Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የር.ሊጳ. ፍራንቼስኮስ የ2009 ዓ.ም. ፋሲካ ሌሊት ቅዳሴ ስብከት

Easter 2009EC Popeበመላው ዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በከፍተኛ ድምቀት ማክበራቸው ይታወቃል። የዚህ በዓል አንድ ክፍል በሆነው በእለተ ፋሲካ ማለትም በሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም. ቅዳሜ ምሽት የትንሣኤ ዋዜማ መስዋዕተ ቅዳሴ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ መሪነት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ዐቢይ ደብር ካህናት፣ ደናግላን፣ ገዳማዊያን እና ገዳማዊያት እንዲሁም ተለያዩ ሀገራት ልዑካን፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ አልፉል። በእለቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙትን ስብከት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል። 
“ሰንበት ካለፈ በኋላ፣ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ጎሕ ሲቀድ፣ ማርያም መቃብሩን ሊያዩሄዱ”። (ማቴዎስ 28፡1)

ይህንን መንገድ እንዴት እንደ ተጓዙ መገመት እንችላለን፣ በጥርጣሬ እና ግራ በተጋባ ስሜት፣ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ለማመን የሚከብድ ነገር ነው በመለት ወደ ቀብር ስፍራ እንደሚጓዙ ሰዎች ዓይነት ጉዞ ነው ያደረጉት። የፊታቸውንም ገጽታ የገረጣ እና በእንባ የራሰ እንደ ነበር መገመት እንችላለን። እውነት ፍቅር ሞቷል ወይ? የሚል ጥያቄም ነበራቸው።
ጌታቸው በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት የመጨረሻውን እስትንፋሱን ሲተነፍስ በቦታው እንደ ነበረውና በመቃብር ውስጥ ኢየሱስን እንዳስቀመጠው የአርማቲያ ሀገር ሰው የነበረው ዮሴፍ እና እንደ ደቀ መዛሙርቱ ሴቶችም በእዚያው ተገኝተዋል። እነዚህ ሁለት ሴቶች ከእርሱ አልሸሹም፣ በጽናት ቁመውም ነበር፣ ሕይወትን እንደ አመጣጡ ተጋፍጠውትም ነበር፣ አድሎ ወይም የፍትህ መጓደል ምን ዓይነት መራር ነገር እንደ ሆነም አውቀውታል። በመቃብሩ ፊት ለፊት በኀዘን ተውጠው እናገኛቸዋለን፣ ነገር ግን በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጉዳይ በዚህ መልኩ ይጠናቀቃል ብለው መቀበል አዳግቶዋቸዋል።
እኛ ይህንን ትዕይንት ለማሰብ በምንሞክርበት ወቅት የእነዚያን ሴቶች የተለያዩ የፊት ገጽታዎችን በምናባችን በማሰብ በአድሎ ምክንያት ከፍተኛ ሸክም እና አስከፊ ነገር ውስጥ የገቡትን የእናቶቻችን እና የአያቶቻችንን ፊት እንዲሁም የሕፃናት እና የታዳጊ ወጣቶችን ፊት መገመት እንችላለን። የእነዚህ ሴቶች የፊት ገጽታ ላይ በየከተማችን መንግዶችላይ የሚገኙ በአስከፊ በሆነ ድኽነት የሚሰቃዩ፣ ለሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ፣ በአሳዛኝ ሁኔታ የተበዘበዙ ወይም መጠቀሚያ የሆኑ ሰዎችን ፊት ያንጸባርቃሉ። በተጨማሪም ሀገራቸውን፣ ቤተሰቦቻችውን እና ቤታቸውን ጥለው ተሰደው በመምጣታቸው ብቻ ለንቀት የተዳረጉ ሰዎችን ፊትም ማየት እንችላለን። እጆቻቸው የተጨማደዱእና የተተለተሉ በመሆናቸው ምክንያቱ ብቻ መገለላቸው እና ብቸኛ መሆናቸውን ፊታቸው ላይ ማንበብ እንችላለን። የእነርሱ ፊት የልጆቻቸው ሕይወት በከፍተኛ ሙስና ምክንያት መብቱን ሲገፈፍ እና ሕልማቸው ሲያጨልም እንደሚያለቅሱ የሴቶች እና የእናቶች ፊት ነጸብራቅ ነው። በየቀኑ በሚፈጸመው የራስ ወዳድነት ተግባር እነዚህን ሰዎች ይሰቅላል ከዚያም የሕዝቡን ተስፋ ይቀብራል። የእነዚያ ሁለት ሴቶች ፊት በየከተማችን መንገዶች ላይ የሚራመዱ ሰባዊ መብታቸው የተሰቀለባቸው ሰዎች ፊት ነጸብራቅ ነው።
የእናንተን እና የእኔን ፊት ጨምሮ የእነዚያ ሴቶች ፊት የብዙኃን ሰዎች ፊት ነጸብራቅም ነው። ልክ እንደ እነሱ እኛም ወደ ፊት እንድንራመድ የሚሰማን ስሜት እና እውነታው በዚህ መልኩ ሊጠናቀቅ ስለ ሚችል ራሳችንን ማግለል እንችላለን። እርግጥ ነው እኛ በውስጣችን የእግዚኣብሔርን ቃል ኪዳን እና የእግዚአብሔርን ታማኝነት በእርግጠኛነት እንሸከማለን። ነገር ግን ለራሳችን እና ለሌሎች ታማኝ ያልሆንባቸውን ብዙ አጋጣሚዎችን፣ ያደረግነውን ጥረት እና ጥረት አድርገን የተሸነፍንባቸውን ነገሮች ሁሉ ያካተተ ጠባሳ በፊታችን ላይ ይታያል። በልባችን ውስጥ ያሉ ነገሮች ከእዚህ የተለየ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ሳናስበው ተስፋ በመቁረጥ በመቃብር ውስጥ መኖርን እንለማመዳለን። ከእዚህም በከፋ መልኩ ይህ ነገር የሕይወት አንዱ ሕግ እንደ ሆነ አድርገን ራሳችንን እናሳምናለን፣ የማምለጫ መንገዶችን በመዘየድ ሕሊናችንን አደንዝዘን አምላክ በአደራ የሰጠን ተስፋ እንቀብራለን። ስለዚህም በአንድ በኩል ለእግዚኣብሔር ያለን ፍላጎት እና በሌላ በኩል ደግሞ ከጨለማ መላቀቅ አቅቶን በእነዚህ ሁለት ነገሮች ውስጥ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተን ልክ እነዚህ ሁለት ማሪያሞች እንዳደጉት ዓይነት ጉዞ እኛም በዚህ መንገድ ላይ ብዙን ጊዜ እንጓዛለን። ጌታ ብቻ ሳይሆን የሞተው ተስፋችንም ከእርሱ ጋር ሞቷል።
“እነሆ በድንገት ታላቅ የምድር መናወጥ ተከሰተ”። እነዚህም ሴቶች ልክ አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር በእግራቸው ሥር ሆነ መሬቱን እንዳንቀጠቀጠው ዓይነት ስሜት ስለተሰማቸው በድንገት ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገቡ። በተጨማሪም አንድ ሰው ወደ እነርሱ መጥቶ “እናንተስ አትፍሩ” ካላቸው ቡኃላ “እርሱ እንደ ተናገረው ከሙታን ተነስቷል” በማለት ጨምሮ ነገራቸው። ይህም መልእክት ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ ዛሬ እዚህ ቅዱስየሆነ ምሽት ላይ በመድረስ “ወንድሞች እና እህቶች በፍጹም አትፍሩ እርሱ እንደ ተናገረው ከሙታን ተነስቱዋል” ይለናል። በመስቀል ላይ የጠፋው ሕይወት ዛሬ እንደ ገና እንደ አዲስ ይነቃል። የኢየሱስ የልብ ምት እንደ ስጦታ ተሰጥቶናል አዲስ አድማስም ከፍቶልናል። የጌታ የልብ ምት ተሰጥቶናል እኛም በአንጻሩም ይህንን የልብ ምት ወደ አንድ ለዋጭ ወደ ሆነ ኃይል እና አዲስ ስብእና እንድንፈጥር እንዲረዳን ልንጠቀምበት ይገባል። ክርስቶስ በትንሣኤው የመቃብሩን ክዳን የነበረውን ድንጋይ ከፍቶታል፣ እኛንም ቆልፎ ከያዘን ስጋት፣ ደኅንነትን ከመግዛት ፍላጎት እና እኛ ሥልጣናችንን የሌሎችን ሰባዊ መብትን ለመግፈፍ ከመጠቀም ፍላጎቶቻችንም ነፃ ያወጣናል።
የካህናት አለቆች እና የሐይማኖት መሪዎች ከሮማዊያን ጋር በግጭት ላይ በነበሩበት ወቅት ሁሉንም ነገር በስሌት እንወጣዋለን የሚል እምነት ነበራቸው፣ ለዚህም የመጨረሻ የሆነውን ቃል ተናገሩ፣ ቃላቸውንም በተግባር በፈጸሙበት ወቅት እግዚኣብሔር በድንገት በመምጣት አበሳጭ የሆኑ ሕግጋታቸውን በመሻር አዳዲስ የሆኑ አጋጣሚዎችን ፈጠረ። እግዚኣብሔር ሊፈጥር እና አዲስ የሆነ የአጋጣሚ ዘመን የሆነውን የምሕረት ዘመን ሊሰጠን እና ሊገናኘን በድጋሚ ይመጣል። ይህም ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበረ ቃል ኪዳን ነው። ይህም እግዚኣብሔር በእርሱ ለሚያምኑ ሕዝቦቹ በድንገት የሚሰጣቸው ስጦታ ነው። ዝግጁ የሆነ ሕይወት ከእንቅልፉ ይነቃ ዘንድ በውስጣችሁ የተደበቀ የትንሣኤ ዘር ስላለ ደስ ይበላችሁ!
በዚህ ምሽት እንድናውጀው የተጠራነው የኢየሱስን የልብ ምት ነው። ኢየሱስ በሕይወት አለ። የመቅደላዊት ማሪያምና የሌላኛዋን ማሪያም ሰላም የፈጠነ እንዲሆን ያደረገው ይህ ነው። ለዚህም ነው በፍጥነት መልካም ዜናውን ለማብሰር የተመለሱት። የሐዘን ቁርበታቸውን እና ሐዘንተኛ ገጽታቸውን አውልቀው እንዲጥሉ ያደረገውም ይሄው ራሱ ነው። ወደ ከተማ ተመልሰው ከሌሎች ጋር እንዲገናኙ ያነሳሳቸውም ይህ ነው።
እኛም እንደ ሁለቱ ሴቶች የኢሱስን መቃብር አይተናል፣ ስለዚህም ወደ ከተማ ከእነርሱ ጋር እንድትሄዱ ጠይቃችኃለሁ። እኛ ሁላችን አካሄዳችንን ተመልክተን የፊታችን ገጽታ መቀየር ይኖርብናል። ከእነርሱ ጋር ተመልሰን በመሄድ የቀብር ስፍራ የሕይወት መደምደሚያ የመጨረሻው ስፍራ አድርጎ ለሚቆጥሩ ሁሉ፣ ሞት ከእዚህ ምድር የመገለያው ብቸኛ መንገድ በሚመስልበት ስፍራ ሁሉ መልካም ዜናውን ለማብሰር እንውጣ። ለማብሰር፣ ለመካፈል፣ እውነት ምን እንደ ሆነ ለመግለጥ ጌታ በሕይወት መኖሩን ለመግለጽ እንውጣ። ተስፋቸው የተቀበረባቸው የሚመስሉ ፊቶች፣ ሕልማቸው ለተቀበረባቸው፣ መብታቸው ለተቀበረባቸው ሰዎች ሁሉ እርሱ ኑዋሪ እንደ ሆነ እና እነርሱንም እንደ ሚያስነሳ ማወጅ ይገባል። መንፈስ ቅዱስ በዚህ መንገድ ላይ እንዲጓዝ የማንፈቅድለት ከሆንን እኛ ክርስቲያኖች አይደለንም ማለት ነው።
ሰለዚህም እንሂድ! በዚህ ድንገተኛ በሆነ አዲስ ንጋት እና ኢየሱስ ብቻ ሊሰጠን ከሚችለው አዲስነትን ለመቀበል እራሳችንን ዝግጁ እናድርግ። የእርሱ ርኅራኄ እና ፍቅር እርምጃችንን እንዲመራው እንፍቀድለት። የእርሱ የልብ ምትየደከመውን የልባችንን ምት ያፋጥነው ዘንድ እንፍቀድለት።

ምንጭ፡- የቫቲካን ሬድዮ ድረ ገጽ

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።