Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የሰው ልጅ በክፋት ላይ ድልን ለመቀዳጀት የክርስቶስ መስቀል ያሰፈልገዋል

ራድዮ ቫቲካን -  ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛው ከትላንትና በስትያ ለቆጵሮስ ውሉደ ክህነት፣ ገዳማውያን እና ዲያቆናት በኒቆስያ በሚገኘው በቅዱስ መስቀል ቤተ ክርስትያን የቀረበውን መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት፦ ብዙዎች ክርስትያን የስቃይ የእስራት እና የግርፋት ምልክት የሆነውን መሣሪያ እንዴት ያመልካሉ በማለት ይጠይቁ ይሆናል፣ ለኛ ክርስትያኖች ይህ መሣሪያ ስለእኛ ብሎ ውርደታችንን የራሱን በማድረግ እኛን በማዳን በማያዳግም ተግባር የእግዚአብሔር ፍቅር በክፋት ላይ ድል የነሳውን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በመሆኑ፣ የድህነታችን ምልክት ነው።

መስቀል ተራ የግል የአምልኮ መግለጫ መሣሪያ እና የመለያ ምልክት ብቻ ሳይሆን ከተአምኖተ ኃይማኖት ወይም ካንድ የፍልስፍና አመለካከት አስገዳጅነት የሚሰጥ ምልክት ሳይሆን ስለ ተስፋ፣ ስለ ፍቅር፣ ሁከት በሰላም መሣሪያ ውድቅ እንደሚሆን የሚያበስር እግዚአብሔር ትሁታንን ከፍ ያደረገበት መለያየትን ውድቅ ያደረገበት ፍቅር በጥላቻ ላይ ድል የነሳበት የድህነት ታሪክ የሚያወሳ ምልክት ነው ብለዋል።

ስለዚህ የተሰቀለውን ኢየሱስን ስናበሥር እራሳችን ወይንም እኛነታችንን ሳይሆን የምናከብረው፣

እርሱን ጌታን ኢየሱስን ክርስቶስን ነው የምናበሥረው። የራሳችንን ጥበብ እና ብርታት ለዓለም የምናበሥርበት ሳይሆን የእርሱ ማለትም የእግዚአብሔር ፍጹም ጥበብ ፍቅር እና የእርሱ የማዳን እቅድ የምንገልጥበት፣ ዓለም የተጠማው እና ሊሰማው የሚፈልገው የድህነት ሓቅ መሣሪያ በመሆን፣ የእዚአብሔር የማዳን እቅድ እርግጠኛነቱን የምናበሥርበት መሣሪያ ነው። የእኛ ውሱንነት የማይበግረው እውነተኛነቱን የማያሳንሰው የፍጹም ፍቅር ተጨባጭ መግለጫ ነው ብለዋል።

የክርስትናው እምነት የውሁዳን እምነት በሆነባቸው የጎሳ እና የሃይማኖት ውጥረት በሚታይባቸው ክልሎች የሚኖረው ማኅበረ ክርስያን እና ውሉደ ክህነት ለመሰደድ ፈተና የተጋለጠ ቢሆንም፣ በዚህ ተጨባጭ ማኅበራዊ ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳይ ሳይበገር እዛው በክልሉ በመቅረት ክርስቶስን መመስከር ለክርስትያኖች ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በክልሉ ለሚኖሩት የላቀው የተስፋ ምልክት ነው እንዳሉም የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።