Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ቡድን እግር ኳስ ተጨዋች በደብሊን ካቶሊክ ቤ/ያን የዲቁና ማዕረግ ተቀበለ።

የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ቡድን እግር ኳስ ተጨዋች በደብሊን ካቶሊክ ቤ/ያን የዲቁና ማዕረግ ተቀበለ።

Deacon Philip38ኛ ዓመት እድሜው ላይ የሚገኘው ዲያቆን ፊሊፕ መልራይን ከወጣት ቡድኑ ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ እ.ኤ.አ. ከ1992-1996-1999 ዓ.ም. የማንቸስተር ዩናይትድ፤ ከ1999-2008 ዓ.ም. ደግሞ በኖርዊች ሲቲ፡ ካርዲፍ ሲቲ፡ ሌይተን ኦሪየንትና ኪንግስ ሊን ቡድኖች የመሀል ሜዳ አጥቂ የእግር ኳስ ተጨዋች የነበረ ሲሆን ባለፈው ቅዳሜ በደብሊን ሊ. ጳጳስ ቤልፋስት መድኃኔዓለም ቤ/ያን ማዕረገ ዲቁናን ተቀብሏል።

ፊሊፕ በነበረው የእግር ኳስ ተጨዋችነት ወቅት ለአገሩ አየርላንድ 27 ጊዜ ተሰልፏል። አብዛኛውን ጊዜ በነበረው ደረጃ የሚገኙ ሰዎች ጫማቸውን ሲሰቅሉ ወደ አሰልጣኝነት ወይም በመገናኛ ብዙኃን የኳስ ሐተታ ባለሙያ ሲሆኑ እርሱ ግን “ጥሪዬ ነው” ብሎ ወዳመነበት መንፈሳዊ ሕይወት አዘንብሎ የተለያዩ የበጎ አድራጎቶችን ሲያበረክት ቆይቶ እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. የዶሚኒካን ገዳምን ተቀላቅሏል።

በመቀጠልም ለክህነት ዝግጅት የሚያስፈልገውን የሁለት ዓመት የፍልስፍና ትምህርት በሮም በማጥናት አራት ዓመት የሚወስደውን የነገረ መለኮት ትምህርት የመጨረሻ ዓመት በአየርላንድ በማድረግ ላይ ይገኛል። የአየርላንድ ዶሚኒካን ወንድሞች ድረ ገጽ እንደሚገልጸው ከጥቂት ወራት በኋላ የክህነትን ሢመት ተቀብሎ ሕዝበ እግዚአብሔርን የሚያገለግል መሆኑ ታውቋል።

ምንጭ፡- http://www.bbc.com/news/uk-northern-ireland-37820819

-      http://www.dailymail.co.uk/sport/football/article-3890752/Former-Manchester-United-footballer-Philip-Mulryne-Catholic-priest-ordained-Belfast.html

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።