተኛው ትእዛዝ በኅብረተሰብ ውስጥ ስለ እኛ ጥቅም ከአምላክ ሥልጣን የተቀበሉ ሰዎችን ሁሉ እንድናከብር ያዝዛል፡፡ ይህ ትእዛዝ የሥልጣንን እርካብ የተቆናጠጡትንም ሆነ ከእርሱም ተጠቃሚ የሚሆትን ሰዎች ኃላፊነት ያብራራል፡፡

የባለሥልጣናቱ ኃላፊነት

ሥልጣን የተቀበሉ ሰዎች ሹመታቸውን እንደ አገልግሎት አድርገው በመቁጠር ሊሠሩበት ይገባል፡፡ “ከእናንተ በታላቅ ለመሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፡፡” ማቴ. 2ዐ፡26 ሥልጣንን የመተግበር ጉዳይ በሥነ-ምግባር የሚመዘነው መሠረቱ መለኮታዊ ከመሆኑ፣ ከምክንያታዊ ባህርዩና ልዩ ከሆነው ግቡ አንጻር ነው፡፡ ስለዚህም ለሰብአዊ ክብር ለባሕርይአዊ ሕግ ተቃራኒ የሆነን ነገር እንዲፈጸም ማዘዝ ወይም መደንገግ የሚችል ማንም የለም፡፡

የሥልጣን ተግባር ላይ መዋል ሁሉም ኃላፊነቱንና ነፃነቱን ያቀላጥፍ ዘንድ ለማስቻል ለትክክለኛ የዕሴቶች ቅደም ተከተል ውጫዊ መገለጫን ለማስገኘት ነው፡፡ ሥልጣንን የጨበጡት ክፍሎች ስምምነትና ሰላም ይሰፍን ዘንድ የእያንዳንዱን ሰው ፍላጐቶችና አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ በማስገባት ፍትሕን በጥበብ ማዳረስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ባለሥልጣናት የሚያሳልፏቸው ደንቦችና ውሳኔዎች የግል ጥቅምን ከሕብረተሰቡ ጥቅም በተፃራሪ በማስቀመጥ ፈተና ውስጥ የሚጥሏቸው መሆን የለባቸውም፡፡

የፖለቲካ ባለስልጣናት መሠተታዊ የሆኑ ሰብአዊ መብቶችን የማክበር ግዴታ አለባቸው፡፡ ፍትሕን ርኅራኄ በሰፈነበት ኅሊና የእያንዳንዱን ሰው በተለይም የቤተሰቦችንና የችግረኞችን መብቶች በሚያከብር መልኩ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለዚጐች የሚሰጡ ፖለቲካዊ መብቶች ለጋራ ጥቅም በሚበጅ መልኩ ተግባራዊ መሆን ይገባቸዋል፡፡ እነዚህ መብቶች ሕጋዊና በቂ ምክንያቶች ካልተገኙ በስተቀር በሕዝብ ባለሥልጣናት ከቶውንም ሊታገዱ አይችሉም፡፡ ፖለቲካዊ መብቶች ተግባራዊ የሚሆኑበት ምክንያት የአገርንና የኅብረተሰብን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው፡፡

የዜጐች ግዴታ

ከባለሥልጣናት ሥር የሚተዳደሩ ሰዎች የበላዮቻቸውን የእግዚብሔር ወኪሎች የስጦታዎቹም አቃብያን አድርጐ የሾማቸውን አገልጋዮች እንደሆኑ መቀበል አለባቸው፡፡ “ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ …፡፡ አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉት” 1ጴጥ 2፡ 13፣16 በዜጐች የሚፈጸም ታማኝነት ያልተለየው ትብብር የሰዎችን ክብር የሕብረተሰቡን ደኅንነት የሚጐዱ ሁኔታዎች በሚፈጠሩበት ጊዜ ተገቢ ሒስ የመሰንዘር መብትን፣ አንዳንድ ጊዜም ሒስን የመሰንዘር ግዴታንም ያካትታል፡፡

ዜጐች ለሕብረተሰብ የጋራ ጥቅም ሲባል የእውነት፣ የፍትሕ፣ የአንድነትና የነፃነት መንፈስ በሰፈነበት ፈቃደኝነት ለሕዝብ ባለሥልጣናት ድጋፍን የማበርከት ግዴታ አለባቸው፡፡ አገርን የመውደድና የማገልገል መንፈስ የሚመጣው ውለታን ለመመለስ ግዴታና ከፍቅር ነው፡፡ ለሕጋዊ ባለሥልጣናት መታዘዝና ለጋራ ጥቅም መሠትን ዜጐች በፖለቲካዊው ማሕበረሰብ ውስጥ ተገቢውን ሚና ይጫወቱ ዘንድ የግድ ይላል፡፡

ለባለሥልጣት መታዛዝና ለየጋራ ጥቅም በጋራ የመሰለፍ ኅላፊነት፣ ከሥነ-ምግባር አኳያ ሲታይ ቀረጥ የመክፈልን፣ የማራጭነትን መብት ተግባራዊ የማድረግንና አገርን የመከላከል ግዴታ ያስከትላል፡፡

“ለሁሉም የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፣ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፣ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ፡፡” ሮሜ. 13፡7

ክርስቲያኖች በአገራቸው የሚኖሩት እንደ መጻተኞች በመሆን ነው፡፡ በሁሉም ነገሮች ውስጥ እንደ ዜጐች ይሳተፋሉ፤ እንደ መጻተኞች ግን ሁሉንም ይችላሉ… ለተደነገጉት ሕጐች ይታዘዛሉ፤ ሕይወታቸው ግን ከሕግጋቱ የላቀ ነው… እግዚአብሔር የሰጣቸው ስፍራ እጅግ የከበረ ነውና ሊተውት አይቻላቸውም፡፡

ሐዋርያው “እግዚብሔርን በመምሰዋና በጭምተኝነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር” ስነ ነገሥታትና ስለ መኳንንት ሁሉ ጸሎትና ምስጋና ለእግዚአብሔር እንድንቀርብ በጥብቅ ያሳስበናል፡፡

በኢኮኖሚ የበለጸጉ መንግስታት፣ ሰዎች በትውልድ አገራቸው ጸጥታና ላመተዳደሪያ የሚሆን ገቢ በመጣታቸው ወደ አገራቸው ሲገቡ ተቀብለው የተቻላቸውን እርዳታ መስጠት አለባቸው፡፡ ባለሥልጣናት እንግዳን ለተቀባዮቹ ጥበቃና እንክብካቤ በአደራነት የሚያስረክበው ተፈጥሮአዊ መበት ማክበሩን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ የፖለቲካ ባለሥልጣናት በጋራ ጥቅም ላይ ኃላፊነቶች ስላሉአቸው፣ ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ሰዎች በተለይም ስደተኞች በሚገቡበት አገር የሚፈጽሙአቸው ግዴታዎችን በተመለከተ ሕጐችን መደንገግ ይችላሉ፡፡ ስደተኞችም በእንግድነት በሚኖሩበት አገር ቁሳዊና መንፈሳዊ ቅርስን በምስጋና መንፈስ የማክበር፣ ለአገሩ ሕግ የመታዘዝና ሕዝባዊ ኃላፊነትን ለማሳካት የመተባበር ግዴታ አለባቸው፡፡

ዜጐች የሕዝብ ባለስልጣናት ስነ-ምግባራዊ ደንብን፣ የሰዎች መሰረታዊ መብቶችን ወይም ትምህርት ወንጌልን የሚቃወሙ መመሪያዎችን የሚያወጡበት ጊዜ መመሪያዎቹን ላለመቀበል ኅሊናቸው ያስገድዳቸዋል፡፡ ትእዛዞቻቸው ትክክለኛ ኅሊና ሊቀበለው ከሚችለው በተፃራሪነት የሚቆሙ ከሆነ ለባለስልጣናቱ አለመታዘዝ በትክክለኝነት የሚወሰደው እግዚአብሔርን በማገልገልና ፖለቲካዊውን ማኅበረሰብ በማገልገል መካከል ባለው ልዩነት የተነሳ ነው፡፡ “ስለዚህ የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚብሔር የሆኑትን ለእግዚአብሔር ስጡ፡፡” ማቴ. 22፡21 “ለሰዎች ከመታዘዝ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባናል፡፡” ሐ.ሥራ 5፡29

ዜጐች ከተሰጠው የሥልጣን ገደብ በመተላለፍ በጭቆና መንግስታት አገዛዝ ሥር በወደቁ ጊዜ እንኳ ለጋራ ጥቅም ተጨባጩ ሁኔታ የሚጠይቀውን ለመስጠት ወይም ለማድረግ ወደ ኋላ ማለት የለባቸውም፡፡ ሆኖም ዜጐች በባሕሪያዊ ህግና በመንጌል የታዘዙትን ትእዛዛት ሳይጥሱ ስለ መብቶቻቸውና ባለሥልጣናት የመብት ረገጣ ስለደረሰባቸው ወገኖቻቸው መብቶች የመከላከል ሕጋዊነት አላቸው፡፡

ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት ሁኔታዎች ካላጋጠሙ በስተቀር በፖለቲካዊ ባለሥልጣናት የሚደረግ ጭቆና በትጥቅ ትግል ለማስወገድ መታገል ሕጋዊ አይደለም፡፡ ሁኔታዎቹ፣ 1. ረጅም ጊዜ የቆየ የመሰረታዊ መብቶች መጣስ፣ 2. ጭቆናን ለማስወገድ የተደረጉ ጥረቶች ሁሉ ፍሬ አልባ መሆን፣ 3. ጭቆናን ለማስወገድ የሚደረገው ጥረት የባሰ ረብሻን የሚያስከትል መሆን፣ 4. ድል የማድረግ አስተማማኝ ተስፋ ያለ ከሆነ እና፣ 5. የተሻለ መፍትሔ ይገኛል ብሎ ለማመን በቂ ምክንያት እንደሌለ የታመነ እንደሆነ ነው፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት