ሢመተ ክህነት በሲታውያን ቅ. ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን

ከህነት ዘሲታውያንበእለተ ሰንበት ጥቅት 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ሁለት የሲታውያን መነኮሳት ዲያቆናት ሢመተ ክህነት አዲስ አበባ በሚገኘው ገዳመ ሲታውያን ዘቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ተከናውኗል።

በብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ሱራፌል ደምረው እጅ ክህነት የተቀበሉት አባ ኃይለ ኢየሱስ (ታገሠ) ጳውሎስና አባ ልደተ ማርያም (ልደት) ብዛኒ ናቸው። በብዙ ካህናት ወንድሞቻቸው፣ በመነኮሳት፣ በወዳጅ ዘመዶቻቸው ታጅበው ደማቅ በሆነ መንፈሳዊ ሥርዓት የተከናወነው ሢመት ለእነርሱና ለአገልግሎታቸው ቅድስናን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለማችን ሰላመ ክርስቶስን የሚያበዛ ያድርግልን።

ለመደምደሚያም ለዚሁ ቀን መታሰቢያ በተዘጋጀው ትንሽ ሥዕል ጀርባ ላይ የሰፈረውን የአዲሶቹ ካህናት ጸሎት እንጋራ፦

“እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ!

ለዚህ ቀን ስላደረስከንና በፊትህ እንድንቆም ስላበቃኸን እናመሰግንሃለን።

የረዱንን፣ ቤተሰቦቻችንን፣ መልካም አድራጊዎቻችንን እና የገዳመ ሲታውያን አባቶቻችንንም ባርካቸው።

ከዓለማችን ይህንን አስከፊ በሽታ አርቅልን።” አሜን።