ጸሎታችን ውጤታማ የሚሆነው እንዴት ነው?

ጸሎታችን ውጤታማ የሚሆነው እንዴት ነው?

በድኅነት አቅድ ውስጥ የጸሎት መገለጥ የእምነት መሠረቱ በታሪክ ውስጥ በሚከሰተው በእግዚአብሔር ስራ ላይ እንደሆነ ያስተምረናል፡፡ የልጅነት አመኔታችን እጅግ የላቀ ሥራ በሆነው በልጁ ሕማማትና ትንሣኤ ተቀጣጥሏል፡፡ የክርስቲያን ጸሎት እግዚአብሔር ስለ ሰዎች ካለው መለኮታዊ ጥበቃና ከፍቅሩ እቅድ ጋር የሚደረግ ትብብር ነው፡፡

ለቅዱስ ጳውሎስ ይህ የአመኔታ ድፍረትን ያገኘው በውስጣችን ባለው መንፈስ ቅዱስ ጸሎት እና አንድያ ልጁን በሰጠው በአብ ታማኝ ፍቅር ነው፡፡ ሮሜ 1ዐ፡ 12-13፤8፡ 26-39 የሚጸልየው ልብ መለወጥ ለልመናችን የሚሰጥ ተቀዳሚ ምላሽ ነው፡፡

የኢየሱስ ጸሎት የክርስቲያንን ጸሎት ውጤታማ ልመና ያደርገዋል፡፡አርአያውም እርሱ ነው፤ እርሱ በእኛ ውስጥ ከእኛም ጋር ሆኖ ይጸልያል፡፡ የወልድ ልብ አብን የሚያስደስተውን ነገር ብቻ የሚፈልግ ከሆነ የልጅነትን ጸጋ ያገኙት ጸሎት እንደምን በስጦታዎቹ ላይ ማተኮር ይችላል?

ኢየሱስ በእኛ ቦታ ሆኖ በእኛ ስም ስለእኛ ይጸልያል፡፡ ልመናዎቻችንን ሁሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተጠቃልለው የቀረቡት ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ በጮኸ ጊዜ እና አብ በሰማው በትንሣኤው አማካይነት ነው፡፡ ኢየሱስ ስለእኛ አብን ለመማለድ የማየቋርጠው ስለዚህ ነው፡፡ ጸሎታችን በልጅነት አመኔታና ድፍረት በሰፈነበት መንፈስ ከኢየሱስ ጸሎት ጋር የተዋሐደ ከሆነ በስሙ የምንለምነው ሁሉ፣ ከማንኛውም ነገር የሚበልጠውን ስጦታዎችን ሁሉ የያዘውን መንፈስ ቅዱስን እንኳን እናገኛለን፡፡