Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የቅብጥ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክና ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ መሠረታዊ የመቀራረብ ሰነድ ፈረሙ

Pope Patriarch Ecumenical doc webያለፈው ቅዳሜ የተገባደደው የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ የግብጽ ጉዞ ትልቁ ተግባራዊ መገለጫ የሆነው ክንዋኔ የቅብጥ ኦርቶዶክስ ቤ/ያን ፓትሪያርክ ከሆኑት ከቴዎድሮስ ዳግማዊ ጋር ያደረጉት ግንኙነትና የተፈራረሙት የአንድነት ሰነድ ነው። በሁለቱ ኃላፊዎች ግንኙነት ወቅት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ጥምረት በሰማእታት ደም ይበልጥ የተሳሰረ መሆኑንና ይህንንም አንድነት በተሻለ መልኩ በፍቅር ድርጊቶች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሁለቱ አባቶች በነበራቸው ግንኙነት ከ1965 ዓ.ም. ጀምሮ በጥናትና በጸሎት ሲካሄድ የቆየ አንድነትን የማጠናከር እንቅስቃሴ ላይ ተመርኩዘው የደረሱባቸው የጋራ ነጥቦችን ገልጸዋል፤ በዚህም መሠረት ሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት በሐዋርያዊ ትውፊት ላይ ተምርኩዘው “አንድም ሦስትም በሆነ አምላክ ማመንን”፣ “ብቸኛ ከአብ የተወለደው ወልድን መልኮታዊነት፣ አምላክነቱን በሚመለከት ፍጹም አምላክ፤ ሰውነቱንም በሚመለከት ፍጹም ሰው መሆኑን”፣ እንዲሁም “በሰባቱ ምስጢራትም  መለኮታዊ ሕይወት ለእኛ የሚሰጠንና የምናድግበት መሆኑ”፣ “ድንግል ማርያምን እንደ እውነተኛው ብርሃን እናት፣ የአምላክ እናት /Theotokos/ ማክብርን” እንደጋራ አቋም አጽድቀዋል። የዚህ ሰነድ ሌላኛው ትልቅ እርምጃም ለክፍለ ዘመናት ከቆየው የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መለያየት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አንዱ የሌላውን ምስጢረ ጥምቀት አንድ መሆኑ መቀበል ሲሆን ይህም ወደ አንድነት የሚደረገውን ጉዞ የሚያፈጥንና ልዩነትንም እጅግ የሚያጠብ ነው።

በተጨማሪም ካቶሊኮችና ቅብጥ ኦርቶዶክሶች የሰው ሕይወት ክቡርነት፣ የተክሊል /ጋብቻ/ ሕይወትና የቤተሰብ ኑሮ ቅዱስነትን እንዲሁም ለተፈጥሮ ያላቸው ክብር የጋራ እሴት መሆናቸውም ተግልጿል። ሰነዱ ባጠቃላይ በዓለም ላይ በተለይም ደግሞ በግብጽና በመካከለኛው ምሥራቅ ስለእምነታቸው ስለሚሰደዱና ስለሚገደሉ ክርስቲያኖች ጥልቅ ጸሎት ይደረግ ዘንድም አሳስቧል።

ይህን መሰል መሠረታዊ የመቀራረብ ሂደት በመንበረ ጴጥሮስና በመንበረ ማርቆስ መካከል መሆኑ ይበልጥ ተስፋ ሰጪና ለሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት ወደ መቀራረብና አንድነት የሚያመላክት ጥሩ መንገድ የሚከፍት መሆኑ እሙን ነው።  

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።