ትሕትና ያልተለየው ልባዊ ንቃት

ትሕትና ያልተለየው ልባዊ ንቃት

የተለመደ የጸሎት ጊዜ ችግር የሐሳብ መበታተን መሆኑ እውን ነው፡፡ የሐሳብ መበታተን በቃል ጸሎት ወቅት ቃላትንና ትርጉማቸውን ሊያዛባ ይችላል፤ የሀሳብ መበታተን የምንጸልይለትን እርሱን በቃል ሥርዓተ አምልኳዊ (ማኅበራዊ) ወይም ግላዊ ጸሎት፤ የህሊና ምርመራና የማሰላሰል ጸሎትን ይበልጥ በጥልቀት ሊመለከት ይችላል፡፡ የሚያስፈልገው ወደ ልባችን መመለስ ሆኖ ሳለ የሀሳብ መበታተንን ለማዳን መነሳት በወጥመዱ መውደቅ ይሆናል፤ የሐሳብ መበታተን ከምን ጋር እንደተሳሰርን ይገልጽልናልና፡፡ ይህ በጌታ ፊት የሚሆን ትሁት ግንዛቤ ለእርሱ የሚኖረንን ፍቅር ሊያነቃቃና ያነጻልንም ዘንድ ልባችንን በቆራጥነት እድንሰጠው ሊገፋፋን ይገባል፡፡ እንግዲህ ውጊያው እዚህ ላይ ነው ለየትኛው ጌታ ማደር እንደሚሹ መምረጥ፡፡

በአዎንታዊ አገላለጽ፣ ሁሉን የራሱ ማድረግና ሁሉንም በራሱ ቁጥጥር ሥር ማድረግ የሚፈልገው ከገዛ ራስ ጋር የሚደረግ ውጊያ ንቃትንና ልብን መግዛትን ይጠይቃል፡፡ ኢየሱስ ነቅቶ ስለመጠባበቅ ሲያስተምር እርሱ የሚመጣበት ጊዜ መጨረሻዋ ቀን በእለቱ ዛሬም ቢሆን ሊሆን እንደሚችል በጥብቅ ያሳስባል፡፡ ሙሽራው በእኩለ ሌሊት ይመጣል፣ መጥፋት የሌለበት መብራት የእምነት ብርሃን ነው፤ ልቤ ፊቱን እሻ! ና! ይለኛል፡፡

ሌላው ችግር፣ በተለይ ከልባቸው መጸለይ ለሚፈልጉ፣ የሚሉት ነገር ጭራሽኑ ማጣት መድረቅ ነው፡፡ ይህ ችግር የሚያጋጥመው የትዝታ፣ የስሜት የሀሳብ ፍላጐት መንፈሳዊም ቢሆን እንኳን ሊጠፋ ልብ ከእግዚአብሔር በመለየቱ በማሳየቱ በማሰላሰል ጸሎት የሚደርስ ችግር ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ጊዜ ብርቱ እምነት በሰፈነበት መንፈስ ተሞልተን ከኢየሱስ ጋር በስቃዩና በሞቱ አንድ የምንሆንበት ወቅት ነው፡፡ “የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፣ ከሞተች ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች፡፡” ቃሉ በጭንጫ መሬት ላይ በመውደቅ ላይ የመድረቅ ምንጩ ሥር ማጣት ከሆነ ውጊያው መለወጥን ይሻል፡፡

 

በጸሎት ወቅት የሚያጋጥም ፈተናን መቋቋም

እጅግ የተለመደው ግን ስውሩ ፈተና እምነት ማጣታችን ነው፡፡ እምነት ማጣታችን የሚገለጸው ይፋዊ በሆነ አለማመናችን ሳይሆን ተጨባጭ በሆነ ምርጫችን ነው፡፡ መጸለይ ስንጀምር በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሥራዎች ወይም አስቸኳይ ተብለው የሚታሰቡ ጉዳዮች ቅድሚያ ይሰጣቸው ዘንድ ይፎካከራሉ፡፡ ሁኔታው ዳግም ለልባችን የእውነት ወቅት ነው፤ እውነተኛ ፍቅሩ ምንድን ነው? አንዳንድ ጊዜ ጌታን እንደ መጨረሻ መጠጊያ በማድረግ ወደ እርሱ እንመለሳለን ግን እንደዚያ መሆኑን በትክክል እናምናለንን? አንዳንድ ጊዜ ጌታን እንደ ወዳጅ እንቆጥረዋለን፡፡ ነገር ግን ልባችን በራሱ እንደተኩራራ ነው፡፡ በሁሉም ሁኔታዎች እምነት ማጣታችን የትሑት ልብን ባህርይ ገና እንዳልተጋራን ያሳያል፡፡ “ያለ እኔ ምንም ማድረግ አትችሉም፡፡”

ስንፍና በርን የሚከፍት ሌላው ፈተና ነው፡፡ መንፈሳውያን ጸሐፍት እንደሚያስገነዝቡን ስንፍና፣ ማለትም የመንፈስ መዛል የሚስፋፋው የብቃትን ልማድ ችላ ከማለት፣ ንቃትን ከማላላትና ከልብ ቸልተኝነት ነው፡፡ “… መንፈስ ተዘጋጅታለች፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው፡፡” ማቴ. 26፡41 ከፍታ ወደላይ በጨመረ መጠን አወዳደቅም የከፋ ይሆናል፡፡ ተስፋ መቁረጥ የሚያም ቢሆንም የአጉል ድፍረት ተቃራኒ ነው፡፡ ትሑታን በጭንቀታቸው አይደነቁም፤ ይልቁንም ይበልጥ እንዲያምኑ በጽናትም እንዲቆሙ ያደርጋቸዋል እንጂ፡፡