በፍቅር መጽናት

በፍቅር መጽናት

"ባለመቋረጥ ጸልዩ፣... በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ነገር እግዚአብሔር አብን ዘወትር አመስግኑ፡፡" 1ተሰ.5፡17፤ኤፌ5፡2ዐ ቅዱስ ጳውሎስ "በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ሰለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤" ኤፌ 6፡18 ሲል ያክልበታል፡፡ ምክንያቱም "ያለማቋረጥ ለመሥራት፣ ነቅተን ለመጠበቅና ለመጾም አልታዘዝንም ነገር ግን ያለማቋረጥ እንድንጸልይ ተደንግጓል፡፡ ይህ መታከት የማይታይበት የጋለ ስሜት ሊመጣ የሚችለው ከፍቅር ብቻ ነው፡፡ ከእኛ ቀዝቃዛነትና ስንፍና አንፃር የጸሎት ውጊያ ትህትና፣ እምነትና ጽናት የተላበሰ ፍቅር ነው፡፡ ይህ ፍቅር ልባችን እምነትን በሚጠቁሙ አስረጂና ገላጭ ሕይወት ሰጪ በሆኑ ሦስት ቁም ነገሮች ላይ እንዲያተኩር ያደርጋል፡፡

ሁልጊዜ መጸለይ ይቻላል፡- የክርስቶስ ዘመን፣ ምንም ዓይነት ማዕበሎች ይነሡ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር የሆነው የተነሣው ክርስቶስ ነው፡፡ ጊዜአችን በእግዚአብሔር እጅ ነው፡፡

በሕዝብ መካከል በምትሄዱበት ወይም በእግር በምትጓዙበት ወይም በመደብራችሁ ውስጥ በመግዛት ወይም በመሸጥ ላይ እያላችሁ፡ ... ወይም ምግብ በምታበስሉበት ሰዓት እንኳ የጋለ ልባዊ ጸሎት ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ St. John Chrysostom, Ecloga de oratione

ጸሎት እጅግ አስፈላጊ ነው፡- በተቃራኒው ያለው ማረጋገጫም አሳማኝነቱ ከዚህ የተነሳ አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስ እንዲመራን ካልፈቀድን፣ ወደ ኃጢአት ባርነት ተመልሰን መውደቃችን ነው፡፡ ልባችን ከእርሱ የራቀ፣ መንፈሰ ቅዱስ እንደምን ሕይወታችን ሊሆን ይችላል?

ከጸሎተ ጋር የሚስተካከል ምንም ነገር የለም፤ ምክንያቱም የማይቻለውን እንዲቻል፣ ከባዱንም ቀላል ያደርጋልና፡፡ በጉጉት የሚጸልይ እና እግዚአብሔርን ያለመሰልቸት የሚጠራ ሰው ወደ ኃጢአት አይወድቅምና፡፡

የሚጸልዩ በእርግጥ ይድናሉ፤ የማይጸልዩ ደግሞ በእርግጥም ወደ ፈተና ይገባሉ፡፡

ጸሎትና ክርስቲያናዊ ሕይወት አይነጣጠሉም ምክንያቱም ሁለቱም የሚመለከቱት ከፍቅር የሚመነጨውን ያንኑ ፍቅርና ራስን መካድን ነው፤ ከአብ የፍቅር ዕቅድ ጋር የሚሆን የልጅነትና ፍቅርን የተላበሰ መጣጣም፣ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ይበልጥ በሚያመሳስለን መንፈስ ቅዱስ የሚሆን ለዋጭ አንድነት እንዲሁም ኢየሱስ እኛን የወደደበት ለሰዎች ሁሉ ያለው ያው ፍቅር ነው፡፡ "በስሜ የምትለምኑት ሁሉ አብ ይሰጣችኋል፡፡ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ይህን አዝዛችኋለሁ" ዮሐ 15፡ 16-17

ጸሎትን ከሥራ ጋር፤ መልካም ሥራንም ከጸሎት ጋር የሚያዋሕድ እርሱ "ያለማቋረጥ ይጸልያል፡፡ ያለማቋረጥ የመጸለይን መርሕ ተጨባጭ ሊሆን ይችላል ማለት የምችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡