የምንኩስና መሐላ በገዳመ ሲታውያን

2የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን ቤተ ክርስቲያን አዲስ አበባ ወንድም ተመስገን ኩቴ ኩሌ እንደ ሲታዊ መነኩሴ ሆኖ የክርስትናን ፍጽምና ለመኖር የመጨረሻ የምንኩስና መሐላውን አከናውኗል።

ወንድም ተመስገን በ1986 ዓ.ም. በዳውሮ ዞን ማረቃ ወረዳ መዳ ኩይሊ ቀበሌ ተወልዶ፤ በሶዶ ሀገረ ስብከት ዳውሮ ጨጫ ቅ. ገብርኤል ቁምስና ዋካ ምሥጢረ ጥምቀትን፣ ሜሮንና ቅ. ቁርባንን ተቅብሏል።

በ2000 ዓ.ም. ወደ መንዲዳ ገዳመ ሲታውያን በመግባት ከ9ኛ እስከ 10ኛ ክፍል እንዲሁም 10+3 የተግባረድ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ከ2004-2005 ዓ.ም. ልብሰ ምንኩስና በመልበስ የተመክሮ ዓመትን አሳለፈ። በመቀጠልም በአዲስ አበባ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን ገዳም ሆኖ ሦስት ዓመት የፍልስፍናና 4 ዓመት የነገረ መለኮት ትምህርቱን በካፑቺን ፍራንሲስካውያን የፍልስፍናና ነገረ መለኮት ተቋም ተምሮ አጠናቋል።

መነኮሳት አባቶችና ወንድሞች፣ ተጋባዥ ካህናትና ሲስተሮች፣ ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም የቁምስናው ምእመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴው ያረገ ሲሆን በነበረው የወንጌል ንባብና የእለቱ ሥርዓት ተመርኩዘው ክቡር አባ ባዘዘው ግዛው፣ በኢትዮጵያ የሲታውያን ገዳም ኃላፊ፣ ቃለ ስብከትን አስተላልፈዋል። በስብከታቸውም የምንኩስና ሕይወት የእግዚአብሔር መንግስት ነጸብራቅ መሆኑን በመግለጽ፣ ሁላችንም ክርስቲያኖች በምንኩስናም ሆነ በተቀደሰ የጋብቻ ሕይወት በተጠራንበት መንገድ ራስን መስጠት እንደሚያስፈልግና  ለዚሁም በእግዚአብሔር መታመንም ወሳኝ  መሆኑን አስታውሰዋል።

የምንኩስና መሐላ ምእመናንንም የሚመለከት ነው፣ ራሱን የሰጠ ሰው ተገኝቷልና በጸሎት ማጀብ አስፈላጊ ነው፣ ስለ ጥሪ መጸለይ ማለት ነው አካሉ በኋላ

ወጣቶችም ጥሪና ስጦታቸውን አውቀው ክርስትናቸውን በውሳኔ መኖር መቻል እንዳለባቸም መክረዋል።

"ይህን የምንኩስና መሐላ ስንፈጽም የምታስተውሉት መነኮሱ መሬት ላይ ተኝቶ ሲጸለይለት ቆይቶ ተነሥቶ መሐላውን ፈጽሟል። ይህም መሬት ላይ መተኛቱ ለጊዜያዊ ነገሮች የመሞት መነሳቱና መቆሙ ደግሞ ለእግዚአብሔር መንግስት ክብር መቆምን ያሳያል።" አካሉ በኋላ ለእግዚአብሔር ክብር ለ

መኖር ከአምላክ ጋር በጸሎት መቀራረብና አብሮነት አስፈላጊ መሆኑን አስታውሰው የእመቤታችንን እና የቅዱሳንን ረድኤት በመማጸን ስብከታቸውን ደምድመዋል።

miniP1060829P1060816miniP1060833miniP1060827miniP1060827miniP1060839miniP1060836miniP1060845

 
miniP1060851
miniP1060887miniP1060876miniP1060882miniP1060900miniP1060916miniP1060635