ጸሎታችን አልተሰማም ብለን ለምን እናማርራለን?

ጸሎታችን አልተሰማም ብለን ለምን እናማርራለን?

በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ሁኔታ መገረም ይገባናል፡፡ ለሰጠን ሁሉ ባጠቃላይ እግዚአብሔርን ስናወድስ ወይም ስናመሰግን ጸሎታችን በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ይኑረው ወይም አይኑረው እምብዛም አንጨነቅም፤ በሌላ በኩል ደግሞ የልመናዎቻችንን ውጤቶች ማየት እንሻለን፡፡ ጸሎታችንን የሚያነቃቃው የእግዚአብሔር አምሳል ምንድን ነው? መጠቀሚያ መሣሪያ ነውን? ወይስ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት?

"እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን" ሮሜ 8፡26 አለማወቃችንን አምነናልን? እግዚአብሔርን የምንለምነው "ለእኛ የሚጠቅመንን ነው"? "እኛ ከመለመናችን በፊት አባታችን የምንፈልገውን ያውቃል"፣ ማቴ. 6፡8 ነገር ግን ልመናችንን ይጠብቃል፣ ምክንያቱም የልጆቹ ክብር የተመሠረተው በነፃነታቸው ላይ ነውና፡፡ ስለዚህ የሚፈልገውን ነገር በእርግጥ ማወቅ እንችል ዘንድ ከእርሱ የነፃነት መንፈሰ ጋር አብረን መጸለይ አለብን፡፡ ሮሜ.8፡27

ለምቾታችሁ ታውሉት ዘንድ በክፋ ትለምናላችሁና አትቀበሉም በተከፋፈለ ልብ ከጸለይን፣ እኛ "አመንዝራዎች" ነን፤ የሚመኝልን ደህንነታችንን፣ ሕይወታችንን ነውና እግዚአብሔር ሊሰማን አይችልም፡፡ "ወይስ መጽሐፍ በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል ያለው በከንቱ እንደተናገረ ይመስላችኋል?" ያዕቆብ 4፡5 እግዚአብሔር ለእኛ "ቀናተኛ" መሆኑ የፍቅሩን እውነተኛነት የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ ወደ መንፈስ ቅዱስ ፍላጐት ከገባን ጸሎታችን ይሰማል፡፡

እግዚአብሔር ይሰጥህ ዘንድ የለመንከውን ነገር ወዲያውኑ ባለመግኘትህ አትጨነቅ፤ ምክንያቱም አንተ ጸሎትህን ሳታቋርጥ ከእርሱ ጋር በቆየህ መጠን ከጠየቅኸው የበለጠም ሊሰጥህ ይፈልጋልና፡፡

Evagrius Ponticus, De oratione

እርሱ ያዘጋጀልንን ነገር መቀበለ እንድንችል ዘንድ እግዚአብሔር ፍላጐታችን በጸሎት እንዲገለጽ ይሻል፡፡

St. Augustine