እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የኢየሱስ የጸሎት ሰዓት

የኢየሱስ የጸሎት ሰዓት

gesu03"ሰዓቱ" በደረሰ ጊዜ ኢየሱስ ወደ አብ ጸለየ፡፡ በወንጌል የሰፈነው እጅግ ረጅሙ ጸሎት መላውን የፍጥረትን የድኅንነትን ሥራ እንዲሁም ሞቱንና ትንሣኤውን ያጠቃልላል፡፡ ልክ ፋሲካው "ለአንዴና ለሁሌም" በቤተክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮ ውስጥ እንደሚኖር ሁሉ የኢየሱስ የመጸለያ ሰዓትም ሆኖ የእርሱ ይዘልቃል፡፡

ክርስቲያናዊ ትውፊት ይህንን ጸሎት የኢየሱስ "ክህነታዊ" ጸሎት በትክክል ይጠራዋል፡፡ ይህ ጸሎት ከመሥዋዕቱ ሙሉ ለሙሉ ወደ "ተቀደሰለት" ወደ አብ ከማለፉ ከፋሲካዋ ጋር የማይነጣጠል የሊቀ ካህናችን ጸሎት ነው፡፡

በዚህ ፋሲካዊና መስዋዕታዊ ጸሎት ሁሉም ነገር በክርስቶስ ይጠቃለላል፡፡ አምላክና ዓለም፣ ቃልና ሥጋ፣ ዘላለማዊ ሕይወትና ጊዜ፣ ራስን አሳልፎ የሚሰጥ ፍቅርና እሱን የሚክደው ኃጢአት፤ ያላት ደቀ መዛሙርትና እነርሱን በመስማት በኢየሱስ የማያምኑ ሰዎች፤ ውርደትንና ክብር ከዚህ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ ይህ ጸሎት የአንድነት ጸሎት ነው፡፡

ኢየሱስ የአብን ሥራ ሙሉ በሙሉ ፈጽሟል፤ ጸሎቱ እንደ መስዋዕቱ እስከ ጊዜ ፍጻሜ ይደርሳል፡፡ የዚህ ሰዓት ጸሎት በፍፃሜ ዘመናትን ይመስላል፣ ወደ ፍጻሜአቸውም ያደርሳቸዋል፡፡ አብ ሁሉን ነገር የሰጠው ልጁ ኢየሱስ፣ራሱን ሙሉ በሙሉ መልሶ ለአብ አስረክቦአል፤ ይሁን እንጂ አብ በሥጋ ላይ ሁሉ በሰጠው ሥልጣን በታላቅ ነፃነት ራሱን ይገልፃል፡፡ ራሱን አገልጋይ ያደረገ ወልድ ሁሉን የሚችል ጌታ ነው፡፡ ስለእኛ የሚጸልየው ሊቀ-ካህናት በውስጣችን የሚጸልየው ጸሎታችንንም በሚሰማው እግዚአብሔር ነው፡፡

ወደ ጌታ ኢየሱስ ቅዱስ ስም በመግባት "አባታችን ሆይ" ሲል የሚያስተምረንን ጸሎት በልባችን መቀበል እንችላለን፡፡ ክህነታዊው ጸሎቱ ከውስጥ በሚመነጭ ሁኔታ የአባታችን ሆይን ታላቅ ልመና፣ ለአብ ስም የሚኖር መቆርቆርን፤ ለመንግሥቱ ክብር የሚኖር የላቀ ቀናኢነትን የአብ ፈቀድና የድኅንነት እቅዱ መፈጸም፤ እንዲሁም ከክፋት ነፃ መሆንን ከፍፃሜ ያደርሳል፡፡

በመጨረሻ በዚህ ጸሎት ኢየሱስ የጸሎት ሕይወት ዋኛ ምስጢር የሆነውንና የማይነጣጠለውን የአብና የወልድን "ዕውቀት" ይገልጥልናል፤ ይሰጠናልም፡፡

ምንጭ፡ የካቶሊክ ትምህርት ክርሰቶስ - ቁጥር 2725-2751

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት